የ 27 ክለብ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 27, 2015
— ዛሬ በፈረንጆቹ መጋቢት 27 ነው»
— የጀርመኗን አውሮፕላን ከሰከሰ የተባለው ረዳት አብራሪ የ27 ዓመት እድሜ ያለው ገለሰብ ነው»
እውነት ይህ ግለሰብ ለአውሮፕላኗ መስከስና ለ150 ንጹሃን ሕይወት ማለፍ ተጠያቂ ነውን?
እኔ አይመስለኝም! ዓለማችንን በማስተዳደር ያሉት ሕጻናት ደፋሪዎችና ሰዶማውያን ቡድኖች ከባቢሎን ሳዑዲዎች ጋር በማበር ህሊናችን መቀበል ከሚያቅተው በላይ ግፍ እና በደል በሕዝቦች ላይ በመፈጸም ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ አየርመንገድና ንጹሀን ተሳፋሪዎቹን በቤይሩት የከሰከሱት እነርሱ ናቸው (ልበአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀበት የአለም እግርኳስ ዋንጫ አጥቢያ) እልባት ያልተገኘለት የማሌሺያ አውሮፕላኖች መጥፋትና መከስከስ (የዩክሬኑ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅት) አሁን ደግሞ ያው ባቢሎን ሳዑዲ በቀድሞዋ የኢትዮጵያ ግዛት፡ በየመን ጭካኔ የተሞላበት የቦንምብ ድብደባ በከፈተችባቸው ቀናት የጀርመኗ የሕዝብ አመላላሽ ጠያራ ይህን መሰል አሰቃቂ አደጋ። ልክ የማሌዢያ አየር መንገድ የዜና ማሰራጫዎችን ሁሉ ትኩረት ከዩክሬኑ አስከፊ ፀረ=ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ዘመቻ (50.000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች አልቀዋል) እንደነጠቀው፡ ይህ የጀርመን አውሮፕላን አደጋም የዓለምን አትኩሮት በየመን ከሚካሄደው ጦርነት የዓለምን አትኩሮት በመቀየር ላይ ይገኛል።
የዚህ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ በሚያስገርም ፍጥነት ለዓለም መገለጡና ይህንም የ27 እድሜ ያለው ግለሰብ ቶሎ መምረጣቸው፡ ምናልባት ከ ቁጥር 27 ጋር የሚያገናኝ ነገር ይኖር ይሆን? ከዚህ ቀደም ይህን አጭር ጽሁፍ አቅርቤ ነበር።
ያለፉትን ሰዎች ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
Leave a Reply