Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2017
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  23242526272829
  3031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for January 16th, 2017

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን | Happy Epiphany

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2017

ምሥጢረ ጥምቀት

ጥምቀት፡ማለት ‹‹አጥመቀ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆ ትርጉሙም ማጥመቅ ፣ መጠመቅ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከራስ ፀጉር እስደ እግር ጥፍር ድረስ በተጸለየበት ውሃ /ማየ ሕይወት ወይም ማየ ገንቦ/ ውስጥ በሥላሴ ስም መጥለቅ መዘፈቅ ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት ሌሎች ምሥጢራትን ለመፈጸም የመግቢያ በር ነው፡፡ ወደ ሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ከመሔዳችን በፊት ጥምቀት በብሉይ ኪዳን ምን እንደሚመስል እንመልከት::

ጥምቀት በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን ጥምቀት በውሃ በታጠብ ፣ መጥለቅና መንፃት ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን በዓል ሲከበር በዓሉን ለማክበር የሚሰበሰበው ሕዝብ በሙሉ በውሃ በመረጨት ለበዓሉ ዝግጅት የሚፈልጉ ዕቃዎችን ሁሉ በውሃ መታጠብና መንፃት ነበረባቸው፡፡ ዘሌ 627

በብሉይ ኪዳን ሰውን ወይም ዕቃን ያረክሳሱ ተብሎ የሚታመንባቸው ነገሮች ነበሩ ለምሳሌ፡ለመሥዋዕት የታረደችውን ጊደር ደም በጣቱ የነካ የዝግባ እንጨትና ግምጃ ወስዶ የጊደሪቱን ሥጋና አጥንት ለሚቃጠልበት የጣለ ካህን ልብሱንና ገላውን በውሃ ካልታጠበ ወደ ሰፈር መግባት አይፈቀድለትም ነበር፡፡ የሞተ ሰው አስከሬን የነካ በሞተበተ ድንኳን ውስጥ የገባ ሁሉ እንደርኩስ የቆጠር ስለነበር በውሃ መታጠብና መንፃት የተለመደ ሕግ ነበር፡፡ ዘፀ 1918 ፣ መዝ 5051፡፡ ከብሉይ ኪዳን ውጭ የነበረ ሰው የኦሪቱን አምነት ሲቀበል ከማኅበረ አይሁድ ከመግባቱ በፊት መገረዝና መታጠብ ገድ ነበር፡፡ ከተገረዘና ከታጠበ በኋላ እንደ አይሁድ ሥርዓት መባዕ ማቅረብና ከማኅበሩ ጋር አንድ መሆን ይፈቀድለታል፡፡ ከሌላው እምነት ወከ ይሁዳነት ሊገባም ዕለት እንደተወለደ ሕፃን ይቆጠር እንደነበር መጻሕፍት ይነግሩናል፡፡ እራሱን ከኢግዙርነት መለየት ከመቃብር እንደመውጣት ነው ተብሎም ፈይታመን ነበር፡፡

ሌላው የብሉይ ኪዳን ጥምቀት የዮሐንስ ጥምቀት ነው፡፡ የሐንስ የንስሐ ጥምቀትን ያጠምቅ ነበር፡፡ ማር 14 የዮሐንስ ጥምቀት አማኞችን ለክርሰቶስ ጥምቀት የሚያዘጋጅ የክርስቶስን ጥምቀት ለመቀበልና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ባለቤት ለመሆ የሚያበቃ ነበር፡፡ ሜቴ 311 የሚያጠምቅበትም ዓለማ ሰዎችን ከኃጢአት ወደ ሥርየት ከአምልከኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መመለስና ሥርየተ ኃጢአት አግኝቶ ከማሕበረ ጻድቃን ጋር አንድ መሆንን ያሳያል፡፡ በብሉይ ኪዳን ይፈጸም የነበረው ጥምቀት ምንም እንኳን ምሳሌነት ቢኖረውም በሐዲስ ኪዳን እንደሚፈጸመው ጥምቀት ምሥጢር አልነበረም፡፡ የብሉይ ኪዳን ጥምቀት ፈየመንጻት ጥምቀት ነበር እንጂ፡፡

ዮሐ 26

የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን

ስለ ጥምቀት አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን ብዙ ምሳሌ ተመስሏለወ ትንቢትም ተነግሯል፡፡ ከምሳሌዎቹም ጥቂቶቹን ስንመለከት፡

