Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2018
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 8th, 2018

ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 8, 2018

ይህን ውብ ቤ/ ክርስቲያን የሠራችለትም ( ፲፱፻፲፮ ዓ./ 1916) ኢትዮጵያ ናት።

እንኳን አደረሰን!!!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ላይ ካሰማራቸው ሐዋርያት መካከል ሐዋርያው ማርቆስ አንዱ ነው

ከአማረ አፈለ ብሻው

ሐዋርያው ማርቆስን በሚመለከት መሪራስ አማን በላይ “ሐዋርያው ማርቆስ ዜግነቱ ሮማያዊ ሲሆን፡ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ነው። በዚያን ጊዜ ግብጾች ቦታ አልነበራቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ሐዋርያው ማርቆስ ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ነዋሪነታቸው ግብጽና ኢየሩሳሌም እንደነበረ በታሪክ ተጠቅሷል።

አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ፡ ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው ሲሉ መጽሐፍ ጽፈዋል። ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ አንበሳ ነው የተባለው መጽሐፍ ገጽ 100 ላይ “ማርቆስ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ጽፈዋል። እኒህ አባት ሐዋርያው ማርቆስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሐዋርያት ኢትዮጵያዊ ደም ያላቸው መሆናቸውን በማመለከት ከፍ ተብሎ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 42 ላይ፡ “ከኢትዮጵያውያን ዘር የሚወለደው ፊልጶስም ነው” ሲሉ ሁለቱ ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ያደረጉትን የቃላት ልውውጥ በሚመለከት ጽፈዋል።

ከዚህ ላይ ማየት ያለብን እነዚህ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቀድሞ ጀምረው ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉና ለክብር የማይሮጡ በመሆናቸው ማንነታቸው ሊታወቅ አልቻለም። እንኳን ቀድሞ በቅርቡ የዳ/ዊ አጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የፃፉት አንዱ ደራሲ መጽሐፉን የዘመኑ የታሪክ ሊቃውንቶችን ጥቅስ ለመውሰድ ሲሉ “የማይታወቀው ደራሲ” እንደጻፈው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው። የጥንት ኢትዮጵያውያን “እወቁልን” የማይሉ በመሆናቸው ብዙ የታሪክ አባቶቻችን ስምና ታሪክ ተደብቆ ቀርቷል። በዚህ ባለንበት አገር አሉ ከሚባሉት ሊቆች መካከል ለአንዱ የሊቀ–ጠበብት ማዕረግ ዩኒቨርስቲው ሲሰጣቸው አስተዳዳሪው ለተሰብሳቢው እንግዳ እንዲህ ብለው ነበር፦

ኢትዮጵያውያን ይህን ሰርተናል የማይሉ በስራቸው እንጂ ለወረቀት የማይጓጉ በመሆናቸው ይህ ዶ/ር እገሌ እንደሌሎች ዶክተሮች ማመልከቻ ይዞ ወደ ጽሕፈት ቤቱ መጥቶ አስቸግሮኝ አያውቅም። የስራውን ጥራትና ብቃት ዩኒቨርስቲው በማየቱ የሌቀ–ጠበብት ማዕረግ ሰጥቶታል” ብለዋል።

ትቤ አክሱም ገጽ 67 “ቅዱስ ማርቆስም ያባቱን ሀገር አስቀድሞም ያውቀው ስለነበረ መጥቶ እንዳስተማረ” ሲሉ ጽፈዋል። ከዚህ ላይ የኢትዮጵያውያን ከቀድሞ ጀምሮ የመጣው ታሪክ የሚያመለክተው ለክርስትና ሃይማኖት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ነው። ሐዋርያው ማርቆስን የመሰለ መምሕር ያስገኘች ኢትዮጵያ ናት። ላይ እንደተጠቀሰው ዛሬ ድረስ በህይወት ያሉ ደራሲያን ኮሎኔልነታቸውን፣ ጠበብትነታቸውን ወይም ሊቅነታቸውን ሳይጠቅሱ መጽሐፍ የጻፉ ደራሲያን ነበሩ። ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን አብዛኛው እወቁኝ የማይሉ ናቸው። በዚህ ምክንያት ከቀድሞ ጀምሮ ተያይዞ በመምጣቱ ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ሳይታወቅ ኖሮ ነበር።

