ለክርስቲያን እህታችን ነፍሷን ይማርላት!
እንደዛሬው ሳይሆን፤ ገና በ52 ዓ.ም ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ወደ ሕንድ ሲጓዝ አሁን “ኢስላማባድ” በምትባለዋ ከተማ በኩል ነበር ያለፈው።
ኢትዮጵያ አገራችን ከነዚህ የቃኤል ፍየል አገሮች ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ማድረጓ በጣም ያሳዝነኛል። ስኳሩና ዱቄቱ ሁሉ ከፓኪስትን ነው የሚገባው… ለመሆኑ እነማን ናቸው ይህን ዓይነቱን ግኑኝነት የሚሹት? ሠርጎ–ገብ እስማኤላውያን? አዎ! ይህ የሚያጠራጥር አይደለም።
፫ኛ ዓመታቸው ነው – በሙስሊሞች እጅ በሰማዕትነት የተገድሉትን ወንድሞቻችንን አንረሳም
አንድ ኢትዮጵያዊ የቅርብ ጓደኛችን ከእስልምና ጨለማ ወጥቶ የተዋሕዶ ብርሃነ ክርስቶስን ከተቀበለ በኋላ ነቀምቴ የሚኖሩትን እናቱንም እንዲሁ ወደ ክርስቶስ አመጣቸው። ከዚያ እስላም ቤተሰቦቹ፡ አባቱን ጨምሮ፡ እናቱን እያሳደዱ ሊገሏቸው ሞከሩ፤ አልተሳካላቸውም፡ እናትየዋ አምልጠው ጠፉ። ይህ ግሩም የሆነ ጓደኛችን፡ የስጋ ነገር ሆኖ፡ በየአገሩ ካሉት የስጋ ዘመዶቹ ጋር በማህበራዊ ድህረ ገጾች ይገናኝ እንደነበር ነገረኝ። ከሦስት ዓመታት በፊት፡ ልክ በዚህ ሰሞን፡ የተዋሕዶ ሰማዕታት በሊቢያ ሲሰው በፌስቡክ ለእነዚህ ሙስሊም ዘመዶቹ ዜናውን አካፈላቸው። ከዚያም ሁሉም የሚከተለውን መልስ ሰጡት፦
“በሊቢያ የተገደሉት ኢትዮጵያውያኑስ ታድለዋል፡ በጎራዴ ብቻ ነውና የታረዱት፤ በደቡብ አፍሪቃ ግን ኢትዮጵያውያኑ በእሳት ተቃጠለው ነው የሞቱት”
ይህን ሲነግረኝ ቁስል ብሎ እያለቀሰ ነበር፤ “ከዚህ በኋላ ከአንዳቸውም ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት አላደርግም፡ በቃኝ!“ አለኝ።