“Demons are Seductive, sneaking, friendly, cajoling, evil, monstrous”
በጥሞና መደመጥ ያለበት ድንቅ ትምህርት›
ቱርክ የጸረ–ክርስቶሱ መቀመጫ ምድር መሆኗን መጽሐፍ ቅዱስ ጠቁሞናል። ቱርክ ክርስቲያን በሆኑ ሕዝቦች ላይ ከፍተኛ በደል የምታደርስ አገር እንደሆነች ታሪክ ያስተምረናል። አሁን በኢራቅና ሶሪያ ክርስቲያኖች ላይ ለሚካሄደው አሳዛኝ እልቂት ቱርክ ቁልፍ የሆነ ሚና ትጫወታለች። በምዕራባውያኑ የሚደገፉት ቱርኮች፡ ሳዑዲዎችና ካታሮች በኢራቅና ሶሪያ የሚገኙትን ጥንታውያን ክርስቲያኖች ከአካባቢው ሙልጭ አድርገው ለማስወገድ ዲያብሎሳዊ ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው። ቱርክ የአገራችን ጠላትና ለቀደሙት አባቶቻችን ከባድ ፈተና በመሆን አገራችን ኋላ ቀር እንድትሆን በማድረጉ ረገድ ዘንድ ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች። 15% የሚሆነው የህብረተሰባችን ክፍል ግን ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ለመማር ፈቃደኛ ባለመሆኑ የተቀረውን ጤናማ ዜጋ እያታለለ፡ በማድከምና በመጉዳት ላይ ይገኛል።
በተለይ በአሁኑ ዘመን ዓይኖቻችን እያዩ፡ ጆሮዎቻችን እየሰሙ በወገኖቻችና በአካባቢያችን በሚገኙት ወንድማማች/እህትማማች ክርስቲያን ሕዝቦች ላይ ቱርኮችና አረቦች የሚፈጽሙትን በደል ተረስቶና ቸል ተብሎ፡ እነዚህ የእግዚአብሔር ጠላቶች በ “ኢንቨስትሜንት” ስም ወደ ውዲቷ አገራችን በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ። ይህ ትልቅ ስህተተት ነው። ደጋግሜ የምናገረው ነገር ነው፡ (ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣኔ ደረጃ ላይ ደርሳ የነበረው፡ ባካባቢያችን ካሉት ወደ ኋላ ጎታች ኃይሎች ርቃና እራሷን ዘግታ በኖርችበት ዘመን ነበር።) አንዳንዴ በሁኔታው በመገረም ቁጭ ብዬ ሳሰላስል፤ ““ማነው እነዚህን ጠላቶቻችንን የሚጋብዛቸው? ይህን ያህል ደህይተናልን? ምናልባት ደግሞ፡ ወዳጅህን ቅረበው፡ ጠላትህን ደግሞ በጣም ቅረበው!” የሚለውን መርሆ ተከትለው ሊሆን ይችላል?” እያልኩ እራሴን አጽናናለሁ። ሆኖም፡ እውነት የዛሬው ትውልድ ምን ያህል ብሱልና ብልጥ ነው፡ ጠላቱን በማቅረብ በመሣሪያነት ሊገለገልበት/ሊጠቀምበት የሚችለው?
እስራኤልንና አርመንያውያን ክርስቲያኖችን በመተናኮል ላይ የሚገኘውና በአውሮፓውያን አገሮች በወንጀለኛነቱ የታገደው “IHH” (International Humanitarian Relief Organization) በ “እርዳታ ሰጪ” ሽፋን የሚንቀሳቀስ እስላማዊ የቱርክ ድርጅት ነፃ በሆነና ጸጥ ባለ መልክ ጂሃዳዊ እንቅስቃሴውን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተጠቁሟል
የሚለውን ዜና ከመገናኛ ብዙኃን ስሰማ ወዲያው የመጣልኝ ፡ “እንዴ፡ በኢትዮጵያችን አፓርታይዳዊው የእስልማ ሸሪዓ ፍርድ ቤት አለ እንዴ?” የሚለው ጥያቄ ነበር። በጣም የሚያሳስብ እኮ ነው! እንዴት ነው ይህ ሊከሰት የቻለው? ፈሪህ እግዚአብሔር በሆነችውና አብዛኛው ሕዝቧ የክርስትና ተከታይ በሆነባት አገራችን “የፌደራል ጠቅላይ ተዋሕዶ ክርስትና ፍርድ ቤት” የሚል ፍርድ ቤት የለም፡ ዓለማዊ የሆነው መንግሥቷም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ዓይን አይቶ ለመፍረድ ያስችለው ዘንድ “የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት” የሚል ፍርድ ቤት አቋቁሟል። ታዲያስ!?
ሃቁን በግልጽ ለመናገር፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ሰላማዊ ሱፊ ቢሆንም፡ ግን ልቡ ለ ‘ኡማው” እና ለሳዑዲ አረቢያ እንደሚመታ ለማወቅ የልብ ሃኪም መሆን አያስፈልግም፤ እራሳቸው በቀጥታ በግልጽ የሚናገሩት ነገር ነው። ታዲያ ለምንድን ነው ለአገራችን ከባድ ሸክም ለሆኑትና በሚያሳዝን መልክ ከወደቁበት መነሳት ለተሳናቸው ሙስሊም ወገኖቻችን ይባስ ብለን ይህን ጭካኔ በተሞላበት ኢ–ሰብዓዊ የሻሪዓ ሕግ የሚተዳደር ፍርድ ቤት ለማቋቋም የቃጣን? ዛሬ፡ አገራችንን ጨምሮ መላው ዓለምን በማሳሰብ ላይ ያለው የእስላሞች ሽብርና አሰቃቂ ጂሃዳዊ ጦርነቶቻቸው በቂ ማስረጃዎች አይሆኑንምን? ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ግብጽ፣ ናይጀሪያ፣ መካከለኛዋ አፍሪቃ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን፣ ማሌዢያ ወዘተ. ከሚያሳዩን ፊልም መማር እንዴት ተሳነን? ይህን ታሪካዊ ስህተት ቶሎ ማረም ግድ ነው፤ የረጅም ጊዜ ልምዱ ያላት አገራችን በተደጋጋሚ ከምትሠራቸው ስህተቶች ተቆጥባ እንደ አውስትርያ ያሉት አገሮች የሚወስዱትን ዓይነት እርምጃ በፍጥነት መውሰድ ይኖርባታል።
ሌላ ተጨማሪ፤ በትናንትናው ዕለት የተባበሩ አረብ ኢሚራቶች ካቢኔት 82 የሚሆኑትን ዓለም አቀፋዊ የእስላም ድርጅቶች “ሽብር ፈጣሪዎች ናቸው!” የሚል ስም ሰጥቷቸዋል። ያው እንግዲህ እራሳቸው እየመሰከሩ ነው፡ አንዴ ይረዷቸዋል፡ ሲያመቻቸው ደግሞ አሳልፈው ይሰጧቸዋል…ጋለሞታዋ ባቢሎን…የድርጅቶቹ ብዛት የሚያስገርም ነው…እንደዚህ ተደራጅተው እርስበርስ ቢጨራረሱ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡ ለምን ገሃነም እሳት አይገቡም! የሚያስገርመው ግን ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዳንዶቹ በኢትዮጵያ አገራቸን በይፋ እንዲንቀሳቀሱ ፈቃዱን ማግኘታቸው ነው። ለምሳሌ፡ የኤሚሬቶች የሽብርተኛው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት በኢትዮጵያ በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ ይንቀሳቀሳሉ፦
- Islamic Relief Worldwide
- Council on American-Islamic Relations (CAIR)
- International Union of Muslim Scholars