መሪራስ አማን በላይ፡ “ጉግሣ” መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 3 መጋቢት 1993 .. ገጽ 17 ላይ “የማርቆስን አክስት ማለት የበርናባስንና የአርስጦሎስን እህት ጴጥሮስን አግብቶ ነበር። እንዲሁሙ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የቤተ እስራኤል የሌዊና የይሑዳ ነገድ የሆነ ወደ ቀሬና ቀራኒዮ ወደ ቤተ መቅደስ ሊሰግድ መጥቶ ስሙም ስምዖን ይባል ነበር። በበነጋታው ከአባቱና ከናቱ ዘመድ ከስምዖን ጋር ማርቆስ የጌታችንን የክርስቶስን ግርፋትና ሕማማቱን እየተከተለ ተምልክቷል። አጎቱንም የአባቱን ዘመድ ኢትዮጵያዊ ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው የጌታን መስቀል እንዲሸከም አይሁዳ ሊያስገድዱት አይቷል ተመልክቷል” ሲሉ ጽፈዋል። ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥበት ምክንያት ስምዖን ጥቁር መሆኑን በሌሎችም ታሪክ ታውቋል።

ሐዋርያው ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ታሪኩን ስላወቁ ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ አጽሙ አጽሙ ቬነስ ግዛት / ከተማ ከሚቀር ግብጽ መግባት ይኖርበታል ብለው ከቬነስ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ጋር ያደረጉት ጥረት ቀላል አይደለም። ቀደም ሲል ግብጾች ሊያስመልሱ ያልቻሉትን አጤ ኃይለ ሥላሴ በጥረታቸው የቅዱስ ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ወደ አፍሪቃዋ ግብጽ እንዲገባ ሆነ። ይህ ታሪክ በመሆኑ ሊገለጽ የሚገባው ሲሆን፡ ጃንሆይ መሠረት ያደረጉት ዋናው ነጥብ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በዘሩ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው።

የአጤ ኃይለ ሥላሴ ታሪክ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 1132 ላይ “ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ወደ ግብጽ ገብቶ ክርስትናን በማስተማር ላይ እያለ የክርስቲያኖችን ዕምነት የሚጠሉና በጣዖት የሚያመልኩ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ለምደውት ለቆየው አምላካቸው በጣም ቀናኢ የሆኑ በአሌክሳንድርያ መንገድ ላይ እየጎተቱ አሰቃይተው ገደሉት። እንደሞተም አሌክሰንድርያ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ቀበሩት። በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 .ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ነጋድያን አጽሙን በድብቃ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥታት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም ለግብጽ እንዲመለስ ብዙ ጊዜ ጠይቀዋል።

ነገር ግን ሁሉም የሚፈጸመው እግዚአብሔር በፈቀደው ጊዜ ስለሆነ ጊዜው ሲደርስ የሮማው ርዕሠ ሌቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ በሞተ በ1900 በተወሰደ 1140 ዓመት ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ።” ካለ በኋላ አጽሙ የገባበትን ቀን ሲገልጹና ጃንሆይም በስፍራው መኖራቸውን ሲያብራሩ ገጽ 1133 ላይ፡ “የቅዱስ ማርቆስ አጽም ከቬነስ ወደ ግብጽ የገባው ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በአለበት ሰኔ 17 ቀን 1960 .ም ነው።” ብለዋል።

ሐዋርያው ማርቆስ አጽም ግብጻውያን ራሳቸው ካልሸጡት አልያም ጠቋሚ ካልሆኑ ቁጥራቸው ትንሽ በሆነ ነጋዴዎች ተሰርቆ ሊወሰድ አይችልም። መሠረቱን ካወቁ ጀምሮ አጽሙን ለማስመለስ ብዙ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም ነበር። በዚህ ምክንያት የሐዋርያው ማርቆስን አጽም ለማስመለስ የቻሉት ኢትዮጵያዊው ቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ ናቸው። ያም በመጀመሪያ ጌታ ሲወለድ የእጅ መንሻ የሰጡ ሰብዓ ሰገል ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ኋላም ጌታችን በስደት መጥቶ የኖረባት ስትሆን ተመልሶም መጥቶ ወንጌልን ያስተማረባት አገር ናት። ከዚያም በጅሮንድ ጃንደረባ ባኮስ34 .ም ተጠምቆ ተመልሶ ወንግጌልን ያስተማረባት ኢትዮጵያ አገራችን ናት።

በድጋሚ የቀረበ

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: