Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2017
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የ CBS TVዋ እህታችን ፡ ራሄል ሰለሞን ፡ እነ Shaquille O’Nealን በበርበሬ አጨሰቻቸው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2017

CBS TVዋ እህታችን ታዋቂውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች፡ ሻኪል ኦኒልን እና የሥራ ባልደረባዋን በበርበሬ በመቃጠል/ባለመቃጠል ሩጫ ረታቻቸው፤ ጎበዝ፡ እህታችን! አገርሽንም እግረ-መንገድሽን ማስተዋወቅሽ ደስ ይላል። በርበሬ ለዘላለም ይኑር!

በርበሬው አጨሰኝ…!

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ያግድም አግድም ሔጄ ብዙ ተመክሬ አልሰማም ሰላልኩኝ፤

በእናቴ ምድጃ ቁልቁል ተደፍቼ በርበሬ ታጠንኩኝ፤

በዐይኖቼ እያነባሁ ባፌ እያስነጠስኩኝ

እንደምንም ብዬ እናቴን በመሓል እንዲህ ስል ጠየኩኝ!

አባዬ ልጅ ሳይኾን በድሜ እየበለጠን፤

ምን አጥፍቶ ይኾን ሲጋራ የሚታጠን…?’

ብዬ ብጠይቃት፥

ፀጉሬን ጨምድዳ ደፍቃኝ ወደ ጭሱ፤

ዝም ብለህ ታጠን ለየት ይላል የሱ፤

ከሕሊናው ዓለም ሲጣላ ከራሱ፤

ገላጋይ አቶ ነው ባፉ እና ባፍንጫው የሚወጣው ጭሱ፤

እናት እና አባቱ እንዳንተ በጊዜ ቢያጥኑት በበርበሬ፤

ብርቅ አይኾንም ነበር ለትንባሆ ዛሬ!

ዛሬም ያንተን ጥጋብ ልክ ካላገባው የበርበሬ ጭሱ፤

ትንሽ ከፍ ስትል ትብሳለህ ከ!

ቶሎ ካልተዘጋ የአመል በራፍህ፤

ይገባል ሲጋራ በመሀል ጣትህ፤

አለችና እናቴ ደግማ ወደጭሱ አንዴ ብትመልሰኝ፤

የወደፊቱን ሱስ ነቅሎ እያስነጠሰኝ፤ ሲጋራ እንዳላጨስ በርበሬው አጨሰኝ!!

______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: