Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2017
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 10th, 2017

የሰሙነ ሕማማት ጸሎት መግቢያና ማሰሪያ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 10, 2017

ሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን እስከ ይዌድስዋ ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና ሰዓቱ የተመደበውን አቡን ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ ይመራሉ፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፡፡ በመቀጠል፡

ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡

አመኑኤልአ ምላኪየ ለከ ኃይል ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡

ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይልለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡

ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኩቴት (12) ጊዜ በመሐሉ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመና እየተደገመ ይባላል፡፡

ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ በዜወነ፡፡

በሌላኛው ወገን ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኀቡረ እስመ ውእቱ ገብረ ምድኃኒተ በብዝኀ ሣህሉ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን (እግዚኦ ተሣሃል)፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን እብኖዲ(በቅብጥ አምላክ) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ታኦስ (በጽርዕ አምላክ) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ (ቅቡዕ የተቀባ መሲሕ) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኢየሱስ (መድኅን መድኃኒት) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ክርስቶስ (ዳግማይ አዳም ምሉአ ጸጋ ቀዳሜ በኩረ ልደት ለኩሉ ፍጥት) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን አማኑኤል (ስመ ሥጋዌ) ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይናን (መሐር ኪያነ፤ መሐረነ) ኪርያላይሶን ፡፡

ኪርያላይሶን እየተባለ በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ

ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን

እየተባለ ይሰገዳል፡፡

በመጨረሻ ጊዜ፡

ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡

ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡

ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡

ምንጭ

____

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: