Coffee = ካፊር? | እስካሁን በተለምዶ የምናውቀውን የቡና አመጣጥ ታሪክ ከልሰን በጭንቅላቱ መገልበጥ ሊኖርብን ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2017
ክፉ = ከፋ = ክቫ = ካፊር?
እጅግ በጣም አስገራሚ ግኝት ነው! – የዚህ ቡና ምስል፡ ልክ፡ 834 × 666 ነው። ጉድ ነው፡ እንደዚሁ ነው ያገኘሁት!
የሚያስገርም UPDATE!! 31. May
መላው ዓለም “ኮፊ/ካፌ/ክቫ…„ ብሎ የሚጠራው ቡና፡ በኢትዮጵያኛ “ቡን” ወይም “ቡና ተበሎ ነው የሚጠራው። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚል ጥያቄ ሁልጊዜ በጭንቅላቴ ይብላላ ነበር። ታዲያ አሁን በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚሰማው አሜሪካዊው አስገራሚ አገላለጽ ትክክል ይሆን? ሰምቼ አላውቅም፣ ግን የሚያስኬድ ነው።
ብዙዎቻችን ባናውቀውም፣ አንዳንድ አባቶች እንደሚያስተምሩን፦
ከ2ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ባህታዊያንና መናኞች በጎጃም ክፍለ ሀገር በዘጌ አውራጃ ሲፀልዩ በነበረበት ጊዜ “መንፈስ ቅዱስ ይህን ቅጠል ሸምጥጣችሁ ጠጡት ለጸሎት እንድትነቁ ይረዳችኋል” ተብሎ እንደነበርና ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በኢትዮጵያ ቡና መጠጣት እንደተጀመረ መነገሩን ነው።
በ10ኛው መቶ ዘመን የዘጌ ሦስት ቅዱሳን ምን እንብላ ብለው ሱባዔ ቢገቡ መልአክ እግዚአብሔር ለጸሎት እንድትተጉ ቡና ጠጡ ብሎ ጥቅሙን ክነአሰራሩ ነገራቸው። ከዚያ በኋላ በየሀገሩ መጠጣት ተጀምሯል።
ነገር ግን ተላላዎቹና ግድየለሾቹ የኢትዮጵያ ልጆች እስካሁን የምናውቀው ታሪክ የሚከተለው ነው፦
በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ በ ከፋ ክፍለሃገር ብዙ ቡና ይጠጣ ስለነበርና የዐረብ ነጋዴዎችን የእስልምና ሃይማኖት ሰባኪዎች በዚያ ክፍለ ሀገር በብዛት ስለገቡ ወደ አረብ ሀገር ከአውራጃው ስም ጋራ ይወስዱታል! በዚህ ምክንያት በብዙ ቋንቋ ካፌ፣ ኮፊ ይባላል።
ለመሆኑ ይህ የ ከፋ ክፍለሃገር፡ እስልምና ከመፈጠሩ በፊት፡ ማለትም ከ666 ዓ.ም በፊት ምን ተብሎ ይሆን ሲጠራ የነበረው?
አትኩሮት ልንሰጣቸው የሚገቡንን እነዚህን ነገሮች ለመድገም፡–
1ኛ. በቀደሙ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን አባቶች ዘንድ ቡና በባህታዊያንና መናኞች ዓማካኝነት በ2ኛው ክፍለዘመን መገኘቱን
2ኛ. ይህን በመቃረን አዲስ ትውፊት በሙስሊሞች አማካኝነት መፈጠሩን፡ ማለተም፦
በድሮ ጊዜ ከፋ ከሚባል የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ አንድ ካልዲ የሚባል የፍየል እረኛ ነበር አሉ። ከለታት ባንድ ቀን ታድያ ካልዲ ከሚጠብቃቸው ፍየሎች ውስጥ አንዷ የሆነ ዛፍ ፍሬን (ወይም ቅጠልን — ከሁለት አንዱን) በልታ ያልተገባ ባህርይ ማሳየት ትጀምራለች — አንደመጨፈር፣ አንደመዝለል አይነት። በዚህ ጊዜ ካልዲ የዛን ዛፍ ቅጠል ወይም ፍሬ እቤቱ ወስዶ ሲቆላው እጅግ በጣም ደስ የሚል እና ልዩ ስሜት የሚሰጥ ሽታ ይሸተዋል። ከዛን ቀን በኋላ ካልዲ ቡናን በተለያየ መልክ መጠቀም ጀመረ፤ ለአለምም አስፋፋው። እነሆ አለምም ከዛ ወዲህ የቡና ወዳጅ ብሎም ሱሰኛ ሆነች። ከዚህ በተጨማሪ የእንግሊዝኛው ስም የመጣው ቡና ከተገኘበት ቦታ እንደሆነ ይነገራል። ምክንያቱም ከፋ የሚለው ስም Coffee ከሚለው ስም ጋር ስለሚመሳሰል።
አሃሃ! ፍየል ገባችበት፡ “ከፊር” የሚለውም ቃል ወጣ፡ ተሸፈነ። ፍየል የአጋንንት ምሳሌ ናት።
3ኛ. ከፋ ባሁን ሰዓት ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች አስቸጋሪ ነው ከሚባሉት ክልሎች መካከል ቀደምተኛ ቦታ መያዙ።
አንዳንድ ሰዎች ቡናን በጸሎት ወቅት መጠጣት ቢጀመሩም በኋላ ላይ ግን ቡና ይከለከል እደነበር የሚናገሩም አሉ።
ሌሎች ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቡና አትጠጡ ብላ የምታስተምረው መሰረቱ ከመናኞች የመጣ በመሆኑ ነው። የቤተ ክርስቲያን አባቶች የሚሉት “ቡናውን ስትቆሉ መልኩ አይጥቆር ቡናው ተቆልቶ ሲወጣና ሲሸትትም ሆነ ሲጠጣ የእግዚአብሔር ስም ይጠራበት” ከማለት በቀር አንዳንዶች እንደሚሉት ቡና አትጠጡ ብላ ለምዕመናኗ አታስተምርም።
እዚህ ላይ የማክለው አንድ ምስጢር፦
ጣልያኖች “Espresso” / ኤስፕሬሶ የሚሉት አጭር ቡና ጥቁር እስኪል ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ ከሚቆላው የቡና ፍሬ የሚገኝ ነው። እንደ እኔ፦ ኤስፕሬሶ ለስጋዊውም ሆነ ለመንፈሳዊ ጤንነት በጣም አደገኛ ሳይሆን አይቀርም። ኤስፕሬሶ በተደጋጋሚ የሚያዘወትሩ ሰዎች “ልቤን! ልቤ መታ!“ ሲሉ ይሰማሉ።
ለማንኛውም፡ እኔ፡ ከፋ የሚለው የቦታ ስም ከመቼ ጀምሮ እንደሚታወቅ እስካልታወቀ ድረስ፤ ይህ አሜሪካዊ ያቀረበው ትርጉም ትክክል ሆኖ ነው ያገኘሁት። ኮፊ/ክቫ የሚለው መጠሪያ “ከፋ ወይም ክፉ” (ቡና ክፉ /የከፋ ነው!) ከሚለው የኢትዮጵያኛ ቃል ሌቦቹ ዓረቦች ሰምተው “ከፊር” የሚለውን ቃል ለእኛ ለክርስቲያኖች እና አይሁዶች ሰጥተውናል። ቡና ብዙ ምስጢር ያለው አትክልት ነው፤ በአረቦች ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሻይ ከቡና ይመረጣል። በአገራችን ቡና ሲጠጣ ብዙ ጊዜ እጣን ይጬሳል፡ እጣንም እንደዚሁ ብዙ ምስጢር ያለው ክቡር ነገር ነው።
አሁን አሁን፡ አባቶቻችን ሲሉን እንደነበረው፡ “ቡናውን ስትቆሉ መልኩ አይጥቆር ቡናው ተቆልቶ ሲወጣና ሲሸትትም ሆነ ሲጠጣ የእግዚአብሔር ስም ይጠራበት” ሳይሆን አብዛኛው ተለምዷዊውን የቡና ሥነስርዓት የሚያካሂደው፡ እንዲያውም በተቃራኒው ክርስቲያን ካልሆኑ ሰዎች ጋር በመደባለቅ፤ እጣኑም ውስጥ አደገኛ የአረብና የህንድ ኬሚካል በመጨመር ሆኗል። ማታማታ ሳይቀር ቡና እያፈሉ ከሙስሊሞች ጋር ተደበላልቀው አብረው የሚጠጡ በየጎረቤቱ ይታያል። (ጋኔን ለመሳብ!)
ዛሬ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቡና የሚጠጣው ጀንፈል የሚሉት የቡናው መሸፈኛ ቅርፊት ሲሆን ከቡና ይልቅ ጀንፈል አምሮቱን ያረካል ይባላል።
ጊዜ ወስዳችሁ አዳምጡት፤ ብዙ ጠቃሚ ትምህርት ያዘለ ቪዲዮ ነው
The Source For 70 Per Cent Of The World’s Coffee Consumption Could Be Extinct By The End Of This Century « Addis Ethiopia Weblog said
[…] — Coffee = ካፊር? | እስካሁን በተለምዶ የምናውቀውን የቡና አመጣጥ ታሪክ ከልሰን … […]
Yonas Abebe said
Wow. 👍 Article.
Mimi said
ቀሽም ማውራት ሰተቻለ ብቻ አፍ አይከፈትም ውሸታ፡፡ እድሜ ልካችሁን አሰሱንም ገሰሱንም ከሃይማኖታችሁ ጋር ስታገናኙ ትኖራላችሁ ኮንፊደንስ ሚባል ነገር አልፈጠረባችሁም፡፡ ነገ ደሞ እንጀራ ከመንፈስ ቅዱስብየእያያዘ ነው በል እያልክ እያልክ ሽሮ እና በሬ ላይግባ፡፡ ለራሳችሁ ሃይማኖት ክብር ከሌላችሁ ይሰውን ግን አትንኩ ራሳችሁን ችላችሁ እዛው ማጀት ተርመጥመጡ ቡና ሻይ ስትሉ እኛን ለቀቅ