1ኛ የኖህ መርከብ ዘፍ 717 1ኛ ጴጥ 320 መርከቧ የጥምቀት ምሳሌ ስትሆን በመርከቧ ተጠልለው የዳኑት ሰዎች የአማንያን ምሳሌ በንፍር ውሃ የጠፉት የኢአማንያን ምሳሌ ናቸው፡፡ በመርከብ ውስጥ የነበሩት እንደዳኑ በጥምቀት አምነው የተጠመቁ ሁሉ ከሲኦል ባህር ከመስጠም ሲድኑ ከመርከቧ ውጭ የነበሩት ሰጥመው እንደጠፉ በጥምቀት ባለማመን ጸንተው ያልተጠመቁም በሲኦል ባህር ሰጥመው ይቀራሉ፡፡

2ኛ ግዝረት፡ዘፍ 1714 ግዝረት የተገረዙ ሁሉ የአብርሃም ልጆች ይባሉ እንደነበር ያለተገረዙ ሁሉ ደግሞ ከአብርሃም ልጅነት የወጡ ነበር፡፡ አሁንም የተጠመቀ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ በመባል ሲኖር ያልተጠመቀ ደግሞ ከእግዚአብሔር ልጅነት ይለያሉና ግዝረት ለጥምቀት ምሳሌ ሆነ፡፡

3ኛ እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው፡እስራኤላውያኑ የክርስቲያኖች ምሳሌ ግብፃውያን የአጋንንት ምሳሌ ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤላውያን በግዞት ከነበሩበት ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡት ባህረ ኤርትራን ከተሻገሩ በኋላ ነው፡፡ ባህረ ኤርትራ ለፈርኦንና ለሠራዊቱ ሞትን ሲያስከትል ለእስራኤላውያን ግን ሕይወት ፣ ደስታንና ነፃነትን አጎናጽፏቸዋል፡፡ ክርስቲያኖችም በጥምቀት በርኩሳን አጋንንት ከመገዛት ከዘለዓለም ሞት ነፃ ወጥተዋል የኤርትራን ባህር ለፈርኦንና ለሠራዊቱ ድል መንሻ እንደሆነ በጥምቀትም አጋንንት ድል ሆነዋል፡፡

4ኛ እስራኤላውያን በኢያሱ መሪነት ፈለገ ዮርዳኖስን መሻገራቸው ኢያሱ 41-9 እስራኤላውያን ዮርዳኖስን ተሸግረው ከነአን እንደገቡ ክርስቲያኖችም ተጠምቀው ወደ እርሳቸው ገነት መንግሥተ ሰማያት ይገባሉና፡፡

5ኛ አብርሃም ፈለገ ዮርዳኖስን ተሸግሮ ከመልከጼዴቅ ኅብስተ አኮቴት ጽዋዓ በረከት መቀበሉ ዘፍ 1417

አብርሃም የምእመናን ምሳሌ

መልከጼዴቅ የክርሰቶስ /የካህናት/ ምሳሌ

ሕብስተ አኮቴት ጽዋዓ በረከት የክርስቶስ ሥጋወደም ምሳሌ

ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌ

አብርሃም ዮረዳኖስን ከተሻገረ በኋላ ህብስተ አኮቴት ጽዋዕ በረከት እንደተቀበለ እኛም ከተጠመቅን በኋላ የጌታን ሥጋና ደም እንቀበላለንና፡፡

የጥምቀት ትንቢት በብሉይ ኪዳን

1ኛ ‹‹ጥሩ ውሃ እረጫችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ›› ሕዝ 3625 ጥሩ ውሃ የተባለው የምንጠመቅበት ውሃ ነው፡፡ በንፁህ ውሃ የታጠበ ነገር ደዕድፈቱ እነደሚጠራ ሰውም አምኖ ሲጠመቅ ኃጢአቱ ይሠረይለታልና፡፡ ሌላው

2ኛ ‹‹ምህረትን ፈየወዳልና… ኃጢአታችንንም በባህር ጥልቅ ይጥለዋል›› ሚክ 719 በጥልቅ ባህር የተመሰለው ጥምቀት ነው፡፡ በባህር ውስጥ የገባ ፍፁም እንደማይታይ በጥምቀትም የተሠረየ ኃጢአት ፈጽሞ አያስቀጣም በፍዳ አያሲይዝምና አንድም ከባህር ውስጥ በክንፋቸው የሚበሩ በእግራቸው የሚሄዱ በደረታቸው የሚሳቡ ተገኝገዋል፡፡

በጥምቀትም አንድ ልጅነት አግኝተው በመንፈስቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች አማካኝነት ለተለያ ደረጃዎች በቅተዋልና፡በክንፍ የሚበሩ የሰማዕታት ምሳሌ ፣ በእግራቸው የሚራመዱ በገዳም ተወስነው የሚኖሩ መነኮሳት ምሳሌ ፣ በደረታቸው የሚሳቡ ደግሞ በዓለም በሕግ የሚኖሩ የክርስቲያኖች ምሳሌ ናቸው፡፡

ጥምቀት ለምን ምሥጢር ተባለ?

