Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2018
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 16th, 2018

መታየት ያለበት | ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገባት ቤተ መቅደስ በፀረ-ክርስቶሱ ቁጥጥር ሥር ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2018

ለጉብኝት ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄዱትን ክርስቲያኖች፡ ገንዘብ ካልከፈላችሁ ቤተ መቅደሱን ማየት አትችሉም፡ በማለት፡ ሙስሊሞች በድፍረት እየሠሩ ያሉት ወንጀል በጣም አሳዛኝ ነው። አቤት ጥላቻ! አቤት ትዕቢት! አቤት ጥጋብ! አቤት መጨማለቅ!

በአገራችንም፡ አንዳንድ ዓብያተክርስቲያናት አካባቢ፡ የነርሱን ያህል ባይሆንም፡ ተመሳሳይ ክስተት ይታያል። አብሮ ከመኖር የተነሳ ብዙ መወረስ የሌለባቸው ባሕርይዎች ይወረሳሉ፡ ይህንም ከፀረክርስቶሳውያኑ መሀመዳውያን የወረሱት መሆን አለብት።

[ዮሐ. 214-17]

በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም፡የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ

እንኳን ለጌታችን የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን!


                                                                        ዘመነ ዕርገት                                           ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲ .


ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡

በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ቀን ፳፻፲ .ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡

በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡ ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡

በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡

ምንጭ

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የ ኮፕት ወንደሞቻችን ቀብር | ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2018

በትናንትናው ዕለት ኮፕት ክርስቲያኖች፡ ከእንባ እና ደስታ ጋር፡ ለዎቹ ኮፕት ሰማዕታት አካላት ዕረፍትጧቸው።

የታረደውን አባቱን ፎቶ የሚነካው ክርስቲያን ህፃን ልጅ በጣም ያስለቅሳል።

የዲያብሎስ ልጆች ሞራላችንን ለመስበርና እኛን ክርስቲያኖችን ለማዋረድ ሞክረዋል፤ አልተሳካላቸውም፤ የመዋረጃቸውና ደም የማልቀሻቸው ጊዜ ተቃርቧል፡ ወዮላቸው!

የነገውን የ”ዕርገት ዕለት” ለሰይጣን ረመዳን መጀመሪያ ዕለት ማድረጋቸውም ብዙ ነገር ነው የሚጠቁመን።


Tears And Joy As Egyptian Christians Killed In Libya Laid To Rest


Tears mixed with joy on Tuesday as the remains of 20 Christians were laid to rest in Egypt’s Minya province more than three years after they were kidnapped and beheaded in Libya in an attack that provoked rare Egyptian air strikes.

The return of the bodies of 20 Egyptian Copts has brought families in rural Egypt a chance for some closure after years in mourning with little hope of having the bodies of their loved ones being recovered for burial.

“Everyone stood beside the martyr that belongs to him and cried a little, but they were tears of longing, nothing more,” said Bishri Ibrahim, father of Kerolos, one of the victims, at the funeral service at a church in the village of al-Our in Minya province, where they were all laid to rest.

“But we are happy and joyful that they have returned to the village. This is a blessing for the country and to all Copts all over the world,” he added.

Thirteen of the 21 Libya victims came from al-Our, a rural town of around 10,000 people south of Cairo.

President Abdel Fatah al-Sisi ordered the Church, named The Church of the Martyrs of Faith and Homeland, to be built soon after the incident and dedicated in their memory.

Sisi also ordered a wave of air strikes on the Islamic State’s militant bases in Libya.

The remains of the victims, who were flown from Libya about a private jet to Cairo on Monday night, were placed inside cylinder-shaped containers covered in velvet cloth with the names of each victim and interred under the church altar.

Families said the burial place would be opened as a shrine for visitors.

The victims had been among the many poor Egyptians who risked their lives to find work in the lawless chaos of Libya following the downfall of Muammar Gaddafi in 2011 and civil war.

A video posted by Islamic State in January 2015 showed 21 people — 20 Egyptian Copts and one Ghanaian Christian — lined up on a Libyan beach in orange jumpsuits before they were executed.

“I wanted to see Milad come back from Libya on his feet after his struggle and hard work to earn a living in a harsh life abroad,” 55-year-old Zaki Hanna, the father of one of the victims.

“But thanks be to God, he died a hero, did not beg anyone to spare his life and he and his brothers, the martyrs, did not abandon their faith or homeland.”

Bashir Estephanos, whose two younger brothers were killed by Islamic State in Libya, said all Christians in al-Our village had been praying for the past three years for the bodies of the “martyrs” to be found.

Libyan authorities recovered the bodies in October after the area where they were buried was recaptured from the militant Islamist group.

“Our prayers were answered, so thanks be to God from the bottom of our hearts,” he said, speaking before the bodies arrived in the village.

The head of the Coptic Church in Egypt, Pope Tawadros II, was at the airport to receive the remains when they arrived in Cairo on Monday night.

Source

______

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: