Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2017
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ግእዝ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ሐይማኖታዊ/ መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። የዓለም ህዝብ ተቀብሎታል፤ ከኢትዮጵያውያን በስተቀር”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 7, 2017

ዛሬ: ..አ: 07/07/2017 ነው። ምስሉ ኩራታችን የሆነው አየር መንገዳችን ቦይንግ 777 ን ሲያበር ያሳያል።

በእግዚአብሔር አምላካችን ዘንድ አንድ ሐቅ ነው ያለችው፤ ወደድንም ጠላንም፡ አንድ ሐቅ ብቻ! ግዜ በእጃችን አይደለም ያለው፤ ለእኛ የተባለውን ነገር ሁሉ፣ የተሰጠነን ህልውና፣ የተረከብነውን ቅዱስ መንፈስ በመጠቀም ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ ነው በሥራ ላይ ማወል የሚገባን። “ቆዩ፤ አሁን ሁኔታው አይፈቅድም ቀስ እንበል!„ እያሉ ከመቀመጫቸው መነሳት የማይሹትን አታላዮችና ሌላውንም እንዲያንቀላፋ የሚያደርጉት፣ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ላይ ነው ከባድ መዘዝ በማምጣት ላይ የሚገኙት። የራሳቸውን ቆሻሻ የቤት ሥራ ለመጪው ትውልድ አሳልፎ በመተው፡ በአሁኖቹ ህፃናት ላይ ሊሰረዝ የማይችሉ በደልና ኃጢአት ነው የሚፈጽሙት።

“ኢትዮጵያ አገራችን ተከባልች፣ ጠላቶቿ እራሳቸው በዘረጉት የጊዜ ጎዳና ላይ በመጓዝ አመቺ የሚሆነላቸውን አጋጣሚ በመጠበቅ ላይ ናቸው!፡” እያልኩ ላለፉት 15 ዓመታት ባቅሜ ያለማቋረጥ እጠቁም ዘንድ እግዚአብሔር ይገፋፋኝ ነበር። ሉሲፈራውያኑ ችግኞቻቸውን በየአገራቱ ተክለዋል፣ በተለይ በአገራችን፤ የክርስቶስንም ልጆች በግልጽ ለመዋጋት ቆርጠው ከተነሱ ውለው አድረዋል። ባሁኑ ሰዓትም ኢአማናያን ሰዶማውያኑን እና መሀመዳውያኑን እንደ መሳሪያ አድርገው በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አሁን ሁላችንም አካሄዳቸውን መከተል የምንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ዓይን ያለው ፈጥኖ ይመልከት።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ምን እንደሚሰሩ፡ ብሎም ማን እንደሆኑ ለመላው ዓለም በግልጽ ደፍረው ብዙውን ነገር እያሳዩን ነው። ካሳዩንም ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉትን እንመልከት፤ ይህ ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ ነው የተከሰተው፦

  1. ታላቋ ብሪታኒያ ከአውሮፓው ህብረት ትወጣለች ብለው በፍጹም አልጠበቁም። brexitሬፈረንደም ውጤቱን ለመከለስ ያው እስካሁን በመታገል ላይ ናቸው

  2. የዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዚደንትነት መብቃት ፈጽሞ አልጠበቁትም ነበር። ከተመረጡበት ቀን ጀምሮ በሳቸው እና ደጋፊዎቻቸው ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃት ዘመቻ በታሪክ ተወዳዳሪ አይኖረውም

  3. ኢትዮጵያውያን በአገር ቤትም በውጩም እርስበራሳቸው እንዲበጣበጡ፣ በህንድ ውቂያኖስ፣ በቀይ ባሕር፣ በሜዲተራንያን ባሕር፣ በቆሼበለንደን እና በካሌ ለሉሲፈር መስዋእት እንዲሆኑ ተደረጉ

  4. ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተመረጡ። አንድ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ማድረግ በሚችል ድርጅት ውስጥ “ሰርጎ” መግባቱ፣ ከኢትዮጵያዊነት አንፃር፡ እሰይ! ትልቅ ነገር ነው! ለአገራችን የሚበጅ ነው! የሚያሰኝ ነው። ከስልጣን፣ ከታዋቂነት እና ከንዋይ ኃብት የበለጠ፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያን፡ ሌላ እጅግ ትልቅ ነገር አለ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እና እግዚአብሔር አምላኳን የሚያስደስት ሥራ ለመሥራት ይበቃሉን? ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም እንጸልይላቸው።

  5. ሊሲፈራውያኑ በአሜሪካ የሠሩትን ዓይነት ስህተት ላለመስራት፣ በፈረንሳይ ሰዶማዊውን ማክሮንን ፕሬዚደንት ለማድረግ በቁ

  6. በአየርላንድም ሰዶማዊውን የህንድ ስደተኛ በጠቅላይ ምኒስቴርነት አስቀመጡ

  7. በጀርመንም አንድ ሳምንት ብቻ በፈጀው ያልተጠበቀ ስብሰባ የሰዶማውያን “ጋብቻ” ሕጋዊ እንዲሆን በጥድፊያ አጸደቁት። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  8. በኢትዮጵያም መንፈሳዊውን ኢትዮጵያኛ የግእዝ/አማርኛ ቋንቋ ለማጥፋት እንዲሁ በተጣደፈ መልክ ምክር ቤቱ ህግ እንዲያጸድቀ ተደረገ። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  9. G20 አገራቱ መሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት በፊት የአፍሪቃው ህብረት መሪዎች በአዲስ አበባ ተሰባሰቡ

እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችም በዚህ የሀምበርጉ የመሪዎች ስብሰባ ላ በሪፖርት መልክ ለውይይት እንደሚቀርቡ የሚያጠራጥር አይደለም። በነገራችን ላይ፡ ሀምበርግ ከተማ በተቃዋሚ ኃይሎች ብጥብጥ እየታወከችና እየነደደች ነው! እሳት! እሳት! እሳት!

አፍሪቃ ዋና የመወያያ ርዕስ እንደሆነች ቀደም ሲል ተጠቁሟል። ብዙ የአፍሪቃ አገሮች መሪዎች በስብሰባው እንዲሳተፉ ቢደረግም፤ አፍሪቃን በዋናነት የሚወክሉት ግን ደቡብ አፍሪቃዊውና ባለ አራት ሚስቱ (ሰዶማዊ) ያዕቆብ ዙማ ናቸው።

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

በእኛ አቆጣጠር በ 2007 .ላይ ታታሪው ወንድማችን ፍስሐ ያዜ ካሳ ሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” የሚለውን ድንቅ መፅሐፍ ጽፎልናል።የዚህ መፅሐፍ ትኩረት ስለ አዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ብቻ ሳይሆን፤ የፍፃሜው ጦርነት ምን እንደሚመስል፣ኢትዮጵያም ከፍፃሜው ጦርነት ጋ በተያያዘ የተለየ ትኩረት እንደተደረገባት፣ ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤ እግዚአብሔርንና መላዕክቱንም እናሸንፋለን!ብለው የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን የሚዝቱበትና የሚዘጋጁበት፤ ጦርነቱም በዋናነት ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሆን፤ጎላቸውም ኢትዮጵያ እንደሆነች ይገልፃል። የዓለማችን ታላላቅ የሚባሉ ገለባ አገራትና መሪዎች ከዚህ በኋላ ትልቁ የቤት ስራቸው ኢትዮጵያ ላይ እንደሆነ በማስረጃ እያስደገፈ ተንትኖታል፡፡

ለዛሬው የሚከተለውን ከመጽሐፉ ጠቅሼ አቅርቤዋለሁ፦

በቅርቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንትን ሊዘጋ ነው ሲባል ሰማሁና በጣም ተገረምኩ። እንዴት? ታሪክ ከታጠፈ ጂኦግራፊም ቀረ ማለት ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። የዲፓርትመንቱ ሃላፊዎች ለምን አደጋ እንዳንዣበበበት ሲጠየቁ “በዘርፉ የሚመረቁ ተእማሪዎች ስራ እያጡ ተቸገርን፣ 70/30 ፕሮግራም፣ ወዘተ…„ የሚል የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ዓይነት ምክንያት ሲሰጡ ሰማሁና ግርም እንዳለኝ ተውኩት። የታሪክ ትምህርትን ያጠፋች አገር ካለች ብየ ኢንተርኔት ላይ አጣራሁ። ይኖራል ብዬ ማሰቤ ራሱ የሚገርም ነው። የለም! ስራ ስላለ ስለሌለ ነው እንዴ ታሪክ ማወቅና መማር ማስተማር ያስፈለገው? ምን ማለት ይሆን? እያልኩ ሳይገባኝ አለሁ። ጭራሽ ኢትዮጵያ ታሪክን ማስቀረት? አሜሪካ እንኳ የሶስት መቶ ዓመት ታሪክ ይዛ ልዩ ትኩረት የሰጠችው ዲፓርትመንት ነው። ጭራሽ ኢትዮጵያ? ታሪክን ማስቀረት ማለት ምን ማለት መሰለህቀጣዩን ትውልድ አገርም ታሪክም ንብረትም ማንነትም ምንም ምንም የለህም ማለት ነው። መነሻም መድረሻም የሌላቸው ከንቱ ትውልዶች ናችሁ! ማለት ነው! ቀጥተኛ ትርጉሙ ይሄ ነው። ቀጣዩን ትውል ምን እያሉት መሰለህየግዛታችሁ ስፋት አይታወቅም። አባቶቻችሁም አልተናገሩም እንደማለት ነው! ደግነቱ ቀጣይ ትውልድ የሚባል ነገር…„

አሁንማ ግልጽ ሆነ! ለምን እንደዚያ እንደተደረገም አውቅነ! ይሄ ብቻ ሳይሆን ይህ በተባለ ማግስት በታሪካዊው ቤተ መፃህፍት የነበሩትን ታሪካዊ ሰነዶች በሙሉ ቦታ ጠበበ በሚል ተልካሻና አስቂኝ ምክንያት ለሲቅ እቃ መጠቅለያነት ይውሉ ዘንድ ጠርገው አወጡና አጫርተው ሸጧቸው። ግራ ገብቶኝ ነበር። ግን ግልፅ ሆነ። ለካስትልቅ የዛፍ ግንድን ሲገዘግዙ ሲገዘግዙ ቆይተው፤ ግዝገዛው ሲያልቅ ግንድስ ብሎ መውደቁ ነው። ገዝጋዡም ስራውን አጠናቆ ላቡን እየጠራረገ እፎይ ብሎ አረፈ። ተገንድሶ የወደቀውን ግንድ ገዝጋዡ ተሸክሞ የመሄድ ግዴታ የለበትም። ለሸክም የተዘጋጁ ሊሎች ሰራተኞች ይኖራሉ። የቀረውን ግፋፎና ቅጠላ ቅጠል የሚጋፋና አካባቢውን የሚያፀዱም ተዘጋጅተዋል፤ ስራው ግን ተጠናቋል!„

በጣም ያሳዝናል! ግዝገዛውን አውቅ ነበር። ይሄኛውን ግን አልሰማሁም፤ አዝናለሁ”

አሁን ነው እንዲያ የሆነው። አንድ ተማሪ አልተቀበሉም። በማግስቱ ግን አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛን ቋንቋ በመደበኛ ፕሮግራም በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ጀመረ። የራሳችንን ትተን ቻይንኛ እየተማርን ነው። ቻይና ደግሞ በተመሳሳይ አማርኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋዋ አድርጋ አገሯ ላይ እያስተማረች ነው። ሌሎች የG20 አገራትም እንደ ቻይና አማርኛንና ግእዝን ሶስተኛ ቋንቁ አድርገው በዲግሪ እያስተማሩ ነው። እስከ ፒ...ዲ ድረስ እያስተማሩ ነው። ይህን ነገር በዜና ሳይ ያው ከልማቱ ጋር በተገናኘ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። አሁን ነው ጅልነቴ የገባኝ። ለካስ ታዘው ነው። ስለዚህ እኛ የነሱን መማር ጀመርንእውነት ለንግዱ፣ ለልማቱ፣ ለምናምኑ ቻይንኛን መልመድ እዚህ ድረስ አስፈልጎ ነው? ከዚህ ወዲያ ውድቀት አለ? ከዚህ ወዲያ ሴራ አለ? ሌቦች ናቸው! እኛም እልል ብለን እንቀበላቸዋለን!

አንድ ተረት ልናገር፦ ሰሜን ሸዋ አካባቢ አንዲት እብድ ነበረች አሉ። ይቺ ታዋቂ እብድ በአንድ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ትነሳና፣ “ዛሬ ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። እያለች ስትለፍፍ አረፈደች። የቀዬው ሰዎች ግን፤ “ዛሬ ደግሞ ይቺ እብድ በጠዋት ተነሳባት” እያሉ አሽሟጠጧት። ቀኑ የገባያ ቀን ነውና የእብዷን ልፍለፋ ከምንም ሳይቆጥሩ ልብ ብለውም ሳይሰሙ ጎጆ ቤታቸውን ዘጋግተው ወደ ገበያ ሄዱ። አጅሪት ደግሞ ቀዬው ጭር ማለቱን ስታይ፤ እሳት በችቦ ትለኩስና ያንን ሁሉ ጎጆ ቤት ታቃጥለዋለች። ሁሉንም ቤት አንድዳ ዞር ትላለች። ያገሬው ህዝብ ገበያ ውሉ ሲመጣ መንደሩ እንዳለ ተቃጥሏል። በዚህ ጊዜ ያች እብድ ተመልሳ መጣችና፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል፤ ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያለች ትናገር ጀመር። አሁንም ከዚህ ቀደም ጥቂት ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ታሪክ እየተዘረፈ ነው፤ ታሪኩም አፈ ታሪክ አይደለም፤ ከ3ሺ ዓመትም ይበልጣል፤ ነጮችንም አትመኑ እያሉ ስድብ ቢጤም እያካተቱ ለመግለፅ ሞክረው ነበር። ይገሬው ጎሳ መሪዎች ግን ፈፈፋውን ልብ አላሉም፤ ወደ ጎን ሊሉት ሞከሩ። አሁን እኔ እነሱን ብሆን ኖሮ እንደዚያች እብድ፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያልኩ በየአደባባዩ እለፍፍ ነበር”

የሚያሳዝን ነው!“

አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል

It’s 07/07/17 | G20 Summit Embarrassment: Germany’s Merkel Bows To Saudi Arabian State Minister


______

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: