የሳውዲ ልዑል መሀመድ፡ በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ቤ/ ክርስቲያን፡ እየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ሆነው ታዩ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 8, 2018
የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ!!!
የሳውዲ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ባለፈው ሰኞ ያልተጠበቀ ጉብኝት በግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አድርገው ነበር። ልዑሉ ከግብጹ ፓትርያርክ ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ታውድሮስ 2ኛ ጋር ሆነው ካይሮ በሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ኮፕቲክ ካቴድራል ውስጥ ተገኝተው ነበር።
ሊቀ ጳጳስ ታዋድሮስ እንደገለጹት ከሆነ ልዑል ቢን ሳልማን ለግብጻውያን ኮፕት ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ነበር። በዚሁ አጋጣሚ ሁሉም የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቀሳውስት ሳዑዲ ዓረቢያን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።
Leave a Reply