የሳውዲ አረቢያ ቴሌቪዥን አስተናጋጇ ሸሪን አል–ራፊዬ ቪዲዮው ላይ እንደምትታየው ጸጉሯን ሙሉ በሙሉ ባለመሸፈኗ እስራትነና የ100 ጂራፍ ግርፋትን ለማምለጥ ስትል ሳውዲ ለቃ ወጥታለች። ትገደል! የሚሉ ጥሪዎች በማሕበራዊ ትስስር ድህረ ገጾች ከተሰሙ በኋላ ለህይወቷ በመስጋቷ ነው ከሳውዲ ለማምለጥ የወሰነችው።
በሱኒ ሳውዲ ቀንደኛ ጠላት በሺያ ኢራን ደግሞ ወጣቱ በማመጽ ላይ ነው። “ሞት ለአያቶላ ካሜኔይ! ሞት ለፍልስጤም!” በማለት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣት ኢራናውያን መንገድ ላይ እየወጡ ነው።
ስለእነዚህ ሁኔታዎች ዋናዎች የሚባሉት ሜዲያዎች ጸጥ ብለዋል፤ ስውዲም ኢራንም፤ ሁለቱም የፀረ–ክርስቶስ አገራት የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። በእነዚህ ትዕቢተኞች፣ ግትር እብሪትኞች ላይ እየመጣባቸው ያለው መቅሰፍት ገና ብዙ ደም ያስለቅሳቸዋል።
በነገራችን ላይ በዛሬዋ ኢራን ወይም በቀድሞዋ ኃያሏ ፋርስ ላይ የእስልምና መቅሰፍት የመጣባት በ፮ኛው መቶ መጨረሻ ላይ በየመን የነበሩትን ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ጨፍጭፋ በመግደል የመንን ግዛቷ ባደረገቻት ማግስት ነበር። ይህ ብዙ የማይነገርለት ታላቅ የታሪክ ማስረጃ ነው!
ስለዚህ አስገራሚ ታሪክ ለአንዲት ክርስትናን ለተቀበለች ኢራናዊት አንድ ጊዜ ሳወሳላት፡ የተደሰተችው ደስታ አይረሳኝም፤ የክርስቶስን ብርኃን ስላየች ሁሉም ነገር ተገጣጠመላትና ነው።
እኛ ኢትዮጵያውያን እጆቻችንን ወደ እግዚአብሔር በመዘርጋት የአምላካችንን ድንቅ ሥራ እንታዘባለን።
ኡራኤል – ጊዮርጊስ – ተክለ ሐይማኖት
______