ቢያንስ ሦስት የአውራሪስ ቀንድ አራጆች መበላታቸውን የደቡብ አፍሪቃዋ ሲቡያ የአራዊት ተፈጥሮ ፓርክ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፤ ከጫማቸው፣ ባርኔጣቸውና ጠመንጃቸው በቀር የተረፈ አካላቸው አልተገኘም።
ከዕለታት አንድ ቀን፡ አንድ “እግዚአብሔር የለም” የሚል ዒ–አማኒ ነጭ እንዲሁ አንበሶች ወደሚገኙበት ቦታ ለአደን ሄዶ ሳለ ጥይቱ አለቀበት፤ ከዛም ከአንድ አንበሳ ለማምለጥ መሮጥ እንደጀመረ በመሃል ደከመውና በርከክ ብሎ፦
“እንደው አምላክ የምትባል ካለህ፡ አምላክነትህን አሁን አሳየኝና ይህን የሚከተለኝን አንበሳ ክርስቲያን አድርግልኝ!” ብሎ ጸለየ።
አንበሳውም ወደ ሰውዬው ጠጋ አለና፦
“አቤቱ እኔን የፈጠርክ ቸሩ እግዚአብሔር ሆይ፡ የዕለት እንጀራዬን ስለሰጠኽኝ ምስጋና ይገባሃል፤ አሁን የቀረበልኝን ማዕድ ባርክልኝ፤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ!” አለና ከሃዲውን እያጣጣማ በላው።