ጥምቀት ምስጢር የተባለበት ምክንያት ከላይ እንደጠቀስነው በሚታይና በሚሰማ አገልግሎት የማይታይ ረቂቅ ጸጋ ስለሚሰጥበትና ላመኑት ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ውሃው ተለውጦ ከጌታ ጎን የወጣውን ውሃ /ማየ ገቦ/ ሲሆን የምንጠመቅበት ገንዳ ከግሞ ማኅጸነ ዮርዳኖስ ሲሆን አለመታየቱ ከመምህር ተምሮ በልቡና በማመን የሚታወቅ በመሆኑ አንድም እግዚአብሔር የገለጠልንን ያህል ካሆነ በስተቀር ስለማነውቀው ምሥጢር ተባለ፡፡

የጥምቀት አስፈላጊነት /ጥቅም/

ድህነት እናገኛለን፡ማር1616 ‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል›› ይላል፡፡ ይህን ይይዙና ‹‹ያላመነ›› እንጂ ‹‹ያልተጠመቀ›› ይፈረድበታል አይልም ስለዚህ አለማመን አንጂ አለመጠመቅ አያስፈርድም ይላሉ፡፡ ይህ ግን አይደለም ባይጻፍም በውስጡ ‹‹ያልተጠመቀ›› የሚለው ቃል እንዳለ እናስተውል፡፡ ምክንያቱም ከፊት ያድናል ያለው ያመነ ብቻ ሳይሆን የተጠመቀም ነው የሚለው፡፡ ታዲያ ያመነና የተጠመቀ ከዳነ የማይድነው ወይም የሚፈረድበት ደግሞ ፈያላመነና ያለተጠመቀው ጭምር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዮሐ 101 ፣ ዮሐ 139 ስለዚህ ግድ ለመዳን ማመን ብቻ አይጠቅምም መጠመቅም ያሻል፡፡

ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ እንወለዳለንጌታችን ምስጢረ ጥምቀትን በትምህርት ለኒቆዲሞስ በሥጋ ከወላጆቻችን እንደተወለድን ሁሉ ‹‹ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ልትወለዱ ግድ አላችሁ›› ብሎ አስረድቶታል፡፡ ዮሐ 33 የሐነስ መጥምቅም ፈሪሳውያንን እና ሰዱቃውያንን ደገሰጻቸው በኋላ ‹‹እኔ የንስሐ ጥምቀት አጠምቃችኋለሁ የጫማውን ጠፈር ልፈታ የማይገባኝ ከኔ በኋላ የሚመጣው ግን እርሱ በመንፈስ ቀዱስ አሳትነት ያጠምቃችኋል፡፡›› ብሎ ግልጽ ቃል ተናግሯል፡፡ ሜቴ 311 ለዚህ ነው በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ከእግዚአብሔር እንወለዳለን ያልነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለመንፈስ ልጁ ለቲቶ ‹‹የመድኃቲታችን የእግዚእብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን›› ቲቶ35 ብሎ ድንቅ ቃል ተናግሯል፡፡ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች እንባላለን፡፡ እናንተን ግን ልጆቼ ብያችኋለሁ ባሮች አይደላችሁም እንዳለ ለነቢያት ያልታደለ የልጅነት ክብር በጥምቀት እናገኛለን፡፡

ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞቱን በሚመስል ሞት ሞተን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ እንነሳለን፡ይህ ከጌታችን ጋር በጥምቀት ከሞቱና ከትንሣኤው ጋር እንሳተፋለን ማለት ነው፡፡ ሞቱን በሚመስል ሞት እሞታለን ሲል ጌታችን አንድ ጊዜ ሞቶ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው እንደለየ እኛም በጥምቀት ከኃጢአት እንለያለን ማለት ነው፡፡

