የጌታ ስቅለት | በዚያን ዕለት የከርስቶስ ልጆች ክርስቲያን፤ የፀረ-ክርስቶሱ እስላም ተባሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2018
ከመጽሐፈ ጸሎት የተወሰደ
“ሕማማተ መስቀል”
የላይኛው ቪዲዮ በ “Passion“ ፊልም ምክኒያት በብዙ አገሮች በዩቲዩብ የታገደ ነውና ይሄኛው እንድ አማራጭ ቀርቧል
ጌታም ቆላተ ዮሳፍጥ ከሚባል በረሀ አውርዶ መናውን ውሀውን ከወትሮ አብልጦ አወረደላቸው። ኃይሉን ክሂሎቱን አሳያቸው። መርዛማ እባብ አስነሥቶ ጐድናቸውን እያስቀደደ አስፈጃቸው። ሙሴም “አቤቱ ጌታዬ ሕዝበ እስራኤልን የሚመግባቸው ቢያጣ ከበረሀ አውርዶ አስፈጃቸው እንዳይሉህ መድኃኒት ፈልግላቸው” ብሎ ጸለየ። ጌታም የወዳጁን ጸሎት ፈጥኖ ይሰማልና “ብረቱን እባብ አስመስለህ በተራራ ላይ ተራዳ ተክለህ ብረቱን በዚያ ላይ ሰቅለህ አሳያቸው። ያን አይቶ ሰምቶ ያመነ ይዳን፤ ያላመነ ይፈጸም፤” አለው። ተራራው የቀራንዮ አምሳል ነው፣ ተራዳው የመስቀል፣ ብረቱ የወልደ እግዚአብሔር፣ እባብ የዲያብሎስ፣ ቍስሉ የኃጢአት፣ መርዙ የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ፣ በረኃው የገሃነመ እሳት አምሳል ነው። ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለቱ፤ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፤ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።
ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለት ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት፣ ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፡ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አይሁድ፣ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።
ነፍስ ያለው እባብ የገደላቸውን ሰዎች ነፍስ የሌለው ብርት እንዳዳናቸው በባሕርዩ ሞት የሌለበት አምላክ ዲያብሎስ ያስገራቸውን ነፍሳት ተሰቅሎ ሞቶ የማዳኑ አምሳል ነው።
ጽዮን የተባለች ማኅፀነ ማርያም ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሏ ነው።
ጌታም እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በማኅፀነ ማርያም አድሬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው። አንድም ጽዮን የተባለ መሰቀሉ ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሉ ነው
እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በመስቀል ተሰቅዬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ
በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው እንዲህ ፯ት ተአምራት ሲሠሩ አይተው የባሕርይ አምላክ ነው እንጂ የባሕርይ አምላክማ ካልሆነ እንዲህ ያሉ ተአምራት ባልተሠሩ ነበር ያሉ ክርስቲያን ተባሉ።
አምላክ አይደለም፣ አልተወለደም፣ አልተሰቀለም፤ የአምላክ ወዳጅ ደግ ሰው ነብይ ብቻ እንጂ ያሉት እስላም ተባሉ። እስላምና ክርስቲያን የተባለበት ያን ዕለት ነው።
አይሁድ ግን አላክም ነብይም አይደለም ሐሳዌ መሲሕ ነው ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለም ብለው ካዱት።
“መናፍቃን ካህናት አላውያን መኳንንት ከሀድያን ነገሥታት ሃይማኖታችሁን ጣሉ ፈጣሪያችሁን ካዱ ለጣኦት ስገዱ ብለው እንደ እኔ እራሳችሁን እየመቱ አክሊለ ሦክ ግንድ አሸክመው በብረት ቢቸነክሯችሁ መራር ሐሞት ቢያጠጧችሁ ዋጋችሁን በመንግሥት ተቀበሉት እንጂ ሃይማኖታችሁን አትጣሉ፤ ፈጣሪያችሁን አትካዱ፤ ለጣኦት አትስገዱ!” በማለት ጌታችን አስተምሮናል።
Leave a Reply