ውቡ የድልድይ መናፈሻ | “እውነት ይህ ኢትዮጵያ ነውን?” አሉኝ ፈረንጆቹ…
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 19, 2018
ይህን ቪዲዮ ሳሳያቸው።
ከቦሌ ድልድይ እስከ ካዛንቺስ፡ ፀደይ ፪ሺ፲ ዓ.ም
አንዳንዶቹ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የሚያውቁ ናቸው፡ ግን ደርሰው ሲመለሱ የሚያሳዩአቸው ቪድዮችና ፎቶዎች “በጥቁር መነጽር” የሚያዩአቸውን ወይም ለማየት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ብቻ ነው (ኔጋቲቩን፣ መጥፎውን ወዘተ)፤ እጽዋቱን፣ አታክልቶችን፣ አበባዎችንና ለምለሙን ነገር በፍጹም ማየትና ማሳየት አይሹም። ለምን? ምክኒያቱም ኢትዮጵያና አፍሪቃን የሚያዩበት መነጸር በጣም የተለየ ነውና፤ ምክኒያቱም አንጎላቸው በሳሙና ሙለጭ ተደርጎ ታጥቧልና። “የማዝነው ለናንተ ነው” እላቸዋለሁ፤ አይተው እንኳን ማመና መለወጥ ያቅታቸዋልና።
ያ ካናዳዊ የመንገድ ሰባኪ ጓደኛችን እዚሁ ድልድይ ሥር ሆኖ ሲሰብክ ነበር፤ ግን ምን መርጦ እንደቀረጸ፣ ምን ዓይነት ብርሃንና ቀለም እንደተጠቀመ በምስክርነት ማየት እንችላለን።
በዚህ አጋጣሚ፡ እዚህ ድልድይ ስር እነዚህን ውብ አበቦች ለሚንከባከቡት እናቶች አድናቆቴን እገልጻለሁ። እናታዊ ትህትናቸው በጣም ደስ ይላል።
እኛ ዲያስፐራውያን እነዚህን እናቶች፤ በተለይ፤ ቆሻሻ የሚሰብሱብትን እና እንጨትና ጭራሮ ተሸከመው የእንጦጦን ተራራ ለሰዓታት የሚወርዱትንና የሚወጡትን እናቶች ባገኘነው አጋጣሚ ሁላ ልንረዳቸው ይገባናል።
Leave a Reply