በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ ቦታ በቤተልሔም የልደት ቤ/ክርስቲያንን ለመጎብኘት የመጡትን ሴት ክርስቲያኖች ከሙስሊሞች ለመከላከል ወደ ገዳማቸው አስገብተው በሩን ሲዘጉባቸው ነበር አባ ፋዲ ሻሉፋ በቢላ የተወጉት። ቢደሙም፡ አወጋጉ በጣም የከፋ ባለመሆኑ አገልግሎታቸውን ወዲያው ለመቀጠል በቅተዋል።
ክርስቶስ በተወለደባት ቤተልሔም ክርስቲያኖች ቀስበቀስ እያለቁ ነው።
[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲፡ ፲፩]
“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶች፡ ጦርነት ላይ ነን!