Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2014
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 28th, 2014

ለታኅሣሥ ገብርኤል እንኳን አደረሰን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 28, 2014

የታኅሣሥ ገብርኤል

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደየሱስ መጽሐፍ የተወሰደ

ከከበረ ሰላምታ ጋር

በታኅሣሥ ወር በ፲፱ነኛው ቀን የሚውለው የ ታኅሣሥ ገብርኤልበዓል የሚከበርበት ምክንያት እንዲህ ነው፦

እግዚአብሔር በሙሴ መሪነት የእሥራኤልን ሕዝብ በግብፅ አገር ይገኙበት ከነበረው የባርነት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ቤተ መቅደሳቸውንና ከተማቸውን በኢየሩሳሌም አድርገው በምድረ ከነዓን እንዲኖሩ አበቃቸው። እነርሱ ግን ባካባቢያቸው ያሉትን አሕዛብ እየተከተሉ አምልኮ ባዕድን በመፈጸም አምላካቸውን እግዚአብሔርን አሳዘኑት። በነቢያቱ ቢመክራቸውና ቢገሥፃቸውም በዚያ ኃጢአታቸው እየጨመሩበት ከመኼድ በቀር ከበደላቸው ተጸጽተው ሊመለሱ ጨርሶ የማይቻል ኾነ።

በዚህ መልክ በፈጣሪያቸውና ከእርሱ ጋር በተጋቡት ቃል ኪዳናቸው ላይ በሥውርና በገሃድ ያካሂዱት የነበረው ክህደት ዓመፅና አመንዝራነት፡ በመጨረሻ ጽዋው ስለሞላ እግዚአብሔር ለዚህ ድርጊታቸው ምስክር የሆነችው ታቦተ ጽዮን ከእሥራኤላዊው ንጉሥ፡ ከሰሎሞንና ከኢትዮጵያዊቷ ንግሥት፡ ከመከዳ በተወለደው፡ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካይነት በቅድሚያ ወደ ኢትዮጵያ እንድትሄድ አደረገ። ከዚያ በኋላም ያወረሳቸውን አገርና ከተማ ወርሮ ይበዘብዝ ዘንድ አረማዊውን ንጉሥ፡ ናቡከደነፆርን ታላቅ የሠይፍ ኃይልን አስታጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፡ እርሱም በዚያ የቅጣት ተልእኮውን እንዲፈጽም ኃጢአተኛውንም የእሥራኤል ትውልድ ፈጅቶ የተረፉትን በምርኮ ወደምድሩ ወደ ባቢሎን እንዲወስዳቸው ለስደትም እንዲዳረጋቸው አሠለጠነው።

ለዚያ ስደት ከተዳረጉት እሥራኤላውያን መካከል በሃይማኖታቸው የጸኑና በምግባራቸው የተጠናከሩ፡ አካሄዳቸው ከነቢዩ ዳንኤል ጋር የሆኑ፡ አናንያ፥ አዛርያን ሚሳኤል የተባሉ መንፈሳውያን ወጣቶች ነበሩ። እነዚህ ሠለስቱ ደቂቅ የተባሉት ሦስት ልጆች በእውቀታቸውና በብልህነታቸው ተመርጠው የንጉሡ ሹማምንት ኾነው ያገለግሉ ነበር።

የኋላ ኋል ግን የአገሩን አማልክት እንዲያመልኩ ንጉሡ ላቆመውም ጣዖት እንዲሰግዱ ያን ባያደርጉም በአዋጅና ባደባባይ እየነደደ ባለ አስፈሪ የእሳት ነበልባል ውስጥ የሚጣሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የፈተና ጥያቄ ከንጉሡ ቀረበላቸው። እነርሱም ለገንዘብና ለሹመት ጓጉተው የንጉሡን ቍጣም ፈርተው አምላካቸውን የማይክዱ፡ ሃይማኖታቸውንም የማይለውጡ መሆናቸውን በመግለጽ ንጉሥ ሆይ! የምናመልከው አምላካችን ፡ ከእጅህም ሆነ ከዚህ ከሚነድደው የእሳት ነበልባል ሊያድነን ይችላል፡ ባያድነንም እንኳ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ጣዖት እንዳንሰግድለት እወቅ!” ሲሉ በድፍረትና በቆራጥነት መልስ ሰጡት።

በዚህ ጊዜ ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ከንጉሡ ታዝዞ ሦስቱም ገድለኞች በሚነድደው እሳት ውስጥ ተጣሉ። ወደ እሳቱ ሊጥሏቸው የወሰዷቸው ኃያላንም በነበልባሉ ብርቱ ወላፈን እየተቃጠሉ ሞቱ።

ወደ እሳቱ ውስጥ ታሥረው የተጣሉት እኒህ መንፈሳውያን አርበኞች ግን የእግዚአብሔር መልአክ እሳቱን አቀዝቅዞላቸው በነበልባሉ መካከል ወዲያ ወዲህ ሲመላለሱ ከመታየት በቀር በአካላቸው ቀርቶ በልብሳቸው ላይ እንኳ አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከተፈረደባቸው የቃጠሎ ሞት ድነው በደህና ሊወጡ ችለዋል። ይህንም፡ የዚያን ጊዜም፡ ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ፡ ፈጥኖም ተነሣ፡ አማካሪዎቹንም ሦስት ሰዎችን አሥረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? … እነሆ፡ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን አያለሁ ምንም አላቆሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡ብሎ መለሰ።

የአራተኛው መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላልየተባለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መኾኑን ከትውፊታችን አግኝተነዋል።

በሃይማኖት ሳይወላውሉ በምግባር ተጠናክረው እስከመጨረሻው፡ ማለትም የሞት ጽዮን ለመቀበል ተዘጋጅቶና ቆርጦ እስከመቅረብ ድረስ በጅመሩት ገድል ጸንቶ መገኘት የሚያስከትለው ውጤትና የሚያስገኘው ፍሬ በነፍስ ብቻ ሳይኾን የሥጋ ሞትን ጭምር በማስቀረት፡ የምሕረት ሕይወትን በክፋት ኃይላትም ላይ ድልን የሚያቀዳጅ የመላእክት ተራዴነትን መኾኑን በዚሁ በታኅሣሥ ፲፱ ቀን የምናከብረው የታኅሣሥ ገብርኤልበዓል ያስታውሰናል፡ ያስተምረናልም።

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

MYSTERY BABYLON THE GREAT

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 28, 2014

ወደ ባቢሎን አረብ አገራት በመሄድ ለከፍተኛ መንፈሳዊ ቀውስ ከሚጋለጡት ምስኪን እህቶቻችን መካከል አንዳንዶቹን ቀርቤ ሳነጋግር፡ ደግመው ደጋግመው የሚያካፍሉኝ አንድ ትልቅ ምስጢር ቢኖር፡ ከመላእክት ሁሉ: ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በይበልጥ እንደሚቀርባቸው፡ በየጊዜው እንደሚገለጥላቸውና ነፍሳቸውንም ለማደስ ይበቁ ዘንድ ተዓምራዊ እርዳታውን ደጋግሞ እንደሚለግሳቸው ነው። ምስጋና ለእግዚአብሔር! የባቢሎን መውደቂያ እና መሠባበሪያዋ ዕለት ተቃርቧል፤ ለንዋያዊ ጥቅም ሲሉ፡ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ፡ እራሳቸውን ለመሸጥ የፈቀዱት፡ ይባስ ብሎ፡ ባቢሎን አረብና ቱርክን ወደ አገራችን በማምጣት ኢትዮጵያን ለመበከል፡ ሕዝቦቿን ለመበረዝና ለመመረዝ የደፈሩት ሁሉ ወዮላቸው! ይህ ቀላል ጉዳይ አይምሰላችሁ፤ የፈተናው ጊዜ እያለቀ ነው፡ አሁኑኑ በፍጥነት ካልተጸጸጣችሁና ንስሐ ካልገባችሁ፡ ሰይጣን፡ የባቢሎን አምላክ አኝኮ ታች ወዳለው ጉርጓዱ ይተፋችኋል!

