Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2018
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for July 2nd, 2018

በአተ ክረምት | ኑ! ወደ ድንቁ አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም አብረን እንውጣ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 2, 2018

ሰማዩን በደመና ይሸፍናል ለምድርም ዝናምን ያዘጋጃል ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም[መዝ ፻፵፮፡፰]

እያልን ከሚገርሙት ወፎች ጋር በአንድ ላይ እንዘምር

ዘመነ ክረምት (ከሰኔ ፳፮ – መስከረም ፳፭ )

እንደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ያለው ወቅት ዘመነ ክረምት ይባላል፡፡ ክረምት የሚለው ሥርወ ቃል ከርመ ከረመ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ወርኀ ዝናም ወርኀ ነጎድጓድ ዘመነ ባሕር ዘመነ አፍላግ ዘመነ ጠል ዘመነ ደመና ዘመነ መብረቅ ማለት ነው ዘመነ ክረምት የዝናም የዘር የአረም ወቅት በመሆኑ ምድር በጠለ ዝናብ ትረካለች ዕፅዋት አዝዕርትና አትክልት በቅለው ለምልመው የሚያድጉበት ምድር አረንጓዴ ለብሳ በሥነ ጽጌያት የምታሸበርቅበት ወቅት ነው

በመሆኑም በሀገራችን ብዙው የግብርና ሥራ የሚካሔደው በእነዚህ ጊዜያት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዜማ ሊቃውንት እነዚህን ሦስቱን የክረምት ወራት በሰባት ንዑሳን ክፍሎች በመክፈል ለወቅቱና ለዕለታቱ የሚስማማ ምንባብ መዝሙር በማዘጋጀት ከምዕመኑ ሕይወት ጋር በማዛመድ ወንጌልን ያስተምራሉ። እነዚህም፡

1. በአተ ክረምት (የክረምት መግቢያ)

2. ምልአተ ባሕር

3. ዐይነ ኩሉ ዕጓለ ቋዓት ደሰያት

4. ጉህ ጽባህ

5. ዘመነ ዮሐንስ

6. ዘመነ ፍሬ እና

7. ዘመነ መስቀል ናቸው፡፡

በአተ ክረምት (የክረምት መግቢያ)

በአተ ክረምት የሚባለው ከሰኔ ፳፭ እስከ ሐምሌ ፲፱ ቀን ድረስ ያሉት ፳፫ ዕለታት የሚጠሩበት ነው ፡፡ በዚህ ጊዜ ዝናምና ደመና ምድርን የሚያለመልሙበት ዘር የሚዘራበት የተዘራው የሚበቅልበት በፀሐይ ሐሩር የደረቁ ዛፎች ሁሉ የሚያቆጠቁጡበት ወቅት ነው።

በዚህ የመግቢያ / የዝግጅት ወቅት / በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዘርን ደመናን ዝናምን የሚያዘክሩ ምንባባት ይነበባሉ። መዝሙራት ይዘመራሉ፤

‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን ይጸግቡ ርኁባን ›› የዝናብ ድምጽ ተሰማ ዝናብም በዘነበ ጊዜ ችግረኞች ይደሰታሉ ረሃብተኞች ይጠግባሉ›› / ድጓ / የሚሉና፡

ከመዝሙረ ዳዊት ደግሞ

‹‹ሰማዩን በደመና ይሸፍናል ለምድርም ዝናምን ያዘጋጃል ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም›› [መዝ ፻፵፮፡፰]

ከወንጌል ደግሞ

‹‹በእርሷ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት ለሚያርሷትም የምትጠቅም አትክልት የምታበቅል ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለች እሾህንና ኩርንችትን ግን ብታወጣ የተጣለች ናት ›› [ዕብ ፮፡፯] የሚል ነው።

ይቆየን!!!

ምንጭ፡ሐመር መጽሔት

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: