Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2017
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 14th, 2017

ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው | በፍቅርና አንድነት ሰባተኛ ሆንን፣ እንኳን ደስ ያለን! የኢትዮጵያ ጠላቶች ፭፣ ፮፣ ፯ ጊዜ ተመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 14, 2017

ተቀበልንም አልተቀበልንም ፥ ወደድንም ጠላንም፡ ኢትዮጵያ አገራችን የሌላ የማንም ምድር አይደለችም፤ የእግዚአብሔር ምድር ናት። ስለዚህ፡ በምድረ ኢትዮጵያ እየተንከባከበ ለድል የሚያበቁን አንድ እግዚአብሔር እና በቅዱሳን ተራሮቻችን ያስቀመጣቸው የእርሱ መላዕክትና ቅዱሳን ናቸው።

ሰሞኑን በለንደኑ የዓለም አትሊቲክስ ውድድር ያየነው፤ አንድነት፣ ፍቅርና መተሰሳብ ለድል እንደሚያበቃንና ምንም ነገር ሊበግረን እንደማይችል ነበር ያሳየን።

የሆነ ወቅት ላይ የእግዚአብሔር እጅ እንዳለበት ሆኖ ነበር የታየኝ።

ሲያሽሟጥጡብን፣ ሲሳለቁብን፣ ሲተናኮሉን፣ ሲያዳክሙንና ቅስማችንን ለመስበር ሲሞክሩ የነበሩት ተንኮለኛ እባቦች በእግዚአብሔር እጅ ተደቁሰዋል። ከሌላ ጊዜ ጋር ሲወዳደር የተገኘው የሚዳሊያ ቁጥር ብዙም አይደለም፣ ነገር ግን፣ በወገኖች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት በሚፈጸምበት የዛሬ ወቅት፣ የቴሌቪዥን ካሜራሰዎችና ፕሮግራም አቅራቢዎች ተራችን ሲደርስ ዘወር ማለታቸውንና ሌሎቹን እንቅፋቶች ሁሉ አልፈው ለዚህ መብቃታቸው በእውነት እንደ ተዓምር ነው የሚቆጠረው። እንደ ኪኒያ ሁለተኛ፣ ወይም እንደ ሞግዚቷ እንግሊዝ 6ኛ ከመውጣት ሰባተኛ መውጣታችን እንደ ትልቅ ድል ይቆጠራል።

በሜዳልያ ደረጃ ሰባተኛ መሆናችንም ያለምክኒያት አይደለም፤ ሙስሊሙ ወንድማችን (በኢትዮጵያዊነት) ሙክታርም የአምልኮ ወንድሙን መሀመድ ፋራን መፈርፈሩ ያለምክኒያት አይደለም (ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)

በቅዱስ መጽሐፍ አቆጣጠር ሰባት () ፍጹምና ሙሉ ቁጥር በመሆኑ ከአንድ እስከ ሰባት ( ፩–፯ ) የተዘረዘሩት ምስጢራተ ቤተክርስቲያንም እንከንና ጉድለት የሌለባቸው ፍጹማን ናቸው።
ሰባት ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓት ፍጹም ለመሆን ለማወቅ ከዚህ የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንመልከት፦

ሰባት ቁጥር ምስጢራት በቤተክርስቲያን፤

በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ስባት ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን ዘንድም ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ [ምሳሌ 2416} እግዚአብሔር ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት የነበሩት በ7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ [ዘዳ 1321]

ከዚህ ቀጥለንም ለቤተክርስቲያን አስተምህሮ የ፯ ቁጥር ምስጢራትን ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፦

/ ሰባቱ አባቶች

1. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
2.
የነፍስ አባት
3.
ወላጅ አባት
4.
የክርስትና አባት
5.
የጡት አባት
6.
የቆብ አባት
7.
የቀለም አባት

/ ሰባቱ ዲያቆናት

1. ቅዱስ እስጢፋኖስ
2.
ቅዱስ ፊልጶስ
3.
ቅዱስ ጵሮክሮስ
4.
ቅዱስ ጢሞና
5.
ቅዱስ ኒቃሮና
6.
ቅዱስ ጳርሜና
7.
ቅዱስ ኒቆላዎስ

/ ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ

1. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
2.
የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
3.
እኔ የበጎች በር ነኝ
4.
መልካም እረኛ እኔ ነኝ
5.
ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
6.
እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
7.
እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

/ ሰባቱ ሰማያት

1. ጽርሐ አርያም
2.
መንበረ መንግሥት
3.
ሰማይ ውዱድ
4.
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
5.
ኢዮር
6.
ራማ
7.
ኤረር

/ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት

1. ቅዱስ ሚካኤል
2.
ቅዱስ ገብርኤል
3.
ቅዱስ ሩፋኤል
4.
ቅዱስ ራጉኤል
5.
ቅዱስ ዑራኤል
6.
ቅዱስ ፋኑኤል
7.
ቅዱስ ሳቁኤል

/ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት

1. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2.
የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
3.
የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4.
የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
5.
የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6.
የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
7.
የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

/ ሰባቱ ተዐምራት

  • ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

1. ፀሐይ ጨልሟል
2.
ጨረቃ ደም ሆነ
3.
ከዋክብት ረገፉ
4.
ዐለቶች ተሠነጠቁ
5.
መቃብራት ተከፈቱ
6.
ሙታን ተነሡ
7.
የቤተ መቅደስም መጋረጃ

/ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
2.
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
3.
ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
4.
እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
5.
ተጠማሁ
6.
ተፈጸመ
7.
አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

/ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን

1. ምሥጢረ ጥምቀት
2.
ምሥጢረ ሜሮን
3.
ምሥጢረ ቁርባን
4.
ምሥጢረ ክህነት
5.
ምሥጢረ ተክሊል
6.
ምሥጢረ ንስሐ
7.
ምሥጢረ ቀንዲል

/ ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት

1. ዐቢይ ጾም
2.
የሐዋርያት ጾም
3.
የፍልሰታ ጾም
4.
ጾመ ነቢያት
5.
ጾመ ገሀድ
6.
ጾመ ነነዌ
7.
ጾመ ድኅነት

/ ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

1. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ 166-19
2.
ሃሰተኛ ምላስ
3.
ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
4.
ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
5.
ለክፋት የምትፈጥን እጅ
6.
የሐሰት ምስክርነት
7.
በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

/ ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት

1. ነግህ የጠዋት ጸሎት
2.
ሠለስት (3 ሰዓት ጸሎት)
3.
ቀትር (6 ሰዓት ጸሎት)
4.
ተሰአቱ (9 ሰዓት ጸሎት)
5.
ሰርክ (11 ሰዓት ጸሎት)
6.
ነዋም (የምኝታ ጸሎት)
7.
መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , | 2 Comments »

 
%d bloggers like this: