ጭካኔ በስዊድን | “ኢትዮጵያዊው” ሙስሊም የቀድሞ ሚስቱን በመጥረቢያ ጨፈጨፋት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 13, 2018
ቪዲዮው የሚያሳያው በስዊድኗ ኡፕሳላ ከተማ መንገድ ላይ ታልፍ የነበረችውን የቀድሞ ሚስቱን፡ አብዲ ሁሴን የተባለው “ኢትዮጵያዊ” በጀርባው የሸጎጠውን መጥረቢያ አውጥቶ ለመጥረብ ሲገሰግስ ነው።
የቀድሞ ሚስቱ ልጆቿን ከመዋዕለ ህፃናት ለማምጣት ስታልፍ ለግማሽ ሰዓት ያህል እዚያ ጠብቋት ነበር ሊያጠቃት የወሰነው። ሴትዮዋን 20 ጊዜ በመጨፍጨፍ ክፉኛ አቁስሏታል። የዓይን ምስክር እንደገለጸው የሴትዮዋ በድን ሰውነት በረዶ ላይ ተዘርሮ ነበር የተገኘው። ሴትዮዋ በህይወት ብትተርፍም የራስ ቅሏ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል፣ አንድ ዓይኗንም አጥታለች።
ባለ 51 ዓመት እድሜው አብዲ ሁሴን ኢትዮጵያ እያለ ሰው ያመጣለትን ይህችን ሴት አገባት፤ ወደ ስዊድን መጥተው አብረው መኖር ከጀመሩ ከ5 ዓመታት በኋላ ነበር የተፋቱት። አብዲ የቀድሞ ሚስቱን በየጊዜው ስለሚያስፈራራት ታስሮ ነበር። በእስር ላይ እያለ ያቀደው የበቀል እርምጃ ስለነበር፡ በገነዘብ ተቀጥቶ፡ ሁለተኛ እንዳይቀርባት ባለፈው የካቲት ወር ላይ ፍርድ ቤት ፈርዶበት ነበር። የልጆቹ እናትም ልጆቿንም ለብቻዋ የማሳደግ መብት እንዲኖራት ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ ወስኖ ነበር።
ባለፈው ዓርብ፡ እብዱ አብዲን ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የ 18 ዓመት እስራት ከፈረደበት በኋላ፡ አሁን ሁለት ዓመት ቀንሶ የ 16 ዓመት እስራት ፍርድ ሰጥቶታል።
ምንጭ፦ Expressen ጋዜጣ
Leave a Reply