RIO 2016 Under The Sign of Baphomet: ግራ የተጋባው ሳጥናኤላዊው የባፎሜት ባሪያ በኢትዮጵያ ላይ ሲደነፋ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 21, 2016
አንጋፋው ኢትዮጵያዊ አበበ ቢቂላ ከመቃብሩ ሳይነሳ አይቀርም!
ሌሎቹ (ኬኒያውን እና አሜሪካዊውን ጨምሮ) ምስጋናቸውን ለፈጣሪ ለማበርከት በመስቀል ያማትባሉ…
ወንድሞቹን ለማቀፍ፡ የኢትዮጵያን ክቡር አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ለመያዝ አሻፈረኝ ያለው ወንድማችን ግን የዲያብሎስ መሣሪያ በመሆን የባፎሜትን የትዕቢትና የጥላቻ ምልክቶች ከፍ ከፍ ያደርጋል። መጨረሻ ላይማ የኢትዮጵያን ሸሚዝ አውልቆ ቁጭ አለ። ኢትዮጵያን የወከለ አንድ ስፖርተኛ እንዳያሸንፍ ስመኝ፡ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር።
ጊዜው የጥላቻ እና የጠይዎች ነው፤ ብቅ ብቅ ይበሉ፡ ይታዩን፦
በዚሁ ኦሎምፒክስ ላይ የጥላቻ ፋብሪካዎች የሆኑት አረቦች በእስራኤል አትሌቶች ላይ አሳፋሪ የሆነ የጥላቻ ቴአትር ሲሠሩ እንደነበር ተመለከትን። (ተሸናፊው ግብጻዊ የጁዶ ታጋይ እስራኤላዊውን አልጨብጥም ሲል፤ ሳዑዲው ከእስራኤላዊው ጋር ለመታገል አሻፈረኝ ሲል፣ እንዲሁም የሊባኖስ ቡድን ከእስራኤላውያን ጋር በአንድ አውቶብስ አንጓዝም በማለት ሲያምጹ)
አገርን መወከል መንግስትን መወከል አይደለም
ዛሬ ተወናባጁ ከዳተኛ ወንድማችን የፈጸመው የክህደት ተግባር ሠለጠኑ በሚባሉት አገር ሳይቀር በሞት ቅጣት የሚያደርስ ነው። (የሜክሲኮ ኦሎምፒክስን “Black Power” ቅሌት መሰል፤ (እነርሱስ ተበዳዮች)) ይህ ወራዳ ግለሰብ በእነ ግብጽ ተገዝቶ ቢሆን አይግረመን፡ እኛ ሞኞቹ ሁልጊዜ ብናንቀላፋ፡ ጠላቶቻችን ለአንድም ቀን እንኳን አይተኙልንም። ግን መሆን ያለበት ይኖርበታል፤ በዳዮች እንደ ተበዳዮች የሚጮሁበት፤ በጎች ከፍዬሎች የሚለዩበት ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የኢትዮጵያን ማንነት ለማጥፋት፡ የኢትዮጵያን ስም በኤርትራና በኦሮሚያ ስሞች ለመተካት ሌት ተቀን የሚታገሉት ሁሉ ያፍራሉ፣ ይዋረዳሉ፣ ፍርዳቸውንም ይቀበላሉ።
በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ የአረቦቹን የጥላቻ ባንዲራ የማውለብለብ ጥሩ እድል ይኖረዋል። መንገዱን ያመቻችለት!
— Conspiracy theorist claims Usain Bolt is a member of the Illuminati – and the Olympics gave it away
ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም፤ ምስሎቹም የታሪክ ምስክሮች ይሆናሉ፦
Mario Marconi said
Yehe betam asnewari new, agherhen le telat masrekeb malet new.yehe ye erkus menfes aghelgai Emmeye Mariam Ethiopia lijioceshen tebikilen.