የረመዳን ጋኔን | በ አርባ ምንጭ ሀይቅ አጥማቂው ጴንጤ ፓስተር በአዞ ተገደሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2018
አስቃቂ ነው፤ ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በተባለ ስፍራ ከሀይቅ ዳር ቆመው መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ ፓስተር በአዞ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው ፖሊስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ፓስተር ዶጮ እሸቴ የተባሉት የሃይማኖት አባት እሁድ ጠዋት 2 ሠዓት ተኩል አካባቢ ቁጥራቸው በግምት ሰማኒያ አካባቢ የሆኑ ተከታዮቻቸውን በሃይቁ ውሃ እያጠመቁ በነበረበት ሰዓት አደጋው እንደደረሰባቸው አቶ ከተማ ካይሮ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አቶ ከተማ ስለ ክስተቱ ሲያስረዱ ”አጥማቂው የመጀመሪያውን ሰው አጥምቀው ሁለተኛውን ማጥመቅ ሲጀምሩ አዞው በድንገት በመውጣት የሚጠመቀውን ሰው ገፍትሮ ሲጥለው አጥማቂውን ግን ጎትቶ ወደ ውሃው ይዞት ሄዷል” ብለዋል።
የወረዳው ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን እውነቱ ካንኮ በበኩላቸው ክስቱት መፈጠሩን አረጋግጠው፤ በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ዓሳ አስጋሪዎችና ወጣቶች በአዞው ጥቃት የተፈፀመባቸውን ግለሰብ ከአዞው ለማስጣል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ ተናግረዋል።
ዋና ሳጅን እውነቱ ምንም እንኳን የፓስተሩን ህይወት ማዳን ባይቻልም የአካባቢው ማህበረሰብ የሟች አስከሬን ከአዞው ለማስጠል እንደተቻለ ጨምረው አስረድተዋል።
የሟቹ ፓስተር ዶጮ እሸቴ የቀብር ሥነ–ሥርዓትም ሰኞ እለት ተፈፅሟል።
Leave a Reply