Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2018
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 20th, 2018

ልብ ብለናል? | በእንግሊዙ ልዑላውያን ሠርግ ላይ “አቡነ ዘበሰማያት” ያደረሱት የግብጽ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2018

የ “የዓመቱ ሠርግ” ነው በተባለለትና የእንግሊዙ ልዑል ሃሪ ከ አሜሪካዊቷ ከሜጋን ሜርክል ጋር በ ዊንዘር ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባደርጉት የጋብቻ ስነሥርዓት ላይ የአቡነ ዘመሰማያት ጸሎት እንዲያደርሱ የተጋበዙት በግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የለንደን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ አንጌሎስ ነበሩ። ሙሽራዎቹን ጨምሮ ሁሉም ባንድ ላይ ፀሎት ያደረሱበት ብቸኛ ሥነስርዓት ነበር።

እኔ የምጠየቀው፦

1. እንግሊዛውያኑ ሠርገኞች የተጋቡት በ አንግሊካን ቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ነው።

2. ሙሽራዋ ከዚህ በፊት አግብታ የፈታች ናት።

ታዲያ እንዴት ነው አንድ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ” በዚህ መላው ዓለም ሁሉ በተከታተለው የሠርግ ሥነስርዓት ላይ፡ ጸሎት ለማድረስ የበቃው ወይም የተፈቀደለት? ኤፒስኮፓሎቹስ አንግሊካውያን ናቸው፤ ግን ካቶሊክን ጨምሮ ሌሎች ዓብያተክርስቲያናት ሳይጋበዙ፤ እንዴት የግብጽ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ተጋበዙ?

በጣም የሚገርም ነገር ነው!

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infotainment | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የረመዳን ጋኔን | በሩሲያ ቅዱስ ሚካኤል ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2018

አብዛኛዎቹ ነዋሪዎቿ ሙስሊሞች በሆኑባት የሩሲያ አውቶኖማዊ ሪፑብሊክ በቼችኒያ ዋና ከተማ ነበር ይህ ፀረክርስቲያናዊ ጥቃት ትናንትና የተሠነዘረው። በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ በምሽት አገልግሎት ወቅት 15 ክርስቲያኖች ጸሎት እያደረሱ ነበር። 4ቱ ሽብር ፈጣሪዎቹ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገና ሳይገቡ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቤተክርስቲያን ውጭ ተገድለዋል። ሁለት ፖሊሶች እና አንድ ክርስቲያን በተጨማሪ ሞተዋል።

ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድ የሚገርም ነገር አለ፦

ይኽውም በብዙ የሩሲያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ህንፃ ላይ መስቀሉ፡ ከስሩ ያለውን ግማሽ ጨረቃ እንዲወጋው ተደርጎ ይሠራል፤ ክቡር መስቀሉ በእስላም ግማሽ ጨረቃ ላይ ተቸክሎ ይታያል።

ይሀም፦ ክርስትና እስልምናን ድል ያደርገዋል ማለት ነው

______

 

Posted in Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: