የጃንሆይና የኬኔዲ መቀራረብ አደገኛ ነበርን? ኬኔዲ የተገደሉባት እና ጃንሆይ በዋሽንግተን የተንሸራሸሩባት ሊሞዚን መኪና አንድ ነበረች።
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 16, 2017
ያለ ምክኒያት ነበርን፡ ባለፈው ወር ላይ፤ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአምስት ዓስርተ ዓመታት በላይ በአሜሪካን ብሔራዊ ቤተመዛግብት መስሪያ ቤት በጥብቅ ምስጢር ሲጠበቅ የነበረውን የጆን ኤፍ ኬኔዲን ግዳያ የያዘ ምስጢራዊ ፋይል ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ማድረጋቸው?
እንደሚመስለኝ፤ ግድያው ከክርስትና ጋር እና ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር ከነበራቸው መቀራረብ የተያያዘ ነው። ም ዕራባውያኑ ኢትዮጵያን ዘለው ቢያልፉ ነው የሚሻላቸው፤ ለሉሲፈር የሚገዙ ስለሆነ፤ ክርስትና እና ኢትዮጵያ ቦታ እንዳይሰጣቸው ወይም ማናቸውም ዓይነት ተጽዕኖ እንዳይኖራቸው ይሻሉ። ለዚህም ነው የአሜሪካ ፕሬዚደንቶችና የሮማ ጳጳሳት ኢትዮጵያን ጎብኝተው የማያውቁት(የቅርቡ የኦባማ ጉብኝት ቀልድ ነው)።
ጥቁር በሚሏት አፍሪቃ፡ ተምሳሌታዊ፣ አርአያ እና አባታዊ ሊሆን የሚችል መሪ እንዲኖረን አይፈቅዱልንም። አፄ ኃይለ ሥላሴን እና በኋላም ጠ/ምኒስትር መለስ ዜናዊን የገደሏቸው ይህን ተምሳሊያዊነት ባለመፈለግ ነው። በአፍሪቃ ፈርኦን እንዲኖራት የተፈቀደላት ግብጽ ብቻ ናት፤ ይህንም ለፕሬዚደንት አል–ሲሲ በስጧቸው ከፍተኛ ቦታ መገንዘብ ይቻላል።
አንድ “ጥቁር”አፍሪቃዊ መሪ ለመጨረሻ ጊዜ በዋሽንግተን እጅግ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ያው እንደምናየው፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት ወር 1963 ዓ.ም ነበር።
በነገራችን ላይ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴን፣ ኬኔዲን፣ አቶ መለስን፣ አቡነ ጳውሎስን ያስገደሏቸው አንድ ዓይነት ኃይሎች ናቸው። ከ5 ዓመታት በፊት ይህን ተናግሬዋለሁ፤ ስለ ጠ/ምኒስትር መለስ እና አቡነ ጳውሎስ ሞት፣ ፕሬዚደንት ኦባማ፣ የግብጹ ፕሬዚደንት ሙርሲ እና ሸህ አላሙዲን የሚያውቁት ነገር አለ።
ሙባረክ በኢትዮጵያ ላይ ዛተ ታሰረ፣ ሙርሲ ደነፋ እስር ቤት ገባ፣ አላሙዲን በኢትዮጵያ ዶሮዎች ላይ ዘመተ ታሰረ…ሰዶማ ኦባማ ነው የቀረው፤ አቤት እሱና ክሊንተንን የሚጠብቃቸው ነገር! አንድ ቀን፡ ሁሉም መውጣቱ አይቀርም።
Leave a Reply