Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2018
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 28th, 2018

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ | እንግሊዝ እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ መብረቅ ወረደባት፤ የኢትዮጵያ ቀለማት ታዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2018

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”

እጅግ በጣም የሚገርም ነው፤ አመጸኞቹ አውሮፓውያን የዔሳውና የእስማኤል ዘሮች የእግዚአብሔርን አሠርቱ ት ዕዛዛት ሙሉ በሙሉ በማፍረስ የራሳቸው የሆነ ዓለም በመፍጠር ከራሳቸው አልፈው እኛንም በጽኑ በመጉዳት ላይ ናቸው። ግን ፈጣሪያችን ትዕግሥቱ እያለቀበት ነው፤ ምልክቶቹን ለመጨረሻ ጊዜ እያሳየን ነው።

በአገራችን ላይ እያውጠነጠኑት ያለውን ዲያብሎሳዊ ሤራ ብዙዎቻችን አሁንም አልተረዳነውም፤ ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር ግን ዝም አይለም። ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች።

ቅዳሜ ሌሊት ላይ፡ በእንግሊዝ አገር ታይቶ የማይታወቅ ነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭልጭታ ብዙዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሷል። በአንድ ምሽት ብቻ 22 ሺህ ጊዜ የለንደን ሰማይ በመብረቅ ተብለጭልጯል።

ቪዲዮው መጨረሻ ላይ እንደሚታየውም በሆነ ወቅት ላይ ደመናው በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ተቀብቶ ነበር። የሚገርም ነው።

ይህ ሁሉ የተከሰተው፤ እንግሊዝ ፀረእስላም የሆኑ ጋዜጠኞችን ማሠር በጀመረችበት፣ ወኪሏን አቶ አንዳርጋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈታ ትዕዛዝ ካሰተላለፈች፣ እንዲሁም እህቷ አየርላንድ ደግሞ የጸነሱ ሴቶቿ ጨቅላዎቻቸውን እንዲያስወርዱና እንዲገድሉ በሬፈረንደም አጽድቃ ፈቃዱን በሰጠቻቸው ማግስት መሆኑ ነው።

ጻድቁ አባታችን፡ አቡነ ተክለሃይማኖት በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉ ብለው ነበር።

እነሱም፡

1. መብረቅ

2. ቸነፈር፣

3. ረሃብ፣

4. ወረርሽኝ፣

5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: