የማርያም እህቶች በጣና ሐይቅ ላይ የኖኅን መርከብ አዩ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2018
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]
“የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”
ድንቅ ነው፤ እግዚአብሔር በደመናዎች ላይ ብዙ ምልክቶችን እያሳየን ነውና ወደ ታች ሳይሆን ወደላይ መመልከቱን ማዘውተር ሊኖርብን ነው።
በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ “ሰባቱ ኪዳናት” ተብለው የሚታወቁትና የቅዱሱ ኪዳን አካላት የኾኑት፡ የኢትዮጵያዊነት ተዋህዶ ሃያማነኖታችን መሠረቶች፡ መደበኛ ስማቸውና መለያ ምልክታቸው ተለይቶና ተዘርዝሮ ይገኛል። እነዚህም፦
-
ኪዳነ አዳምና ሔዋን፥
-
ኪዳነ ኖኅ፥
-
ኪዳነ መልከ ጼዴቅ፥
-
ኪዳነ አብርሃም፥
-
ኪዳነ ሙሴና
-
ኪዳነ ዳዊት፥ በመጨረሻም፡
-
በድንግል ማርያምና በኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘው “ኪዳነ ምሕረት”
የሚባሉት ናቸው።
Lidj Yefdi said
Really appreciated this post! It has an intense similarity to the Scofield Study Bible’s (8) eight Covenants & the Octateuch of the old EOTC.