የነነዌ ጾም መልዕክት | ዲያቢሎስ ጫትን፣ ቡናንና ጥንባሆን ለመሀመድ ሰጠው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 28, 2018
ቸሩ እግዚአብሔር፡ አምላኬ ሆይ፡ ለዚህ ዕለት ብቻ “ዮናስ” እንድሆን ፍቀድልኝ።
የቡና ጉዳይ ለብዙ ዓመታት ሲያሳስበኝ የነበረ ጉዳይ ነው። እስካሁንም ስለ “ድርሳነ ጽዮን” ምንም ዓይነት እውቀት አልነበረኝም፡ ይህ ድንቅ ድርሳን፡ ሳስብባቸው ከነበሩት ነገሮች ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣጣማል፤ የሚገርም ነው። አሁን 100% እርግጠኛ ነኝ፡ መንፈስ ቅዱስ የተሞላባቸው ክርስቲያኖች፤ እንኳን ጫት፣ ሲጋራና ሺሻ (አጋንንት መሳብ ነው)፤ ቡና እንኳን መጠጣት የለብንም።
በሚገባ ተምረን ቢሆን ኖሮ፡ እነዚህን ሱስ አስያዥ ነገሮች በመላው ዓለም ለማሰራጨት የበቁት መሀመዳውያኑ አረቦችና ቱርኮች መሆናቸው ብቻ በቂ ምክንያት ሊሆነን ይገባ ነበር።
“ከፋ” የሚለው ቃልም “ኩፋር / ካፊር” ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ነው። እነዚህ ክፉ ሰዎች በዲያብሎስ አባታቸው እየተመሩ ወደ ከፋ አምጥተው ተክለውት ይሆን?
“ድርሳነ ጽዮን ማርያም” :- ተአምር 1 ላይ የተጻፈው እንዲህ ይላል:-
”ሰማያዊት የሆነች የእናታችን የጽዮን ተአምር ይህ ነው : ጸሎቷና በረከቷ ህዝበ ክርስቲያን ከምንሆን ከሁላችን ጋር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን::
ህዝበ ክርስቲያን ሆይ ልንገራቹ ሁላችሁም ስሙ የተጻፈ መጽሃፍ ሁሉ እኛ ልንመክርበት ተጽፏል እንዳለ ጳውሎስ ሮሜ 13:4 : ከአዳም ልጆች ወገን ሴሩህ የሚባል ሰው ነበር ለሴሩህ ስሙ ብኑ የሚባል ልጅ ተወልዶ በህጻንነቱ ሞተበት በብኑ ስም በተቀረጸው ጣኦት መመለክ ተጀምሯል በመቃብሩም ላይ ሰይጣን የሚወዳት ከሱስ የተነሳ ጾምን የምታሽር የከፋች ዕጽ በቀለች ይህውም በስንዴ መካከል እንክርዳድ የዘራ ጠላት ዲያብሎስ ካለችበት አምጥቶ ዘራት ማቴ 13: 28::
በብኑ ስም ቡን ተብላለች ቡና ማለት ነው: ማክሰኞ ከተፈጠሩት ዕፅዋት መልካምና ክፉ አሉ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያፈራል እንዳለ ማቴ 7:12
እስማኤላውያን የሚያመልኳቸው የጣኦታቸው መስዋዕት ሆነች የተንባላት አለቃ የሚሆን እስከ መሃመድም ትደርሳለች ተንባላትም ያለ እርሷ ሌላ አይሰውም ተንባላት ማለት የመሃመድ ተከታዮች ናቸው: ጣኦት የሚያመልኩ ባለዛሮችም ይህችኑ ይሰዋሉ የቡና ሱስ ያዘን ብለው ጾምን የሚሽሩ በበዓል የሚወቅጡ ራሳችንን አመመን በማለት በውስጣቸው ላደረ ለሱስ ጋኔን የሚገብሩ ብዙዎች ናቸው ወደ ቅዳሴም እንዳይሄዱ በጥዋት እሷን እየጠጡ ይህችም ዕጽ ክፉ ሁና ሰውን ስታሳስት ትኖራለች።
በሰለሞን ምሳሌያት ትርጉም 13:10 ክፉን ሰው ወንድሜ እንደዚህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋለህ ቢሉት እንደፈለግሁ ልሁን ለራስህ እወቅ እያለ ይነቅፋል ይላል እኛስ መንቀፍ ትተን ከቶ ብንተው ምን ይጎዳናል: “ትርጓሜ ወንጌልም “የማያሰክር ቡን አልጠጣም መንፈስቅዱስ አድሮበታል እና ይላል አንድምታ ሉቃ 1:15 እኛም በአርባ ቀን መንፈስቅዱስን ተቀብለን የለምን ? የመንፈስቅዱስ ማደርያ አካላችን የሱስ ጋኔን መደርያ ለምን ይሆናል::„
ተአምር 2፦
“ሌላም የሚያስረዳና ልቡናን የሚያጸና ስሙ ልንገራችሁ የተንባላት መምህር የነበረ ስሙ መሀመድ የሚባል አንድ ሰው ከመካዱ የተነሳ ከአጋንንት ጋር ይውላል ከዕለታት አንድ ቀን ሲሰግድ በልጅነቱ ያመው የነበረው የራስ ምታት በሽታ ይነሳበታል በዚህ በሽታ እየተሰቃየ ሳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን ዲያቢሎስ በተንኮሉ ያስተው ዘንድ ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ መሀመድ ሆይ ምን ሆንክ ይለዋል የራስ ምታት በሽታ የሆነበት እርሱ ዲያቢሎስ ነው፡፡
መሀመድ መልሶ ከፍተኛ የራስ ምታት ነበረብኝ በዚህ ደዌ እጨነቃለው ይለዋል ዲያቢሎስም የራስ ምታት መድሀኒት ብነግርህ ታደርገዋለህን የልቦናዬን ፈቃድ ትፈጽመሀልን? ይለዋል መሀመድም ካዳንከኝ አዎ ያልከኝን ሁሉ አደርገዋለሁ ብሎ የመልስለታል፡፡
ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ፡
-
ዕጸ ጌት የተባለች ጫትን፣
-
ዕፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናንና
-
ዕፀ ስጥራጢስ የተባለጭውን ጥንባሆን
እነዚህን ሶስቱን ዕፅዋት ከአሉበት አምጥቶ መድሀኒት ናቸው ብሎ ይሰጠዋል፡፡ይህንንም ቡና ከጠጣህ ፈጥነህ ትድናለህ ለልጅ ልጅ ዘመን በመካ መዲና መስዋዕት አድርገህ ሰዋ ብሎ ቆልቶ ያሰየዋል፡፡
መሀመድም ብረት ምጣድ አግሎ ያሳየዋል እንደመልኬ ከሰል አስመስልህ አጥቁረህ ትቆላለህ ይለዋል እንዳለው አድርጎ ከሰል አስመስሎ ይቆላል ሁል ጊዜም እንደዚሁ ካላከሰልክ መድሀኒት አይሆንህም ይለዋል ራስ ምታቱም ለጊዜው የተወው ይመስለዋል ኋላ ግን ሰዓት እየጠበቀ ይነሳበታል።”
አይን አይደል፡ ምን ዓይነት ከባድ ወጥመድ ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንደገባን?!
ቡና ኢትዮጵያ ነው የተገኘው በማለት ብሔራዊ መጠጥ እንዲሆን በማድረግ ዲያብሎስ ኢትዮጵያን ከጽዮን ለማራቅ መሞከሩ ይሆን? ልክ፡ የመጀመሪያዋ ሴት “ሉሲ” ናት በማለት ሙዚየም ሳይቀር እንዲሠራና የዓለማቱ መሪዎች ሁሉ እየመጡ እንዲሳለሟት እንደተደረገው? የሚገርም ነው!
Leave a Reply