መታየት ያለበት | ከኢየሱስ ክርስቶስ የመጣልንን መንፈስ ቅዱስ ያገኘንበት የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ይህ ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 26, 2018
ይህ የሚመስጥና የሚያስለቅስ ታሪክ ነው።
ክርስትና እዚህ ቦታ ላይ ነው የተወለደው! በ ጰራቅሊጦስ ወይም ጰንጠቆስጤ ዕለት ከኢየሱስ ክርስቶስ የመጣልንን መንፈስ ቅዱስ ያገኘነው እዚህ ቦታ ላይ ነው።
በዓለም በጣም አስፈላጊ/ ተፈላጊ ከሆኑት ቦታዎች መካከል አንዱ ይህ ነው።
በዓለም የመጀመሪያው የቤ/ ክርስቲያን ህንፃ በጽዮን ተራራ ድብቅ በሆነ ቦታ መሬት ሥር ውስጥ ተቀብሮ ነው የሚገኘው።
በእየሩሳሌም የሚገኘው ይህ እጅግ በጣም ታሪካዊ ቦታ በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ቁጥጥር ሥር ነው።
በዚህ ቅዱስ ቦታ፡ ልክ በኢየሱስ ዘመን እንደነበረው አሁንም በተከታዮቹ ላይ በደል ሲደርስባቸው
ማየቱ በጣም የሚያስገርም ነገር ነው።
ከ ሮማውያን ወታደሮች ለማምለጥ መሬት ውስጥ ተደብቀው ነበር ጸሎት ሲያደርጉ የነበረው። (ልክ እንደ ላሊበላ ዓብያተክርስቲያናት)
ቅ/ ያዕቆብ የመጀመሪያዋ የዚህች ቤ/ክርስቲያን ሐዋርያ ነበር።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደዚህ ቤተክርስቲያን ትመጣ ነበር።
ኢየሱስ የ ያዕቆብ ወንድም ነበር። ያዕቆብ የኢየሱስን ትንሣኤ ካየ በኋላ አመነ፡ ከዚያም የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ሐዋርያ ለመሆን በቃ።
የመጀማሪያዎቹ ክርስቲያኖች በ44 ዓ.ም አካባቢ ለሮማውያኑ ህገ ወጥ ነበሩ፡ ስለዚህ ያሳድዷቸውና ይበድሏቸው ነበር። ለዚህም ነበር በመሬት ውስጥ ተደብቆ እንዲሠራ የተደረገው።
በዚህም ዘመን ቢሆን ቤተክርስቲያኑ ታሥሯል፤ ልክ በኢየሩሳሌም እንዳለው፡ ወይም በአገራችንም እንዳሉት ገዳማትና ቅዱሳን ቦታዎቻችን፡ ይህም ቤተክርስቲያን አሁንም ድረስ ፈተናዎች ይበዙበታል። የቤተክርስቲያኑን በር ለመክፈት እንኳን ልዩ ፈቃድ ያስፈልጋል፤ ለጎብኚዎች ዝግ ነው፣ ማደስና መጠገንም አይፈቀድም። እንዲያውም ጽንፈኛ የሃይማኖት አክራሪዎች ወደዚያ እየሄዱ፡ በመስክቶት በኩል፡ ውስጥ ድረስ ቆሻሻ ይደፉበታል። ፀረ–ክርስቶሱ ነው ኢየሩሳሌምንም የሚቆጣጠራትና።
ልክ በኢየሱስ ዘመን እንደነበረው አሁንም በተከታዮቹ ላይ በደል ሲደርስባቸው ማየቱ በጣም የሚገርም ነገር ነው።
በእውነትም፡ ይህ የሚያነቃቃና የሚመስጥ ድንቅ ቦታ ነው።
ይህ የመጀመሪያው ቤ/ ክርስቲያን የመጨረሻው ቤ/ ክርስቲያን ይሆንን?
የእግዚአብሔር መንፈስ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ይገልጣል
‹ጰራቅሊጦስ› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ፦
- ናዛዚ (የሚናዝዝ)
- መጽንዒ (የሚያጸና)
- መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል፡፡
በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል (ሐዋ.፪፥፩–፵፩)፡፡
አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ተገዢነት እና ከሲኦል ባርነት ያወጣው ቸሩ መድኃኔ ዓለም የወደቁትን ወገኖቻችን ያንሳቸው፣ ጰራቅሊጦስንም ያውርድላቸው።
እንኳን አደረሰን!
Leave a Reply