After the Flood the city state of Babylon became the center of Satan’s great attack on human history. After the destruction of the Tower of Babel, Babylon remained in hidden mystery form in Satan’s Cosmic System. The world counterattack of Mystery Babylon continued through the ages. The power of the great evil in the world today is defined through the symbolism of the Evil King and the Prostitute of Babylon in Revelation.

Foreword

Mystery Babylon, which is taught from Genesis to Revelation, is one of the major doctrines in the Bible and one of the major themes of human history. Yet, this strategically important doctrine lies beyond the grasp of most people. So well-hidden is the mystery, right under the nose, that the symptoms are seen but not the cause. The reason lies in the power that Satan has over this world through fundamental values like the love of money and honey (sexuality). Satan controls the pastors as well as the congregations. He controls the parents as well as the children. So, each generation is doomed to repeat the mistakes of the past.

It doesn’t have to be this way. The Light is available for those who want it. However, the Light to see Mystery Babylon will only be revealed to those whom the Lord chooses. Only true believers can see the Light, and the Lord decides who those true believers are. Many of the best and brightest students of Bible Doctrine are totally oblivious to the paradigm of Mystery Babylon. They talk a good fight, but they are not genuine. The power of Christianity seems to have eluded too many of the so-called doctrinal believers, who are so busy conforming to Mystery Babylon that the power of God has departed. These people can’t make a decision by themselves. The Holy Spirit is a mystery to them, whereas, they accept Satan’s Mystery Babylon as the gospel.

Mystery Babylon is a doctrine for Christians who have reached Spiritual Maturity and are advancing to Spiritual Rapport. It is not meant for arrogant theologians who are educated beyond their intelligence. Yet, even though the doctrine may only be mastered in Spiritual Rapport, it should be heard even by school children, who are bombarded with human viewpoint from Satan’s factory of lies and deception. Christian schools are blind to Mystery Babylon the same as their secular counterparts. And no Christian teacher should teach without studying this all-important doctrine of our Christian heritage.

The exposure of Mystery Babylon, which is Satan’s Cosmic System, is not meant to be an academic exercise. It has far-reaching practical value. It doesn’t take a professor to recognize daylight from dark. When Marriages don’t click, there must be a reason. There is. The Prostitute of Babylon, who represents Satan, has infiltrated every institution of society, especially the Church. She is out to destroy Marriage; yet, most Christians are oblivious to her. Satan is much more brilliant and much more active than most people think. He has a master plan in place to destroy every divine institution and every Christian life. But genuine Christians who Love the Lord Jesus Christ and obey the Holy Spirit can see through Satan’s ploy. They can grasp his master plan of Mystery Babylon because it is written in the Bible. And they can see Spiritually what is happening in the world around them.

There are many practical applications to be gained from mastering the doctrine of Mystery Babylon. Some value could be gained from simply looking at the pictures in this document. The pictures of Light and darkness in the human body can be applied to breast cancer as well as other diseases and maladies. The source of marital problems and lack of harmony can be understood. The true course of history is explained. Social relationships and relationships with animals are cast in a new light. The love of money and honey are exposed. Two of the most wonderful Christians in history, Patrick and Brigid, from Ireland, are introduced. And Bible prophecy is accurately interpreted. The attacks on Client Nation Israel are explained. And the attacks on the Church in light of the seven churches of Revelation has application throughout the Church Age. For those who will master the doctrine, the application will come.

Seeing the faithfulness of God in light of the Satanic counterattack of Mystery Babylon will challenge the Christian to operate inside the Integrity Envelope. The impact of genuine Christian Integrity on human history will be seen. And Satan’s counterattack to prevent the Christian from achieving Spiritual Rapport with God and harmonious rapport with the spouse and all mankind will be exposed.

Preview of Contents

  • Lessons of Eden
  • Antediluvian Anarchy
  • Tower of Babel
  • Babylon the Great
  • David and Solomon
  • Jezebel
  • Daniel
  • Early Church
  • Prostitute of Babylon
  • The Evil King and Prostitute in Modern Times
  • The Spiritual Solution

Continue reading…

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: