“ልጃገረዶች ለቤተሰቡ የገቢ ምንጭ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ስለሌለ መገደል ይኖርባቸዋል”
እንደ “ኤድሂ ፋውንዴሽን” ከሆነ በ 2017 ዓ.ም ብቻ በፓኪስታን የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታዎች ላይ 355 የሞቱ ሕፃናት ሬሳዎች ተግኝተዋል። አዲስ የተወለዱ ሕጻናት በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ከተማዋ.
ከ 300 በላይ አዲስ የተወለዱ ሕፃናት በየካቲት2017 ዓ.ም እና ሚያዝያ 2018 ዓ.ም መካከል በካራቺ ከተማ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቤቶች ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል።
በዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች መረጃ መሠረት በካራቺ አንዳንዶቹ ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ናቸው።
ከእነዚህ ጨቅላ ህፃናት ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው
አንዳንዶቹ ህፃናት በካራቺ በሚገኝ አንድ መስጊድ በር ላይ ተጥልው ከተገኙ በኋላ፡ ኢማሞች በድንጋይ ወቅጠው እንደገደሏቸው፡ ኢማሞቹ እራሳቸው መስክረዋል። ለዚህም የሰጡት ምክኒያት “እነዚህ ህገ–ወጥ የሆኑ ህፃናት በመሆናቸው በድንጋይ ተቀጥቅጠው መገደል ነበረባቸውና ነው።” “በእነዚህ ገዳይ ኢማሞች ላይ የፓኪስታን መንግስት እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ አይደለም” በማለት የፋውንዴሽኑ መሪ ብሶታቸውን ገልጠዋል።
እንደ ‘ጉትማከር ተቋም‘ በፓኪስታን 4.2 ሚልዮን የሚሆኑ ሴቶች ባልተጠበቀ እርግዝና ይጠመዳሉ። ውርጃ በጣም ውሱን የሆነ ሕጋዊነት ስላለው፡ ለወላጆች ልጃገረዶችን ከመውለድ ይልቅ ወንዶችን መውለዱን ይመርጣሉ፤ ስለዚህ በድንገትና “ህገ ወጥ” በሆነ መንገድ ከተወለዱ “ልጃገረዶች ለቤተሰቡ የገቢ ምንጭ የማያበረክቱት አስተዋጽኦ ስለሌለ መገደል ይኖርባቸዋል”።
ምንጭ፦ DailyMail