ፍቅር? አንድነት? | ፕሬዚደንት ኢሳያስን ለመቀበል የወጡ አንዳንድ ፈረሰኞች ለምን “የኦሮሚያን” ባንዲራ ያዙ?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 19, 2018
ይህ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬ የመራኝ ክሰተት ነው።
ሁለተኛው ክፍል ላይ “ኦሮሞ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” የምትለዋ ከሃዲ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ታቃጥላለች። ለንስሐ ያብቃት!
ለነገሩ ከዚያኛውም ባንዲራ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ፤ የሉሲፈር ኮከብ እስካልተነሳ ድረስ፡ የአንድነትና ፍቅር ጉዳይ ህልም ሆኖ ነው የሚቀረው። ዶ/ር አብይ በሚቀጥሉት ቀናት የሚፈተኑት በሦስት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ነው፤ የሚከተሉትን እርምጃዎች ከወሰዱ፡ ምንም እንኳን በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ጥቃት ሊደርስባቸው ቢችልም፤ በኢትዮጵያውያንና በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ግን ትልቅ ቦታ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህም፦
1ኛ. በአንግሎ–አሜሪካውያን ሉሲፈራውያኖች አስገዳጅነት የተገበረውን የብሔር ፖለቲካና ፌደራሊዝም ካፈረሱ
2ኛ. በአንግሎ–አሜሪካውያን ሉሲፈራውያኖች አስገዳጅነት ክቡሩ ባንዲራችን ላይ ያረፈውን ኮከብ ካስነሱ
3ኛ. አገራችን ከሉሲፈራውያን አረቦችና ቱርኮች ጋር የምታደርገውን ጥብቅ ግኑኝነት ቀስበቀስ ካላሉት
esubalewchekol said
Reblogged this on የጥበብ ጋጋታ በእሱባለዉ ቸኮል.