ቪዲዮ | ኢትዮጵያ መንፈሳዊ ጥበቃ የሚደረግላት ብቸኛ የፕላኔታችን አገር በመሆኗ ግብዙ የአድቬንቲስቶች ‘ሊቅ’ ሲመጻደቅባት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 22, 2017
ቀናተኞች! በዓለማዊውና ቁሳቁሳዊ ድኽነታችን ቀዳዳ እየፈለገ ያሽሟጥጥብናል። ሌላ ምክኒያት ሊኖር አይችልም።
እኔ እንኳን ባቅሜ የማቀርባቸውን የቤተክርስቲያናት ቪዲዮዎች ይህ ሊቅ ነኝ ባይ ወስላታመርጦ ካቀረባቸው ፎቶዎች ጋር አነጻጽሩ። ባቅራቢያዬ ያሉና ኢትዮጵያ ሄደው የማያዉቁት ብዙ ፈረንጆች ስለ ዓብያተክርስቲያናቶቻችን ያነሳኋዋቸውን ቢዲዮዎች ሳሳያቸው “ለምንድን ነው እንዲህ ዓይተን የማናውቀው? እናንተም እነድዚህ የመሳሰሉ ህንፃዎች አሏችሁ?” በማለት አንዳንድ ቀና የሆኑት ተገርመው ይጠይቁኛል። ብዙዎቹ የሚያነሱት ሆን ብለው መጥፎ መጥፎውን፣ የራሳቸውን አኗኗር ከፍ የሚያደርጉበት፤ ባጠቃላይ እነርሱ የተመረጡ ሕዝቦች መሆናቸውን የሚያሳዩበትን ነገር ብቻ ነው። ደካሞች! ያው ብዙዎቹ ነፍስ አዳኞች ተመሳሳይ በሆነ መልክ ነው ለዘመናት ስለ ኢትዮጵያ የሚናገሩት፤ ቅጥፈት ብቻ። አቤት ለአገራችንን እና ለኢትዮጵያውያን ያላቸው ንቀት! የሰው ልጅ ሁሉም አገር ይበላል፣ ይጠጣል ወደ መጸዳጃ ቤት ይሄዳል… ልዩ ምርጥ ዘር አለ? በተጨማሪ፡ መቼሽ ሁሉንም ነገር ማወቅ አይችል፡ ታዲያ ምናለ ትንሽ እንኳን እራሳቸውን በኃፍረትና በትሕትና ዝቅ ቢያደርጉ! የኛ በጎነት ይከነክናቸዋል፡ በቃ እድሉን የከዳቸው ያስመስላቸዋል። አዎ! ከኛ የተሻለ አንድ የሚያቁት ቁልፍ ነገር ኢትዮጵያ መንፈሳዊ ጥበቃ የሚደረግላት ብቸኛ የፕላኔታችን አገር መሆኗን ነው። ይህን ይደብቁናል፤ በዚህ በጣም ይቀናሉ!
ሰዉዬው ደቡብ አፍሪቃዊ ነው፣ Walter Veith ይባላል፤ አድቬንቲስቶች በመላው ዓለም የሚኮሩበትና ሊቅ ነው የሚሉት ግለሰብ ነው። መንፈሳዊ ነኝ የሚል ግለሰብ ይህ ዓይነት መረጃ ቁምነገር ነው ብሎ ያመጣልን? በፍጹም!
Leave a Reply