Archive for March 22nd, 2018
A Lovely March 22
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2018
Posted in Love, Music | Leave a Comment »
የአለም ፍፃሜ ደርሶ ይሆን? | ታዋቂው የእስራኤል ራቢ ጥቁር ሕዝቦችን ክዝንጀሮዎች ጋር በማነፃፀራቸው በአይሁዶች ተወገዙ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2018
የጌታችን መምጫው ቀን ሳይቃረብ አይቀርም፤ ያው ፀረ–ክርስቶሱ ዓለም በዘረኝነት ጋኔን ተለክፏል፤ የመጀመሪያው ተጠቂዎችም ጥቁር የምንባለው ሕዝቦች ነን።
አይሁዶችም ሆኑ ሙስሊሞች የክርስቶስ ብርሃንና ፍቅር ይጎድላቸዋል፤ ክርስቶስን ካልተቀበሉና፡ በዓመጽ ከቀኝ ወደግራ መጻፉን ከቀጠሉ ለመቅሰፍት መጋለጣቸው የማይቀር ነው።
የሚገርም ነው፡ በሃይድ ፓርክ ጥቁሮችን ዝንጀሮ ያለው የግብጹ ሙስሊም ሰባኪ ስም “ኦማር” ነው። እንዲሁ፡ አሁን ጥቁሮችን ዝንጀሮ ያሉት የእስራኤል ራቢ ይስሐቅ ዮሴፍ አባታቸው (አብደላ የሱፍ) ከኢራቅ የፈለሱ የባግዳድ ተወላጅ ናቸው። እሳቸውም የጻፉት ታዋቂ መጽሐፍ ስም “ያቪያ ኦማር” ይባላል። ራቢ ዮሴፍ ከዚህ ከአባታቸው መጽሐፍ አምስት መመሪያዎችን ሰብሰበዋል።
የሴፋርዲያን አይሁዶች ራቢን የሆኑት ይስሕቅ ዮሴፍ በየሳምንቱ ቅዳሜ በሚያደርጉት የስብከት ስነሥርዓት ላይ ነበር በአሜሪካ ነጭ ቤተሰቦች ያሉትን ህፃን ሲያዩ “እንደ እንግዳ ነገር” እንደሆነባቸው በማስተማሪያ ጽሑፋቸው የገለጹት።
አድኤል የተባለውና በ ኒው ዮርክ ከተማ ተቀማጭነት ያለው የአይሁድ ተሟጋች እና ፀረ–ሴማዊነትን የሚዋጋው ድርጅት፣ የራቢ ዮሴፍ አስተያየትን “ዘረኝነት የተሞላበት” እና “ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው” እንደሆነ በማውሳት ተቃውሞውን ገልጧል።
ከ Ynet News የተገኘው የስብከት ቪዲዮ “ኩሺ” የሚባለውን የዕብራይስጡን ቃል “ዝንጀሮ” ከሚለው ቃል ጋር እያፈራረቁ ሲጠቀሙ ይሰማል። በዘመናዊ የዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት “ኩሺ” የሚለው ቃል ከ “ባሪያ” ወይም “ንዑስ ሰው” ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኩሽ “ኢትዮጵያ” የምትባለዋን አገራችንን ተክቶ ይገኛል።
ራቢ ዮሴፍ ዩሲፍ ጥቁር ሰዎችን ከዝንጀሮዎች ጋር ያነጻጸሩት ታልሙድን በመጥቀስ እንደሆነ ገልጠዋል።
ራቢ ዮሴፍ በእስራኤል ውስጥ ከሁለቱ የአሁዳውያን ታላላቅ መምህራን አንዱ ናቸው። እሳቸው በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በኢቤሪያ ባሕረ ገብ እና በሰሜን አፍሪካ የተገኙትን የአይሁድ ዝርያዎችን ሴፋርዲያንን ሲወክሉ፤ ራቢ ዳዊት ሎው ደግሞ የ አይሁዶችን የአውሮፓ የዘር ሐረግ ያላቸውን አሽከናዝ አይሁዶች ያገለግላሉ።
ራቢ ይስሐቅ ዮሴፍ በሃገረ እስራኤል፡ አህዛብ በጭራሽ መኖር የለባቸውም የሚል እምነት አላቸው።
— ጥቁሮችን “ዝንጆሮ” እያለ ሲሳደብ የነበረው ግብጻዊው ሙስሊም ሰባኪ የእንግሊዙን ፖሊስ በክፉኛ አቆሰለው
______
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: Anti-Defamation League, ራቢ የስሐቅ ዮሴፍ, ሴፋርድያን, ስድብ, አይሁዶች, እስራኤል, ዘረኝነት, ዝንጀሮ, Israel, Jewish, Rabbi, Yitzhak Yosef | Leave a Comment »