Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2017
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

እግዚኦ! ፈረንጁ መነኩሴ፡ “የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ማህበረሰብ በጣም እንግዳ የሆነ አንድ የአምልኮ ሥርዓት አለው” ይላል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 20, 2017

ለገና በዓል የቸኮሌት ጥንቸልለፋሲካ ደግሞ የቸኮሌት አባባ ገና

ለስጦታ ይዘው ይመጣሉ – አንዳንዴም ፎፎ ቆሎ ያቀርባሉ

39 ዓመት እድሜ ያለው ጀርመናዊ ካቶሊክ መነኩሴ ነበር ከመላው ዓለም ወደ እየሩሳሌም ለመጡ ጋዜጠኞች ይህን የተናገረው፤ ኒቆዲሞስ ስኬንቤል ይባላል፤ ያውም በጌታችን ልደት ዋዜማ።

Source/ ምንጭ፡ Haaretz + Die Welt

በቃ ሙሉዋ ዓለም የእነርሱ ብቻ ናት! እነዚህ ሰዎች አይማሩም!

ኢትዮጵያዊው በተሰጠው መንፈሳዊ ጸጋ በጣም ነው የሚቀኑት፤ ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁላ የቁሳዊ ድህነታችንን እየተጠቀሙ እኛን ለማንቋሸሽ ሲሞክሩ ይታያሉ።

ወንድሞቻችና እህቶቻችን በሆኑት የምስራቅ እና የጥንታውያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሳይቀር ተመሳሳይ ነገር አልፎ አልፎ ይታያል፦

ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን “ክርስቲያን በሚባለው ሌላው ዓለም”፣ አይሁድ ኢትዮጵያውያን በእስራኤል፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአረብ አገሮች፤ በሁላችንም ላይ አድሎዓዊ እና አስከፊ የሆኑ ድርጊቶች ሲፈጸሙ እናያላን፤ በዚህም ለእኛ ኢትዮጵያውያን ያለችን አንዲት አገር፡ ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗንን በደንብ እንታዘባለን፤ ታዲያ ከፈረንጆች እና ከአረቦች ጋር እየተባበሩ ይህችን እግዚአብሔር የሰጠንን ቅድስት አገር ለማጥፋት የሚታገሉት ቅሌታሞችና ማፈሪያዎች ይህ ጉዳይ አያሳስባቸውምን? ትግላቸውና ጦርነታቸው ከእግዚአብሔር ጋር አይደለምን?

እራሳቸውን “ነጮች” ብለው የሰየሙት ፈረንጆቹ ነጭነታቸው ለመንፈሳዊ ኑሮ እንደሚያስቸግራቸው የራሳቸው የሳይንስ ሊቆች ይጠቁማሉ። ከጸሐይ ብርሃን እጥረት የተነሳ ብዙ የሚላኒን ኬሚካል ይጎድላቸዋል። ሚላኒን ወይንም ሚላቶኒን በጥቁር ሕዝቦች ላይ፣ በተለይ በኢትዮጵያውያንን ላይ (ከፍተኛ ተራራ ላይ በሠፈሩት) ላይ በብዛት የሚገኝ ኬሚካል ሲሆን የመንፈሳዊ እና የሃይማኖታዊ ሕይወትን በማጠንከሩ ረገድ ዘንድ ከፍተኛ ሚናም እንደሚጫወት ይነገርለታል።

ነጮቹም ቢሆኑ በተሰጣቸው የማወቅ ፍላጎት-ጸጋ በቅንነት ከተራመዱ ተመሳሳዩን መንፈሳዊ ጸጋ እግዚአብሔር ይሰጣቸዋል፤ ግን በእንዲህ ዓይነት መልክ አይደለም፤ በማፌዝና በማጥላላት፤ ሌላውን ዝቅ ለማድረግ በመሞከር አይደለም።

 ጀርመናዊ ዶ/ር መነኩሴ እንዲህ ይላል፦

እዚህ እየሩሳሌም የምንገኝና የተለያዩ ዓብያተክርስቲያናት የምንወክል ክርስቲያኖች በዚህ በገና ወቅት፡ ለቡና እና ለተለየዩ መጠጦች እርስበርስ የመገባበዝ ባሕል አለን ነገር ግን ከዓብያተክርስቲያናቱ ሁሉ ትንሿ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በጣም እንግዳ የሆነ አንድ የአምልኮ ሥርዓት አላት።”

ልብ እንበል፡ “ትንሽ የሆነችው!“

ሰውዬው ቀጠል በማድረግ፦

የበዓላቱ አከባበር ስነ ሥርዓት ሁሉ ተመሰቃቅሎባቸዋል፤ ለገና እና ለፋሲካ የሚያመጧቸው ጣፋጮች ተዘበራርቀውባቸዋል፤

ለምሳሌ አለ ዶ/ር መነኩሴው፦

ለገና በዓል የቸኮሌት ጥንቸልለፋሲካ ደግሞ የቸኮሌት አባባ ገና በስጦታ መልክ ይዘው ይመጣሉ – አንዳንዴም ፎፎ ቆሎ ያቀርባሉ

አየን አይደለም፤

ስለ ጉርብትናው፣ ስለ ትህትናው፣ ስለፍቅሩ፣ ስለ አጽዋማቱ፣ ስለ ቅዳሴው እንዲሁም ኢትዮጵያውያን የጌታን ልደት በ ጃንዋሪ 7 እንደሚያከብሩ ያወሳው ነገር የለም።

አሁን ይህ ሰው ክርስቲያን ነኝ ሊል ነው?

ቀደም ሲል እንዳቀርብኩት ይህ አሜሪካዊ በገዳም አባቶች ላይ ሲያሽሟጥጥ የነበረውም በተመሳሳይ መንፈስ ነው፦

 

አይክፋን! እንዲያውም ደስ ይበለን!

ይህ በቅናትና በትዕቢት ላይ የተመረኮዘ ድርጊት የኢትዮጵያን ቤ/ክርስቲያን ብቸኛ በክርስቶስ ደም ላይ የተገነባች ጽኑ ቤት ያደርጋታል እንጂ ሊያፈርሳት አይችልም።

ተመሳሳይ ፊዘኛነት፣ ቅናትና ምቀኝነት፤

  • + ቃኤል በአቤል ላይ፣
  • + እስማኤል በይስሐቅ ላይ፣
  • + ኤሳው በያዕቆብ ላይ፣
  • + የዮሴፍ ወንደሞች በዮሴፍ ላይ፤

ሲያሳዩ አይተናል።

በዮሴፍ የቀኑት ወንድሞቹ ዮሴፍን በጥላቻ ወደ ጉድጓድ መጣላቸው ዲያብሎስ በቤተሰብ መካከል እንኳን እየገባ ሁከት እንደሚፈጽም እንማራለን።

አለምን ሁሌም ሲያመሰቃቅሏትና አሁንም እያወኳት ያሉት የቃኤል፣ እስማኤልና ኤሳው ዘሮች በዲያብሎሳዊ እራስወዳድነት መለከፋቸውን እያየነው ነው፦

  • + ስግብግብነት
  • + ቅናት
  • + ጥላቻ
  • + ጥፋት
  • + ግድያ

ፍሬዎቻቸው ለይተን እናውቃቸዋለን።

______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: