አለም ለቅዱሳን መቃብር ትቆፍራለች – ኢትዮጵያ ግን ለቅዱሳን ቤተመቅደስ ትሰራለች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2016
“ኢትዮጵያ በሦስቱ ህግጋት” በተሰኘው ቪዲዮ ላይ፡ ዲያቆን አባይነህ ካሤ የሚከተለውን ኃይለኛ መልእክት ያስተላልፋሉ፦
“እኛ ነብያትን፡ ቅዱሳንን እናከብራለን እንጂ ወደ ጉድጓድ አንፈቅድም፣ ደማቸውንም አናፈስም፣
ክብራቸውንም አንጋፋም – እናከብራቸዋለን – ይህ ነው የኢትዮጵያውያን ምግባራቸው – አለም ለ ቅዱሳን መቃብር ነው የምትቆፍረው – ኢትዮጵያ ግን ለ ቅዱሳን ስፍራ ነው የምታዘጋጀው፣ ቤተመቅደስ ነው የምትሰራው።
ልጅነታችን ቅዱስ ዮሐንስን ይቀድማል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስን እንቀድመዋለን፣ ካወቅንበት። ቀድመን ነው አሥራት የተሰጠነው። ልጅነት – ለ እመቤታችን አደራ የተባልነው ቀድመን ነው፡ ከመስቀሉም በፊት ነው፤ በመጀመሪያው መከራ በስደት ነው።
ስለማንናገረው ባዶ ታሪክ ይመስላል። ለሌሎች ምንም አድራሻ፡ ፍንጭ ሳይኖራቸው ስንት ቆፍረው ሊናገሩ ይሞክራሉ፡ እኛ ግን መጽሐፍ ቅዱሱ እየመሰከረልን አንገታችንን ደፍተናል። የማያስፈልግ ትህትና አለ፡ አስፈላጊም ትህትና አለ።“
አዎ! አስፈላጊው ትህትናችን አላስፈላጊ ከመሆንም አልፎ ጎጂ ወደሆነ መንገድ እየመራን ነው። ማንነታችንን አጠንቅቀን ባለማወቃችን፥ ስለማንነታችን የምናውቀውም ለማያውቀው ባለማሳወቃችንና ባለመናገራችን ብዙ ጉዳት እየደረሰብን ነው። ሠለጠኑ እንደሚባሉት መሠልጠን እንፈልጋለንን? ታዲያ የምንፈልግ ከሆነ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር አለ ይኼውም፦ በሌላው ዘንድ አንገትን በመድፋት “የሠለጠነ” ወይም ኃያል የሆነ ሕዝብ የለም። ኃያል የሚባሉ ሕዝቦች የሌላቸውን ነገር እንዳላቸው፣ ያላቸውንም አጥብቀው በመያዝና እራሳቸውንም በሁሉም መስክ ከባዕዳዊ ሌላው ሁሉ የተሻሉና የበለጡ አድርገው በመውሰድ ነው እየሰረቁና እየተዋጉ ለብልጽግናውና ለሥልጣኔው የበቁት። የኛ ግን በተቃራኒው ብዙ እጹብ ድንቅ ነገር እያለን፡ ምንም እንደሌለን አንገታችንን ለባዕዳኑ እየደፋን ያለንን በከንቱ እናስነጥቃለን። አስፈላጊ የሆነ ትህትና ብርቅ በሆነበት ዘመን ትሁታዊ አቀራረባችን የሚንጸባረቀው ለሚያስፈልገው ለወገናችን በሕዝባችን ዘንድ ሳይሆን ትህትና ለማያውቀው ነጣቂ ባዕድ፤ ለጠላት፡ በባዕዳውያኑ ዘንድ ነው። ይህ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው።
