በጠዋት ተነስቶ በዝናብና በብርድ ለ አንድ ሰዓት ያህል የእንጦጦን ተራራ ከ ቍስቋም ማርያም እስክ ቅድስት ማርያም በመውጣት ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንዲሆን እምነቱ የጠራውን ሕዝብ ማየት በጣም ያስደስታል፣ ያስገርማል፡ የተቀረውንም ዓለም በእውነት በጣም ያስቀናል። ከቅዳሴ በኋላ ቁሉቁለቱን ሲወርድ የነበረው የምዕመናን ብዛት አፌን አስከፍቶኝ ነበር፤ የዓመቷ ማርያም ስትሆን ምን ያህል ሰው እንደሚሄድ መገመት አያዳግትም። የክርስቶስ ጠላቶች ወዮላችሁ፡ መርዛችሁ አይሠራም! መንፈሰ–ጠንካራና በፍርድ ጊዜ መስካሪ ትውልድ ድምጹን ዝቅ አድርጎ በመምጣት ላይ ነው!