Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2018
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    30  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ታላቅ የእጅ ጽሑፍ ግኝት | በ፰ኛው መቶ ክፍለዘመን መሀመዳውያኑ የኮፕቶችን መጽሐፍ ቅዱስ ደልዘው ቁርአንን ጽፈውበታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2018

ፈረንሳዊው ምሁር ዶክተር ኤሎነር ዋልድ ይህን ግኝት አሁን በይፋ አሳውቀዋል። ይህ በብራና ላይ የተጻፈ ዘጠኝ የእጅ ጽሑፍ ቁርጥራጮች ስብስብ በትናንትናው ዕለት በለንደን የጨረታ ሽያጭ ማዕከል በሆነው  ክሪስቲበጨረታ ቀርቦ ነበር

ዝርዝሩ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በስምንተኛው፡ መቶ ክፍለ ዘመን በክርስቲያኖች ጽሑፍ ላይ ተደለዞ የተጻፈበት የቁርአን ቅጂዎች ቁርጥራጮችንም ያካተተ ነው።

በግብፅ የኮፕቲክ ማኅበረሰብ በስምንተኛው ክፍለ ዘመን ላይ አርብ ሙስሊሞች በተወረሩ ጊዜ ክርስቲያናዊ መጻሕፍታቸውን ሁሉ ተነጥቀው ነበር።

በዚህ የእጅ ጽሑፍ በኮፕትኛ ቋንቋ ተጽፎ የነበረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፍ ተደልዞ በላዩ ላይ የቁርአንን ጽሁፍ በአረብኛ አስፍርውበት ይነበባል።

8ኛው መቶ ክፍለዘመን እስልምና ወደ ግብጽ በወረራ ገብቶ የኮፕት ህዝቦችን ሲያስር ክርስቲያን ኮፕቶች በሙስሊሞች ፊት የራሳቸውን የኮፕቲክ ቋንቋ መናገር እንኳን ተከልክለው ነበር፤ በኮፕትኛ የተናገሩ ምላሶቻቸው ተቆረጠው ይወጡባቸው ነበር። በዚህ መልክ ቁንቋቸውን ሙሉ በሙሉ አጥፍተውባቸዋል፤ በኮፕት ቋንቋ ፈንታ አረብኛን ተክተውባቸዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍን በድፍረት መደለዛቸው ክርስትናን ለመዋጋትና ለማጥፋት የመጡ መሆናቸውን ብሎም መሀመድ ሀሰተኛ ነብይ መሆኑን ነው የሚያረጋግጠው።

በተጨማሪም መሀመዳውያኑ በበላይነት የእብደት ስሜት መጠመዳቸውን፣ ለክርስቲያኖች አምላክ እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ ያላቸውን ድፍረት፣ ንቀትና ጥላቻ፤ ባጠቃላይ ዲያብሎሳዊ እብሪተኛነታቸውን ነው የሚያሳየን።

በቁርአን ጽሁፍ የተደለዘው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍለ ጽሑፍ ይህ ነው፦

[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፰]

፲፬ የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል።

፲፭፤፲፮ አምላክህን እግዚአብሔርን በኮሬብ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን። እንዳልሞት የአምላኬን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አልስማ፥ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አልይ ብለህ እንደ ለመንኸው ሁሉ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።

፲፯ እግዚአብሔርም አለኝ። የተናገሩት መልካም ነው፤

፲፰ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል፤

፲፱ በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ።

ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ፥ እርሱ ይገደል።

፳፩ በልብህም። እግዚአብሔር ያልተናገውን ቃል እናውቅ ዘንድ እንዴት ይቻለናል? ብትል፥

፳፪ ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።

______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: