ከትናንትና ወዲያ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች በርካታ የዓለማችን መሪዎች በተገኙበት ብሩሴልስ በተካሄደው የኔቶ ጉባዔ የእራት ሥነስርዓት ላይ ነበር ይህ አሳፋሪ ቪዲዮ የተቀረጸው።
የ63 ዓመቱ ዩንከር ወዲያና ወዲህ ሲወዛወዝ የፊንላንድና የዩክሬን ፕሬዚደንቶች እንዲሁም የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ ሲያግዙት ይታያሉ።
የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ፣ ኔቶ፡ ካውካስያኖች የሚባሉትን የነጮችን ጥቅም ለመከላከል የቆመ እርኩስ ድርጅት ነው። በዚህ አጋጣሚ ሉክሰምበርጋዊው ዣን ክላውድ ዩንከር፡ ኃያላን ከሚባሉት ፀረ–ክርስቶስ የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ጋር ሆኖ ይህን ያህል መዋረዱ የእግዚአብሔርን ሥራ ነው የሚያሳያን፤ በዓለም ፊት ገና ብዙ ያዋርዳቸዋል!
ለመሆኑ ይህ ቅሌታም ሰው ለምንድን ነው ሁሌ ሁሉንም የሚስመው!?
[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፴፪፥፴]
“የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።”