የክርስቶስ መንፈስ ወደ ‘ዬሬቫን’ የአውሬው መንፈስ ወደ ‘ኢስታምቡል’
ማን ወዴት እንደሄደ ለይቶ በማየት የመስቀሉ ወዳጅ ወይም ጠላት ማን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል
ቅዱስ ፓትርያርኩ፡ አባ ማቲያስ ወደ ዬሬቫን እንዳያመሩ፡ በቱርክ እና ሳዑዲ የሚደገፈው የ ‘አይሲስ‘ ቡድን መሰናክል ሆነ፡ በወንድሞቻችን ላይ አረመኒያዊ ግድያውን በዳግማዊ ትንሣኤ እለት ፈጸመ። አሰቃቂ ድርጊቱ ከዚህ ጋር ተቀነባበሮ የተካሄደ ይሆን? እነዚህ ህዝቦች ከምናስበው በላይ እጅግ በጣም ግራ የተጋቡ ናቸው!
በዛሬው እለት የክርስቶስ ልጆች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድም ከኾነው የአርመኒያ ሕዝብ ጋር በየሬቫን ከተማ ባንድላይ ሲቆሙ፡ የጸረ–ክርስቶሱ ወዳጆች ደግሞ ከገዳዮቹ ቱርኮች ጋር ለማበር ክርስቲያኖች በተጨፈጨፉባት ኮኒስታንቲኖፕል (ኢስታንቡል) ይገኛሉ። የኦቶማን ቱርክ ሙስሊሞች በ 2ሚሊየን ክርስቲያን አርመኖች እና አሹሪያኖች ላይ ያካሄዱትን አሰቃቂ የግድያ ዘመቻ መቶኛ አመት መታሰቢያ ለማጨናገፍ በነገው እለት መካሄድ የነበረበትን የ “ጋሊፖሊ” መታሰቢያ ወደዛሬው እለት በማዘዋወር የቱርክ መሪዎች ቅሌታማነታቸውን አረጋግጠዋል። የምእራቡ የመገናኛ ብዙኃንም አብዛኛውን አትኩሮት ለአርመን ክርስቲያኖች ወይም ለተሰውት ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ሳይሆን ለግፈኛው፡ ለጨፍጫፊው ቱርክ እንደሚሰጡ እንታዘባለን። ቱርክ ከአረመኖች በተዘረፈና በተሠረቀ ኃብት፣ እውቀትና ደም ላይ መመሥረቷን ቱርክን ወደ ውዲቷ አገራችንን ለማቅረብ የሚጥሩት ወገኖቻችን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
Turkey eclipses centenary of Armenian massacre by moving Gallipoli memorial
ለመሆኑ፡ “Oil Libya” በተባለ መጠሪያ የሚታወቁት የነዳጅ ማደዮች ከከተሞቻችን መንገዶች አሁን እልም ብለው መጥፋት አይገባቸውምን?