የኃጢአት ሥርየት እናገኝበታለን፡ከጥምቀት በፊት ያለ ኃጢአት በጥምቀት ከጥምቀት በኋላ ያለ ኃጢአት ደግሞ በሥጋወደሙ እንደሚሠሬ ተጽፏል፡፡ በዚህም ሰው ከኃጢአት በመለየቱ በጸጋም ከእግዚአብሔር በመወለዱ የመንግሥተ ሰማይ ወራሽ ይሆናል፡፡ ሕዝ 3625 ሐዋርያትም ‹‹ኃጢአታችሁ ይሠረይ ዘንድ ንሥሐ ግቡ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ስም ተጠመቁ›› ሐዋ 238 በማለት አስተምረዋል፡፡ ከእነርሱ በኋላ የተነሱት ሠለስቱ ምዕትም ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ብለው በጸሎት ሃይማኖት ጽፈውልናል፡፡

በጥምቀት የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡በዘመነ ኦሪት የእግዚአብሔር ሕዝብ የአብርሃም ልጆች ለመባል ግዝረት ሃይማኖታዊ ግዴታ ነበር፡፡ ጥምቀትም በክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ከቅድስት ቤተክርስቲያ የሚገኝ ጸጋ ተካፋይ ከማድረጉም በላይ ራሱን ተጠማቂውን የእግዚአብሔር ልጅ ያሰኘዋል፡፡ ቆላ 211 በዚህ የክርስቶስ ቤተሰቦች የቤተክርስቲያን አባል እንሆናለን፡፡

የጥምቀት አመሰራረት በሐዲስ ኪዳን

ጥምቀት በሐዲስ ኪዳን የመሠረተው የሁሉ መሠረትና መሥራች የሆነው ጌታችንና አምላካችን መክኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሲመሠርተውም በ3 መልኩ ነው፡፡

. በትምህርት፡ለኒቆዲሞስ በማስተማር ዮሐ 35

. በትእዛዝ፡ሐዋርያትን መርጦ ካጸናቸው በኋላ እርሱ ወደ ሰማይ እንዳረገ ዓለምን ዞረው ወንጌልን እንዲሰብኩ አሕዛብንና ያላመኑትን ሁሉ ‹‹በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጉ›› ብሎ በማቴ 2819 በማዘዝ መሥርቶታል፡፡

. በተግባር፡እኛ ክርስቲያኖች ራሱ አምላክ ከኃጢአት በቀር ሳያደርገው ለኛ ለልጆቹ አድርጉ ያለን አንዳች ነገር የለም፡፡ ተጠምቆ ተጠመቁ ፣ ጹሞ ጹሙ ፣ መከራ ተቀብሎ መከራ ተቀበሉ፡፡ ስለዚህ ጥምቀቱንም በ30 ዘመኑ በእደ ዮሐንስ በባሕረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ በተግባር መሥርቶአልና፡፡

በምሥጢረ ጥምቀት ሙሉ ጸጋ የተሰጠው ግን በበዓለ ሃምሳ ለሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መውረድ በኋላ ነው፡፡

የጌታ ጥምቀት

ጌታ መቼ ተጠመቀ?

ከእመቤታችን በተወለደ በ30 ዘመኑ በዘመነ ሉቃስ ጥር 11ቀን ማክሰኞ ሌሊት 10 ሰዓት፡፡

ጌታችን ለምን ተጠመቀ?

እንደምናውቀው ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ከሠራቸው ብዙ ሥራዎች አንዱ መጠመቅ ነው፡፡ በወንጌል ትርጓሜም ‹‹ወሖሮን እግዚእ ለኃምስ ግብራት›› ማለት ጌታችን አምስቱን ሥራዎች ሄዶባቸው ወይም ሠራቸው ይላል፡፡ እነዚህ ጥምቀት ፣ ተአምኖ ኃትውእ /ኃጢአትን ማመን/ ይህ ከኃጢአተኞች ጋር መቆጠሩ እንጂ እርሱ ኃጢአት የለበትም ፣ ከዊነ ሰማዕት ሰማዕት /ምስክር/ መሆን ብሎ ስለእውነት ሲመሰክር እንደመጣ እራሱ ተናግሯል ፣ ተባሕትዎ መጾሙ ፣ ምንኩስና በድንግልና መኖሩን፡፡ እነዚህን ሁሉ ፈጽሟል፡፡ ታዲያ ጌታ ለምን ተጠመቀ? ስንል 3 ዐበይት ነጥቦችን እናያለን፡፡

1. ለትሕትና፡– ‹‹ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና›› እንዳለ በማቴ 1129 ለአርአያ /ለትምህርት/ እንዲሆነን ብሎ ተጠመቀ፡፡ ዮሐ 131-7

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: