Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 19, 2018
ይህን ቪዲዮ ሳሳያቸው።
ከቦሌ ድልድይ እስከ ካዛንቺስ፡ ፀደይ ፪ሺ፲ ዓ.ም
አንዳንዶቹ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የሚያውቁ ናቸው፡ ግን ደርሰው ሲመለሱ የሚያሳዩአቸው ቪድዮችና ፎቶዎች “በጥቁር መነጽር” የሚያዩአቸውን ወይም ለማየት የሚፈልጓቸውን ነገሮች ብቻ ነው (ኔጋቲቩን፣ መጥፎውን ወዘተ)፤ እጽዋቱን፣ አታክልቶችን፣ አበባዎችንና ለምለሙን ነገር በፍጹም ማየትና ማሳየት አይሹም። ለምን? ምክኒያቱም ኢትዮጵያና አፍሪቃን የሚያዩበት መነጸር በጣም የተለየ ነውና፤ ምክኒያቱም አንጎላቸው በሳሙና ሙለጭ ተደርጎ ታጥቧልና። “የማዝነው ለናንተ ነው” እላቸዋለሁ፤ አይተው እንኳን ማመና መለወጥ ያቅታቸዋልና።
ያ ካናዳዊ የመንገድ ሰባኪ ጓደኛችን እዚሁ ድልድይ ሥር ሆኖ ሲሰብክ ነበር፤ ግን ምን መርጦ እንደቀረጸ፣ ምን ዓይነት ብርሃንና ቀለም እንደተጠቀመ በምስክርነት ማየት እንችላለን።
በዚህ አጋጣሚ፡ እዚህ ድልድይ ስር እነዚህን ውብ አበቦች ለሚንከባከቡት እናቶች አድናቆቴን እገልጻለሁ። እናታዊ ትህትናቸው በጣም ደስ ይላል።
እኛ ዲያስፐራውያን እነዚህን እናቶች፤ በተለይ፤ ቆሻሻ የሚሰብሱብትን እና እንጨትና ጭራሮ ተሸከመው የእንጦጦን ተራራ ለሰዓታት የሚወርዱትንና የሚወጡትን እናቶች ባገኘነው አጋጣሚ ሁላ ልንረዳቸው ይገባናል።
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Music | Tagged: ቦሌ ድልድይ, አበባ, አታክልት, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እናቶች, እጽዋት, ካዛንቺስ, ውበት, ዜማ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 19, 2018
ይህ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬ የመራኝ ክሰተት ነው።
ሁለተኛው ክፍል ላይ “ኦሮሞ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” የምትለዋ ከሃዲ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ታቃጥላለች። ለንስሐ ያብቃት!
ለነገሩ ከዚያኛውም ባንዲራ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ፤ የሉሲፈር ኮከብ እስካልተነሳ ድረስ፡ የአንድነትና ፍቅር ጉዳይ ህልም ሆኖ ነው የሚቀረው። ዶ/ር አብይ በሚቀጥሉት ቀናት የሚፈተኑት በሦስት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ነው፤ የሚከተሉትን እርምጃዎች ከወሰዱ፡ ምንም እንኳን በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ጥቃት ሊደርስባቸው ቢችልም፤ በኢትዮጵያውያንና በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ግን ትልቅ ቦታ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህም፦
1ኛ. በአንግሎ–አሜሪካውያን ሉሲፈራውያኖች አስገዳጅነት የተገበረውን የብሔር ፖለቲካና ፌደራሊዝም ካፈረሱ
2ኛ. በአንግሎ–አሜሪካውያን ሉሲፈራውያኖች አስገዳጅነት ክቡሩ ባንዲራችን ላይ ያረፈውን ኮከብ ካስነሱ
3ኛ. አገራችን ከሉሲፈራውያን አረቦችና ቱርኮች ጋር የምታደርገውን ጥብቅ ግኑኝነት ቀስበቀስ ካላሉት
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: ሰንደቅ ዓላማ, ባንዲራ, አዲስ አበባ, ኦሮሚያ ባንዲራ, የኢትዮጵያ, ዶ/ር አብይ አህመድ, ፈረሰኞች, ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቅ | 1 Comment »