Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2018
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

እህተ ማርያም | ቡና፣ ጫት፣ ሺሻ፣ ሰንደል፣ ጥንቁልና፣ ቀይ መጋረጃ፣ የኢሬቻ በዓል፤ ሁሉም ከሰይጣን ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 18, 2018

ሁሉም የክርስቶስን ልጆች ለማጥፋት በዲያብሎስ የተተከሉ አረሞች ናቸው። ክርስቶስን ወይም አረሙን ምረጡ”

ይህ እንከን የማይወጣለት ኃይለኛ መልዕክት ነው። በጣም የሚደንቅ ነው፤ እህታችን ጥቃቅን መስለው የሚታዩትን ነገሮች ሁሉ ነው እንድትታዘብ እድሉ የተሰጣት፤ ጆሮ ያለው ያዳምጥ!

ባለፈው መስከረም ላይ የ ቅ/እስጢፋኖስ ዕለት በቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብዬ እንዳለሁ፤ አንዲት ሴት መኪና እየነዳች መጥታ አጠገቤ አቆመች፤ ከዚያም ወርዳ እኔ አጠገብ ቁጭ አለችና ቦታው የማይፈቅድልንን ጥያቄዎች ትጠይቀኝ ጀመር፡ በዝምታ ሳልፋት ስልኳን ከፍታ ስታወራው የነበረው ብልግና ለጆሮ የሚቀፍ ነበር። በዚህ ወቅት በቃ “ጠንቋይ” መሆን አለባት ብዬ ተንስቼ ሄድኩ።

አዎ! አይጦቹ በየጎረቤቱ፣ የተለከፉት ሴትና ወንድ በየቤተክርስቲያኑ እየተላኩ ነው።

በተዋሕዶ ልጆች ላይ ያነጣጠረው ቀስት ከሁሉም አቅጣጫ ነው ተወጥሮ የሚታየው። ይህ ጦርነት ዓለማቀፋዊ መልክ የያዘና በሁሉም አቅጣጫ የሚካሄድ ነው።

እኛ ክርስቲያኖች የብሔራዊ ስሜት ሳይገድበን የክርስቶስ ከሆኑ ወንደሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንድናብር እንታዘዛለን።

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ፡ “ይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ይለናል።

ኮራጁ ዲያብሎስ ፀረክርስቶሱም የራሱ የሆኑትን ሁሉ ለዓላማው በመላው ዓለም በጋራ ሰብስቧቸዋል፦

ለምሳሌ ኮሙኒዝም “የዓለም ወዛደሮች ሁሉ ተባበሩ” በሚል መርሆ አመጸኞቹን ግራኞች ያስተባብራል፣ እስልምና ለ “ኡማችን / እናታችን” በሚል መርሆ በመላው ዓለም ያሉትን ግራኝ ሙስሊሞች ሁሉ ያስተባብራል፣ ዓለማዊነት/ ሴኩላሪዝም ደግሞ ዓማናይየሆኑትን ግራኝ ልጆቹን በመለው ዓለም ያስተባብራል። ዓለማውያኑ ምዕራባውያን ሙስሊሞችን አምልኳቸውን ወደ አገሮቻቸው ሲያስገቡ፣ ሙስሊሞቹ ደግሞ ወደ አገሮቻቸው የምዕራባውያኑን አምልኮና የገባያ ማዕከላት ያስገባሉ፤ ዓብያተ ክርስትያናትን ግን ይከለክላሉ።

እነዚህ ሦስት ቡድኖች የተለያየ የሚመስል መንገድ ቢከተሉም ግን የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው፤ ሁሉም የፀረክርስቶሱን ልብስ ለብሰዋልና። ምንም እንኳን ተልዕኳቸው ዓለም አቀፋዊ ባሕርይ የያዘ መስሎ ቢታይም፤ እግረ መንገዳቸውን ግን “ብሔራዊ” ማንነታቸውን በመላው ዓለም ለማሰራጨት ነው የተነሱት፦ ኮሙኒዝም እና ሴኩላሪዝም የምዕራባውያኑን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት፤ እስልምና ደግሞ የአረቡን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት ለማስፋፋት ይታገላሉ።

በአገራችን የሚታዩት ፀረኢትዮጵያዊነትና ፀረተዋሕዶ ዘመቻዎች የእነዚህ ሦስት ቡድኖች ወኪሎች መሆናቸው በግልጽ የሚታይ ነው። አኩሪውን ክርስቲያናዊው ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ለማጥፋት በክህደት ወሃ የተጠመቁት ወገኖቻችን ለዓለም አቀፋዊው የሉሲፈራዊ ሥርዓት እራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው። ያውም ለጊዚያዊ ጥቅም ሲሉ!

የአረቡ፣ የህንዱ፣ የሱዳኑ፣ የሶማሌውና የቻይናው መጉረፍ፣ ጎረቤት አገሮች እየፈራረሱ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መደረጉ፣ እንዲሁም የጠንቋዩ፣ የቃልቻው፣ የዕጹ፣ የሺሻው፣ የቡናው ወዘተ ባህል መስፋፋት በኢትዮጲያዊነት ላይ የተጠነሰሰ ሤራ መኖሩን ይጠቁመናልኢትዮጵያዊነት = ክርስትና!

እህቶቻችንን ወደ አረብ አገር በመላክ በጋኔን እንዲሞሉና ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው ቡናውን ለሰዎች በየቦታው እንዲያጠጡ ይደረጋሉ፣ ሰይጣናዊውን የኢሬቻ በዓል ብሔራዊ በዓል ለማድረግ ይሞከራል፣ (መስቀልን ለምተካት … በመስቀል ክብረ በዓል ማግስት) ፣ የተዋሕዶ ወጣቶችን በእናት ቤተክርስቲያናቸው መንፈሳዊ መዝሙሮችን እንዳይዘምሩ ሲተናኮሏቸው፤ የራያ ጨፋሪዎች ግን በየቤተክርስቲያኑ ሰተት ብለው እንዲገቡና ባሕላቸውን እንዲያስተዋውቁ ይታዘዛሉ።

ይህን ከባድ የፈተና ጊዜ የመወጣቱ ኃላፊነት ያለብን እኛ እያንዳንዳችን ነን፤ በግላችን፡ ከታች ወደላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ ከቻልን የጠላቶቻችንና ተባባሪዎቻቸው ሤራ ብዙም ሊያሳስበን አይገባም።

እስኪ ለጊዜው ከቡናው፣ በተለይ ደግሞ በጣም አደገኛ ከሆኑት ሺሻና ጫት እንቆጠብ፣ (እንደ አዲስ አበባ ከፍተኛማ በሆኑ ቦታዎች ጫትና ሺሻ የጤና ጠንቅ ናቸው)። እስኪ በእምነት ከማይመስሉን ጋር መደበላለቁን እናቁም። እነዚህን በእጃችን ያሉትን ቀላል ነገሮች እያንዳንዳችን ማድረግ ካልቻልን ሌላውን መውቀስና መኮነን መብት ሊኖረን አይገባም።

______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: