የመሀመድ ቀጥተኛ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገርላቸው የዮርዳኖሱ ንጉሥ | “እኛ ሙስሊሞች ክርስቶስን፣ ቅድስት ድንግል እናቱን እና መጽሐፍ ቅዱስን እናከብራለን”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 27, 2018
በማለት ተናግረዋል። ይህ ድንቅ ነው፣ ድንቅ ነው! — (በዕብራይስጥ ቋንቋ ማለቴ ነው)
ይህን መጀመሪያ ላይ ስሰማ፡ ““ታኪያ” ወይም እስልምና ሙስሊሞችን ቅጠፉ ዋሹ ብሎ ስለሚያስተምራቸው፡ እንደተለመደው ንጉሡ እየዋሹን ይሆናል። የእኛንም ንጉሥ አርሜህን ልክ እንዲህ በማለት ነበር የመሀመድ ተከታዮች ከ1400 ዓመታት በፊት ያታለሏቸው” የሚል ሃሳብ ውስጥ ነበርኩ።
ግን ሪክ ዋይልስ እንዳለው የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ነውና፡ ምናልባት በእኝህ ንጉሥ በኩል ብዛት ያላቸውን ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ ለማምጣት አቅዶ ይሆናል።
የእኔ መለኮታዊ ምኞት፦ እንደ ሽኽ አላሙዲን የመሳሰሉ ሰዎች – በተለይ አሁን በገዛ አረብ ሙስሊም ወንድሞቻቸው እስር ቤት እንዲሰቃዩ ከተደርጉ በኋላ – ተመሳሳይ የሆነ ድርጊት እንዲፈጽሙ ነው። ይታየን አላሙዲን ከእስር ቤት ወጥተው ቢጠመቁ፣ ክርስትናን ቢቀበሉና የእስልምናን ሰይጣናዊት ቢያጋልጡ? እርግጠኛ ነኝ በሚሊየን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያችን ሙስሊሞች መዳን በቻሉ ነበር።
Leave a Reply