ቻይኖች ይህን የያዝነውን አዲስ አመታቸውን፡ “የውሻ አመት” ብለውታል።
የውሻ መንጃ ፈቃድ የሚወጣበት ዘመን እየመጣ ይሆን?
በምስራቅ ጀርመኗ ማግደበርግ ከተማ አንድ የሶሪያው ተወላጅ ፓርክ ውስጥ ከሚስቱና ልጆቹ ጋር ሲዘዋወር ነበር በውሻ የተነከሰው። የውሻው ባለቤት ተፈርዶበት ታሥሯል።
ቪዲዮውን ያነሱት የሶሪያው ቤተሰቦች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች እንደጠቆሙት ከሆነ ሙስሊሞች ውሾችን ስለሚጠሉ ሶሪያውም እንዲሁ የውሻውን ባለቤት ሆን ብሎ ሳይተናኮለው አልቀረም።
ለማነፃፀር፦
እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደተገለጸው፤ “ኢትዮጵያዊት” የተባለችውን ልጃገረድ የነከሳት ውሻ ከባለቤቶቹ ተነጠቀ እንጂ ባለቤቶቹ ክስ አልተመሠረተባቸውም፤ አልታሠሩምም። ክስተቱ ተመሳሳይ ነው፤ የህግ አስከባሪዎቹ ውሳኔ ግን የተለያየ ነው፤ የሚገርም ነው።
እዚህ ላይ ምን የሚታየን ነገር አለ?
ለማንኛውም፤ ሁለቱም ተነካሾች፤ “አቤት ሲሳይ!” ብለዋል።