Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2018
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 24th, 2018

እኅተ ማርያም | የእግዚአብሔርን ቃል ደግፉ ፤ መንግስት ብቻ አይደለም ለአገራችን ውድቀት ተጠያቂው፡ ሕዝብም እንጂ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 24, 2018

የእመቤታችን አሥራት አገር ኢትዮጵያ፡ መሠረቷ ክርስቶስ ነው!

ወገኖች መንግስቱን ዘረኛ ነው እያሉ፡ “ነፃነት ባለበት” ውጭ አገር እንኳን ሳይቀር በጎሣ ተከፋፍለዋል። አይገርምም! ከተዋሕዶ ትግሬ መሪ ሙስሊም ኦሮሞ መሪ የተመረጠበት ግዜ ላይ ደርሰናል፤ ሆይሆይ የሚለውን ሰው ብዛት ስናይ፡ ለስላሳው ፀረክርስቶስ ጨረቃዋን መጎተት ሲጀምር ምን ያህል ተከታይ እንደሚኖረው መገመት አያዳግተንም። የሚፈለገው ይህ ነው፤ አላማውም ያ ነው።

ሰው በኢትዮጵያ መሠረት ላይ (ትግራይ ነው የሚገኘው) ጥላቻ እንዲኖረው በማድረግ መሬት መንቀጥቀጥ መፍጠር መቻል፡ ነው አላማው። በዚህም መልክ በተዋሕዶ ሃይማኖት አማኙ ህዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር ሙከራ ተደርጓል። ላለፉት ሺህ ዓመታት ጦርነቱ፣ ረሃቡና በሽታው ሁሉ ይከሰት የነበረው በወሎ ላሊበላ አካባቢ እና በትግራይ ነው። በዱሮ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎችን (ራያ) ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አምጥተው አስፈሩ፤ በኋላ ላይ ደግሞ የደርግ መንግስት ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖችን ከትግራይ በማፈናቀል በደቡቡ ኢትዮጵያ ለማስፈርና ትግራይን ከተዋሕዶ ለማጽዳት ሞክሯል። Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ሄገል።

ልክ በአይሁዶች በኩል የእስራኤልን መሠረት ለመነቅነቅ እንደሚሞክሩት፡ አሁን በአገራችንም በትግሬዎች በኩል የኢትዮጵያን መሠረት ነቅንቀው ለማፍረስ እየታገሉ ነው። ይህ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: