666
[ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፮፥፮]
በቅዳሜው የኪየቭ ቻምፒየንስ ሊግ መጨረሻ ጨዋታ ላይ የ Liverpool እግር ኳስ ቡደን መርሆ፡ “ Reds, Bring Home Number Six!„ „ቀዮች፤ ቁጥር ስድስትን (6) ይዛችሁ ኑ!„ የሚል ነበር።
ግን አልተሳካላቸውም፤ ለአላህ ለሰው ይታይ ዘንድ የጸለየው ግብዙ ግብጻዊ “ሞ ሳላህ” ወይም መሀመድ ሳላህ (ሞ ፋራህ ን እናስታውሳለን?) መሰናክል ሆናቸው።
ሞ ሳላህ በማን እጅ ወደቀ? በማድሪዱ ሰርጂዮ ራሞስ እጅ። ሰርጂዮ ራሞስ ለ600 ዓመታት ያህል አረብ ሙስሊሞችን ታግላ እስልምናን ሙሉ በሙሉ ካጠፋችው ከአንዳሉሲያ ስፔይን ክፍለሃገር የተገኘ ስፖርተኛ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል ቁጥሩም፤ 6:6፤ ይጠቁመናል፦
“አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።“
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፮፥፭፡፯}
ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።