“እግዚአብሔርን የካዳችሁ የጦር ኃይሎችና ፖለቲከኞች ኢትዮጵያዊ መልካችሁን ትለውጡ ዘንድ አይቻላችሁምና ቶሎ ወደ ወላዲተ አምላክ ተመለሱ!”
መልዕክቱ ምንም እንከን አይወጣለትም፤ 100% ትክክል ነው። አገር ቤትም ሆነ ውጭ ያሉት ፖለቲከኞች ሁሉ በእግዚአብሔር ሥርዓት ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ ማንንም ምንንም ባልፈሩና የነኞችና አረቦች ባርያ ባልሆኑ ነበር። ባንዲራውንስ አስገድደዋቸው አይደል!?
በተለይ ፀረ–ክርስቶሷ ታሪካዊ ጠላታችን ቱርክ ባገራችን ላይ አሁንም እየፈጸመች ያለችው ወንጀል ደም እንባ የሚያስለቅስ ነው፣ አባቶቻችንና እናቶቻችንን ከመቃብር የሚያስነሳ ነው። ከአረቦች ጋር ሆና ውሃውን፣ ጤፉን፣ ዱቄቱን፣ ከብቱን፣ ዘይቱንና ስኳሩን እየመረዘች ነው። ምዕራባውያኑ በኪኒን፣ መርፌና ቴክኖሎጂው፣ እስማኤላውያኑ ደግሞ በሕዝብ መሃል ሰርገው ገብተው በምግባችን፣ መጠጣችን እና ልብሳችን ላይ ዘምተዋል።
በተጨማሪ ቱርክ የጦር ሠራዊቷን በሶማሊያ እና ሱዳን በማከማቸት ላይ ትገኛለች፤ ግብጽን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደቀድሞው ለመቆጣጠር ስለምታልም፤ ዋናው ትኩረቷ አባይና ጣና ሃይቅ ላይ ነው። በጣና ሃይቅ የታየው አረም በቱርኮች የተዘራ ነው ቢሉን አይድነቀን፤ ወደ አዲስ አበባ የሚበረው የቱርክ አየር መንገድም ልክ በጣና ሃይቅ ሰማይ በኩል ነው በየቀኑ የሚያልፈው። በሰሜን ሶርያ ባለፈው አርብ ብዙ ወታደሮች የሞቱባት ቱርክ በኩርዶች ላይ የኬሚካል ቦምቦችን ተጠቅማ እንደነበር ተለጿል፤ የኔቶ አባል በመሆኗ ምዕራባውያኑ ጸጥ ብለዋል። ልፍስፍሱና ጉረኛው የቱርክ ህዝብ፡ በቅርቡ ከሰማይ እሳት ይወርድበታል!
ቤተመንግስት ውስጥ የገባው አንዱ ዘንዶም ከጣልያን ወረራና ወረራው ካስከተለው የአፄ ኃይለ ሥላሴ የእንግሊዝ አገር የስደት ኑሮ ጋር የተያያዘ ነው።
ደጋግሜ የምለው ነው፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አገር ናት፤ እግዚአብሔር በሰጠን አገር ሌላ ሕዝብ ወይም የውጭ ኃይል ዕጣዋን የመወሰን መብት የለውም። አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሠረት የክልል ሲስተም መቀየር ይኖርበታል፤ ሬፈረንደም በፍጥነት ተካሄዶ የቀድሞዎቹ ክፍለ ሃገራት መመለስ አለባቸው።