ቢቢሲ፤ „Is this the world’s toughest commute?“
“ይህ በዓለም በጣም ከባድ የሆነው ጉዞ ይሆንን?“ የሚል ርዕስ ሰጥቶታል።
ቪዲዮው የሚያሳየው የኢትዮጵያን ውብ የሆነ መልክዓምድራዊ ገጽታን የተላበሰውን የ ”ገራልታ ሰንሰለታማ ተራራ” ነው። በውስጡም እንደ “አቡነ የማታ ጎህ ገዳም” የመሳሰሉትን እፁብ ድንቅ የሚባሉ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶችን አቅፎ ይዟል፡፡ ገራልታ በትግራይ ክልል ሓውዜን ይገኛል፡፡ ሓውዜን ከውቡ ገራልታ ሰንሰለታማ ተራራ በተጨማሪ በርካታ ውቅር አብያተ–ክርስቲያናት የሚገኙባት፤ የታታሪ ነዋሪዎች መገኛም ነች፡፡
ሁሉም ነገር ድንቅ ነው! ተራራዎቹ፣ ብርሃኑና ቀለማቱ በጣም ያስደንቃሉ። ጽሑፉ “ኮፕቲክ ቄስ” ከማለቱ በስተቀር፡ የካሜራው አነሳስም የሚያስደንቅ ነው። ምናለ ወደእነዚህ የተቀደሱ ተራሮች ሄጄ እንዲህ ማንሳት ቢቻለኝ?!