Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2015
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    232425262728  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 21st, 2015

አቡነ አረጋዊ / Abune Aregawi ቤ/ክርስቲያን / Church

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 21, 2015

በዝቋላ ገዳም የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር በሚዲያ የተሰራጨው ዜና ማረሚያ እንዲሰጥበት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ

በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ላይ በመጋቢት ወር መጨረሻ የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር መስከረም 15 ቀን 2007 .. በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ መተላለፉ ተገቢ እንዳልሆነና ችግር ሊፈጥር የሚችል መሆኑን በመግለጽ የተላለፈው መረጃ እርማት እንዲደረግበት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ለክቡር አቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡

“የሃይማኖቶች እኩልነት በታወጀበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕግ መንግሥት አንዱ ቤተ እምነት የሌላውን እምነት መንቀፍም ሆነ መንካት እንደሌለበት ተደንግጓል” ያሉት ቅዱስነታቸው፤ በሚዲያ ሽፋን የተሰጠው ጉዳይ ሕገ መንግሥቱን የሚተላለፍ፤ የገዳሙን መናንያን መነኮሳትና በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝበ ክርስቲያኖችን የሚያስቆጣ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለተዘገበው ጉዳይ እርማት እንዲሰጥበት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ለክቡር አቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: