እነ አብደላ ጉዳቸው ፈላ፤
“መድኃኔ ዓለም” በመባል የሚታወቀውንና፡ በ 16ኛው ክፍለ ዘመን በጣሊያኑ ሊዖናርዶ ዳቪንቺ የተሳለውን ስዕል የገዙት እነ አላሙድኒን መሬት ላይ አንጥፈው እንዲተኙ ያደረጉት የሳዑዲው ልዑል ‘መሀመድ ቢን ሳልማን‘ ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል።
ቀደም ሲል የአጎታቸው ልጅ፡ ልዑል ባድር ናቸው ተብሎ ሲወራ ነበር፡ ነገር ግን እሳቸው እንደ ደላላ ሆነው ነበር ያገለገሉት። የአብደላ ደላላ!
በጣም የሚገርመው፦
በእስልምና ስዕል አይፈቀድም ይላሉ፤ ደግሞ፡ በኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኔ ዓለምነት አያምኑም፤ ታዲያ ይህን ያህል ገንዘብ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል ለምን ያወጣሉ? ተዓምረኛ የሆነ ጊዜ ላይ እንገኛለን!
እግረ መንገድ፦ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ብቻ 10.000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተጠርፈዋል። ተመስገን! እንበል! መድኃኔ ዓለም ለጥምቀቱ ያብቃቸው!
እግረ መንገድ፦ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ብቻ 10.000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተጠርፈዋል።
ተመስገን! እንበል! ተርፈዋል፤ ለጥምቀቱ ያብቃቸው!