በአንድ የበርሊን ከተማ የ KFC ፈጣን ምግብ ቤት ውስጥ የ 118 ዩሮ ምግብ እየበሉ እንዳሉ ነበር የሬስቶራንቱ ሠራተኞች ፖሊስ ጠርተው እንዲባረሩ የተደረጉት።
ከእንግሊዝ አገር የመጡት ሦስቱ ጥቁር ሴቶችና አራቱ ጥቁር ወንዶች ምግቡን በልተው በበርሊን ከተማ በዓል ላይ ያነሷቸውን ቪዲዮዎች እያዩ ሲሳሳቁ ነበር። ሌሎችም እንግዶች እንዲሁ ተመሳሳይ ጨዋታዎችና መሳሳቆችን ሲለዋወጡ ይሰማ ነበር። ነገር ግን የKFC ሠራተኞች ወደ ጥቁሮቹ ብቻ መጥተው ነበር ጸጥ እንዲሉ ያሳሰቧቸው። ይህ ያስቆጣው አንዱ ጥቁር፦ “ምን አጠፋን? እንደ ሌሎቹ እኛም እየተጫወትን ነው፤ ለምን እኛን ብቻ?” ብሎ ሲጠይቅ፤ ወዲያው ፖሊስ እንዲጠራ ተደረገ።
ቀሪው ከቡድኑ ጋር አብራ በነበረችው ሴት የተነሳው ቪዲዮ ላይ ተመዝግቧል።
ይህም ሐሙስ ግንቦት 18 እና 21 2018 ዓ.ም በጥቁሮቹ ላይ የደረሰው ድርጊት ዘረኝነት የተሞላበት ነው በማለት ግለሰቦቹ ሬስቶራንቱንና ፖሊስን ወንጅለዋቸዋል።
አሁን በማሕበራዊ ድህረገጾች የዘረኝነት ክሶች እና የፀረ-KFC ዘመቻ ጥሪዎች እየጨመሩ ነው። በጥቂት ቀናት ብቻ ቪዲዮው ግማሽ ሚሊየን ጊዜ ቋ! ተደርጎል
ይህ ጉዳይ ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ላይ በአሜሪካዋ ፊላደልፊያ ውስጥ፡ በአንድ የስታርባክስ ቡና ቤት የተከሰተውን ክስተት የሚያስታውስ ነው። እዚያም ሁለት ጥቁር አሜሪካዊያን ነጋዴዎች ቡና ቤት ውስጥ ባልደረባቸውን በመጠበቅ ላይ እያሉ አንድ የቡናቤቱ ሠራተኛ ፖሊስ በመደወል ከቡና ቤቱ በሰንሰለት ታሥረው እንዲወጡ ተደርገው ነበር። ይህ ክስተት በአሜሪካ ውስጥ ዘረኝነትን አስመልክቶ ብዙ ክርክር አስነስቶ ነበር።
ከዚያ በኋላ የስታርባክስ ኃላፊ የፀረ–ዘረኝነት ስልጠናን ለሰራተኞቹ ለማጠናከር ሲል 8,000 ቅርንጫፎችን ለአንድ ቀን በመዝጋት “የሙያ ስልጥና” አካሄዶ ነበር። ዋና ሥራ አስኪያጅ ኬቪን ጆንሰን ግለሰቦቹን ይቅርታ ተጠይቋል። ሠራተኞቹ ፖሊስ መጥራታቸው “ሙሉ ለሙሉ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው” በማለት ምላሽ ሰጥቶ ነበር።
ስለዚህ ጉዳይ ብዛት ያላቸው የጀርመን ሜዲያዎች ሪፖርት አቅርበዋል። ለምሳሌ አንጋፋው “ዲ ቬልት” ጋዜጣ ላይ በጣም ብዙ አንባብያን ዘግበዋል፤ (እስከ 400 የሚሁን ዘጋቢዎች)፤ ታዲያ ከድርጊቱ ይበልጥ በጣም የሚያሳዝነው፤ ሁሉም፤ (100%) የወነጀሉት ጥቁሮቹን መሆኑ ነው፤ አንድ እንኳን “አላየሁም፣ አላውቅም፣ በቦታው አልነበርኩም” በማለት ሚዛናዊ አመለካከት የነበረው የለም። በብዛት “ላይክ” የተደረገላቸውም ጥቁር የሚሏቸው ሕዝቦችን የሚኮንኑት ዘገባዎች ናቸው። “ነጮች የጥቁር ሰዎችን ችግር ለመረዳት አይፈልጉም” ወይም “ስሜታዊ ዓልባ ናቸው” “Empathy የላቸውም“ የሚለው ነገር፡ ምናልባት እውነት ሊሆን ይችላል። ምን ዓይነት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ይገርማል!
— When Did Fried Chicken Become a Symbol of Racism?
______
Like this:
Like Loading...