ትክክል ናት እህታችን፡ እያየነው እኮ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ እኔ በግሌ ያየኋቸው ወይም የታዘብኳቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። የዶክትሬት ቆብ ማድረግና ከረባት ማሰር ሁሌ ይከነክነኛል። የ ዶ/ር ማዕረግ ከአውሬው ምልክቶች አንዱ ነው፤ በክርስቲያናዊው የመንፈሳዊ ሕይወታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀን የክርስትና ስም፡ ብሎም ቅብዓ–ቅዱሱን ተቀብተን የሊቅነቱ ማዕረግ እንደሚሰጠን፡ በፀረ–ክርስቶሱ ዓለምም እንዲሁ ዶክትሬቱን ለመቀበል የአውሬውን ቅባት “በመቀባት” እርሱ የፈጠረውን ሥርዓት ለማገልገል ቃል በመግባት ነው፤ ነፍስን በመሸጥ። በተለይ በውጭ አገራት ዶክትሬቱን የተቀበሉ ወገኖች ማዕረጉን ከተቀበሉ በኋላ ለለገሰቻቸው አገር እድሜ ልካቸውን ጠበቃ መቆም ወይም የአገሪቷን ፍላጎቶች የማሟላት ግዴታ አለባቸው። ባጠቃላይ፡ የባዕዳን መጠቀሚያ በመሆን ከሀገራቸው ጥቅሞች በተጻራሪ ይቆማሉ።
ለምሳሌ፡ በእምነት በኩል ፕሮቴስታንቶች ለ አሜሪካና አውሮፓ፣ ካቶሊኮች ለጣልያን፣ ሙስሊሞች ለሳዑዲ አረቢያ ሲሉ ከማንነታቸውና ከገዛ ሀገራቸው ጥቅም በተጻራሪ እንዲንቀሳቀሱ ሲደረጉ፤ በዶክትሬት የተካኑትም ወገኖች፡ ምዕራባውያኑ “ዲሞክራሲ” “ኒዖ ሊበራሊዝም፣ ወይም “ሊበራል ዲሞክራሲ” ለሚሉት የማታለያ ርዕዮተ ዓለም እንዲታገሉ ይገደዳሉ።
በጥቂቱም ቢሆን ቢዲዮው ላይ፡ ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ እና ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው ለዚህ ኃይለኛ መልዕክት እንደ ምስክር ሆነው ቀርበዋል።
ሁሉም ከተቀበረባቸው የዶክትሬት መርዝ እንዲፀዱ እግዚአብሔር ይርዳቸው፡ ይርዳን።