አንድ መልኩን የማይቀይር ኢትዮጵያዊ ለባዕዳኑ እንጂ ለኢትዮጵያዊው ወገኑ ኩራትን፣ ንቀትን ወይም ጥላቻን ማሳየት ፈጽሞ የለበትም። አንተም አንቺም ኢትዮጲያዊ፤ እርሱም እርሷም ኢትዮጵያውያን፤ የተፈለገው ደረጃ ላይ ቢቀመጥ፡ ማንም በምንም እርስበርስ ሊበላለጥ እና ሊናናቅ አይገባውም። እስኪ እናስብ፡ አንበሳ አንበሳን ሲያገኝ ደረቱን በኩራት ሲደፋ፦
አንበሳ ለአንበሳ ቢያገሳ
ይሆናል የጥንብአንሳ ምሳ
ባለፈው ጊዜ በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሮም የምትወሰደውን በራሪ ለመያዝ እመፈተሻ መሳሪያው ጋር ሰልፍ ላይ ከቆምኩ ከአሥር ደቂቃ በኋላ፤ ኃይለኛ የጩኽትና የጭቅጭቅ ድምጽ ሰማሁ። ጣልያናዊ ይመስላል፡ ከኢትዮጵያዊት ሴት እና ከልጃቸው ጋር ሻንጣቸውን እያሽቀነጠረና የህጻኑን ጋሪ እየገፉ ፈታሿን ኢትዮጵያዊት ሲያመናጭቃት፤ “ወቸው ጉድ!“ “ምን ዓይነት ድፍረት ነው!” አሰኘኝ። ተራዬ እንደደረሰም፤ ፈታሽ እህታችንን፡ “ፈረንጁ ሲያሳየው የነበረው ጥጋብ የሚያሳዝንና ቅሌታማነትም የተሞላበት ነበር፤ አውሮፕላን ማረፊያ አይደለም እንዴ፡ ለምን ፖሊሶች አልጠራችሁም? እነሱ በአገራቸው፤ እኛን፡ እንኳን ይህን ያህል ጩኽት አሰምተን፡ አንገታችንን ደፍተን እንኳን ስነምግባር የጎደለውና የተለየና የጠበቀ ፍተሻ ነው የሚያካሂዱብን” ስላት፤ እሷም፡ “አዎ! ትሁት ስለሆንንና አንገታችንን ስለምንደፋ እኮ ነው ድምጹን ከፍ ያደረገብን፤ በርግጥ ጋሪያቸው ችግር ነበረበት” አለችኝ። ይህን መሰሉ ድርጊት በቦሌ ሲገጥመኝ የመጀመሪያ ጊዜ አልንበረም። ከዚህ በፊት አንድ ቆሻሻ ቱርክ የፍተሻ ቦታው ወለል ቆሻሻ ስለሆነ ጫማዬን አላወልቅም ብሎ ፈታሾች ላይ ሲጮኽ እንደነበር አይረሳኝም።
ጠላቶቻችን ብዙ ናቸው፤ ሁሉም ባይሆኑም፡ አብዛኞቹ፡ በጣም የሚቀርቡን እና ከኛ ጋር የተጋቡት ሳይቀሩ፤ ጥማታቸውን ካረኩ በኋላ ቀዳሚ ጠላቶቻችን የሚሆኑት እነሱ ናቸው። ሁሉንም ነገር ለፈጣሪ በመተው ጠላትን በአምላካዊ ቁጣ ሂድ ጥፋ በማለት ማድረግ ያለብንን ነገር እራሳችንው ካላደረግን፡ ግዴለሾች፡ ሰነፎች እንጂ ፈሪህ አምላክ ናችሁ አንባልም።
ምናልባት ለአብዛኛዎቻችን የማይታየን ኃይለኛ የመንፈሣዊ ጦርነት በዓለማችን በመጧጧፍ ላይ ይገኛል። አብዛኛው የዓለም ነዋሪም ከፍተኛ የመንፈሣዊ ቀውስ ላይ ይገኛል፤ ስለዚህ አደኑን እንደ ኢትዮጵያ በመንፈሳዊ ኃብት በጣም የታደሉ አገሮች ላይ ነው የሚያካሂዱት፤ አንዳንዴ፡ ቱሪስት የሚባል ወደ ኢትዮጵያ ጭራሹን ባይገባ ጥሩ ነበር ያስብለኛል፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናልና። የጥላቻ ዘመቻ ማካሄዴ አይደለም፡ ግን በተለይ አረብ የሚባል እግሩን በአገራችን ባያሳርፍ በጎ ነው እላለሁ። በተለያዩ አጋጣሚዎች፡ በትምህርት ይሁን በሥራ፡ ከአረቦች ጋር አብረን ለመኖር የበቃን ብዙ ኢትዮጵያውያን አለን፤ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲያው፡ ሃሃሃ! ለማለት፡ ወይም ለጥቅም ካልሆነ በቀር፤ ከአረብ ጋር ጥሩ ጓደኝነት ወይም ወዳጅነት ለመመሥረት የበቃ ኢትዮጵያዊ በጭራሽ አይኖርም። ጉዳዩ፤ ከባድ የመንፈሣዊ ጉዳይ ነው፤ እንድናርቃቸውና እንድንርቃቸው የሚያስገድደን ምስጢራዊ ነገር አለ። ፈረንጁም ይቀናል፤ ግን እንደ አረብ በኛ አብልጦ የሚቀና፡ የኛን ውድቀት፣ የኛን ሞት የሚመኝ ሕዝብ የለም። አልገባንም፡ አልነቃንም እንጅ፡ ጦርነቱንማ ካወጁብን ሺህ ዓመታት አስቆጥረዋል፤ በትህትናችን ስላስጠጋናቸውም በብዙ መንገድ እኛን እየተተናኮሉና እያታለሉ ሊከፋፍሉን ሊያደክሙን በቅተዋል። እባብ መቼም ከፈሪነቱ የተንሳ ተርገብጋቢ ነገርን በቶሎ መቃኘት ይችላልና፡ አረቦቹም፡ እየተርገበገበ በራቸውን በማንኳኳት ላይ ያለውን አውሎ ነፋስ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ፡ አገራችንን ሊበጠብጧትና ሕዝቧንም እንደገና እርስበርሱ ሊያናክሱት በመሞከር ላይ ይገኛሉ። ግን፡ የፍርድ ጊዜ አሁን ደርሷልና በቅድሚያ የተፈረደባቸው እነርሱ መሆናቸውን በቅርቡ ያውቋታል። ሞኙና ተላላው ሕዝባችንም በማገገም እና በመንቃት ላይ ይገኛል፤ ለእነርሱ ግን ወዮላቸው! የኤርታ አሌ እሳት ጉድጓድ ውስጥ ከሁሉም ቀድመው የሚገቡት እነርሱ ናቸው። በባዶ የኮሩትና የጠገቡት የሚዋረዱበት ቀን ሩቅ አይደለም፤ በመጭዎቹ ሣምንታት ጉዳቸውን እናያለን።
ወደ ሰማይ ቀና ብንመልከት…
ባለፉው የአዲስ አበባ ቆይታዬ በየቀኑ ድንቅ የሆኑ ነገሮችን በሰማያችን ላይ ለመታዘብ በቅቼ ነበር፤ የሰማይ ምልክቶች ቀርበውናል፤ ደመናዎች ምስሎችን እየሳሉልን ነው፣ እንቅስቃሴዎቻቸው ቀለሞቻቸው፤ ሁሉም በእውነት አስደናቂ ሆኖ ነው የሚታየው።
ይህን ፎቶ ሳነሳ፤ አፉን ከፍቶ የሚያጓራ/ የሚያገሳ አንበሳ በመካኒሳ – ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከመስቀሉ ከፍ ብሎ በግልጽ ይታይ ነበር። ባነሳሁ ማግሥት፡ የዝናብ ውሃ ባይተዋር በሆነችው በሳዑዲዋ መካ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እና ዝናብ የህንጻ መሥሪያውን የብረት ምሰሶ ሰባብሮ መስጊዱን ማፍረሱን ስሰማ ወዲያው ብልጭ ብሎ የታየኝ…አንበሳ ፡ አገሳ… አውሎ ነፋስ ፡ በእስትንፋስ…።
“ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።“[ራዕይ 5፥5]
Leave a Reply